Saturday, 02 March 2024 12:10

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትን በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ”የሥራ መልቀቂያ አስገቡ“ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን የባንኩ ባለድርሻ አካላት ገለጹ፡፡

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሆኖም  መረጃው ሙሉ በሙሉ ሃሰተኛ ነው ብለዋል - ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት የሥራ መልቀቂያ አስገቡ በሚል የተሰራጨው ሃሰተኛ መረጃ የባንኩን ጥቅም እንደሚጎዳ የጠቆሙት የባንኩ ባለድርሻ አካላት፤ ሃሰተኛ መረጃውን ያሰራጩ ማህበራዊ ሚዲያዎችንና ግለሰቦችን በህግ እንደሚጠይቁ አመልክተዋል፡፡

Read 808 times