ልብ-ወለድ

Saturday, 02 November 2019 13:36

ገጣሚውi

Written by
Rate this item
(5 votes)
አባቴ ቀን ከሌት ነበር የሚፅፈው፡፡ በልጅነቴ ከጓደኞቼ ጋር ስጫወት ቆይቼ ቤት ስገባ ጠረጴዛና ወንበሩ መሀል አገኘዋለሁ፡፡ባለቅኔ ነው አባቴ፡፡ ቅኔው ግን ከሰዎች የመረዳት አቅም በላይ ስለሆነ ሰው ሳያውቀው፤ መጽሐፍ ሳይኖረው አለፈ፡፡ ፅፎ… ፅፎ… ፅፎ … ማሳተም ባይችል፤ አንድ ቀን ስራዎቹን ሰብስቦ…
Saturday, 26 October 2019 12:35

ማራ

Written by
Rate this item
(10 votes)
 መኝታ ቤቴ ውስጥ ነኝ፡፡ መስኮቱ እንደተከፈተ ነው፡፡ ከውጪ የሚገባው ቀዝቃዛ ነፋስ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ቅዝቃዜ ቢኖረውም፣ መስኮቱን ልዘጋው አልፈለግሁም:: ደረቴና ክንዴ እንደተራቆተ ነው፡፡ አብዝቼ በጠጣሁት መጠጥ ምክንያት የፈዘዙ ዐይኖቼን ከመኝታ አልጋዬ ፊት ለፊት ከቆመ የልብስ ቁምሳጥን ጋር አብሮ ከተሠራ…
Rate this item
(3 votes)
የመጽሐፌ ስኬት ፍርሃት ፈጠረብኝ የምትለው ደራሲ በዚህች አጭር ጽሑፌ የማወጋችሁ ኤልዛቤት ጊልበርት ከተባለች አሜሪካዊት ደራሲ የሰማሁትን ንግግር ነው፡፡ ከደራሲዋ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የማውራት ዕድል አልገጠመኝም፡፡ በዲቪዲ የተቀረፀውን ንግግሯን የሰማና የተመለከተ ደራሲዋን አግኝቶ ለማውራት ቢቋምጥ ግን አትፍረዱበት፡፡ ንግግሯ ይጥማል፡፡ ሌክቸር…
Rate this item
(4 votes)
“ሔዋን…ሔዋን”እንደ እባብ ወደ ጐጆው ውስጥ እየተሳበ ይጣራል፡፡ ሀሳብ ጓዙን ጠቅልሎ፣ ግሳንግሱን በእጁ አንጠልጥሎ፤ ልቡ ውስጥ ውሎ ማደር ጀምሯል:: ሀሳቡ ምክንያት አልባ አልነበረም፡፡ ልጆቹ ከእናታቸው ጋር በፍቅር ሲተሻሹ አየ፡፡ ሚስቱ ልጆቿን እያገላበጠች ስትስም (ልክ እሱ መጀመሪያ እሷን ሲስማት እንደሆነው ልቧ ጥፍት…
Rate this item
(1 Vote)
. . . እና ምን ይደረግ?ስለእናቶች ክብር እናት ያለው ሁሉ ተነስቶ ይውረግረግ?ሺ ሻማ ይለኮስ? ርችት ይተኮስ? አዲስ ጥበብ ቀሚስ ኩታ፣ ቅቤና አደስቀጤማ ይነስነስ? ምድሩ ይታረስ? በእንቁ ዕንቆጳዝዮን ልስራ እቴዋ መቅደስ?የት አባቴ ልድረስ አንቺን ለማወደስ?ውድ ሽቶ ይረጭ እጣን ጢሱ ይጨስ ከርቤና…
Monday, 09 September 2019 11:35

ቅናት!

Written by
Rate this item
(6 votes)
ከስራ መጥቼ መክሰስ እንኳን ሳልበላ ወደ ጥናት ክፍል አመራሁ፡፡ የያዝኩትን ጥቁር ቦርሳ ከጠረጴዛ ላይ አሳረፍኩና መጋረጃውን ገልጬ መስኮቱን ከፈትኩት፡፡ ውጭ ህፃናት የእግር ኳስ ይጫወታሉ፡፡ ሌሎች ጥባጥቢ ያንጠባጥባሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ አንድ ጅራፍ እየተቀያየሩ ያጮሃሉ፡፡መጋረጃውን ዘግቼ ጀርባዬን ለመስኮቱ ሰጥቼ፣ እጄን አጣምሬ ቆምኩኝ፡፡…