ልብ-ወለድ
አዲሱ መስሪያ ቤት ከተቀጠርኩ ትንሽ ጊዜ አለፈኝ፡፡ “ጊዜ ንጽጽር ነው” የሚለው የሰአቱ አቆጣጠር ትዝ ሲለኝ ቀና ብዬ ተመለከትኩት፡፡ ሰአት አልፎኛል፡፡ ሰላሳ አመት እንደማለት ነው፡፡ አንድ ሰአት እና አንድ አመት ብዙ ለውጥ የላቸውም፡፡ ህይወት እና ስራ አንድ ናቸው፡፡ ሀገር እና መስሪያ…
Read 3381 times
Published in
ልብ-ወለድ
አባ ማቴዎስ ዛሬ ስሜታቸው ድብልቅልቅ ብሎ ነው ከአልጋቸው የተነሱት፡፡ ሰሞኑን በጣም ደስ ብሏቸው ነበር የከረሙት፡፡ ሳራ (ያሳደጓት ልጃቸው) ከሁለት ቀን በኋላ ልታገባ ነው፡፡ በዛ ላይ እህቷ ርብቃ የዛኑ ቀን ቅዳሜ የኮሌጅ ትምህርቷን ትመረቃለች፡፡ ከምትማርበት ከተማ ወደነሱ የገጠር ከተማ ዛሬ እንደምትገባ…
Read 3060 times
Published in
ልብ-ወለድ
ከስድስት ኪሎ ካምፓስ ስወጣ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ይላል፡፡ ቤተክርስቲያን ለመሄድ ነጠላ ከለበሱ እና ለእስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማለዳ ከነቁ ጥቂት ተማሪዎች በቀር ጊቢው ለማለዳ ወፎች ተለቋል፡፡ ታክሲ ይዤ ለ5 ደቂቃ ያህል ከተጓዝኩ በኋላ ከታክሲ ወርጄ አንድ “ጥቃቅን” የመንግስት ቤቶች የሞሉበት ግቢ ደረስኩ፡፡…
Read 3666 times
Published in
ልብ-ወለድ
“የማስታውሰው በልጅነቴ መሳል እወድ ነበር” አለ አይኑን ከእኛ ላይ እና ከአሁን አንስቶ ወደ ልጅነቱ አማትሮ እየተመለከተ፡፡ “ሶስተኛ ክፍል በሳልኩት ስዕል ወላጅ ጥራ ተባልኩ” ብሎ አቋረጠ፡፡ አርቆ ልጅነቱ ላይ የሚያየውን ምስል በቀጥታ እየነገረን ይሁን ወይንም ለሱ የሚታየውን በጊዜ ርቀት እየተጭበረበረበት እውነትነቱን…
Read 3477 times
Published in
ልብ-ወለድ
እሁድ ዛሬ ሰንበት ነው፡፡ ጠዋት ሶስት ሰዓት አካባቢ፡፡ በአዘቦት ቀን በዚህ ሰዓት ጐዳናው ላይ ፈሰው ከፀሐይ ንዳድ በማያስጥል እጃቸው ግንባራቸውን ከልለው ወደ ታክሲ መምጫ በጉጉት የሚመለከቱ ሰዎች፣ ተገፈታትረው ተረጋግጠው የሚሳፈሩ ሰዎች፣ ቢሳፈሩ ቢሳፈሩ የማያልቁ ሰዎች…ዛሬ የሉም፡፡ ነጭ ነጠላ የለበሱ ከቤተ…
Read 3296 times
Published in
ልብ-ወለድ
እዚህ ጭርንቁሳም ሰፈር ውስጥ እየኖርህ የሰማይ ግዝፈቱ፤ የምድር ስፋቱ፤ የተፈጥሮ ትንግርቱ አይታይህም፡፡ ትንሽ አሳቢ ነኝ ብለህ አንገትህን ብታቀና ከዛጉ የቆርቆሮ ጣሪያዎች ላይ የተኮለኮሉ ድንጋዮች ለአይንህ ይቀርባሉ፡፡ ጣራው መሬት እስኪመስልህ ድረስ፡፡ ለማን ትፈርዳለህ? ለአንጀትህ ወይስ ለሆድህ? “አንጀቴም አንጀቴ ሆዴም ሆዴ ነው”…
Read 4088 times
Published in
ልብ-ወለድ