Wednesday, 28 February 2024 20:57

ጠ/ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማፍረስ ፕሮጀክት እንደማይሳካ ተናገሩ

Written by 
Rate this item
(3 votes)

ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ ላይ የሚረባረቡት ተስፋ ስላላት ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ ኢትዮጵያውያን ሃገራቸውን ስለሚወዱና የመጨረሻው የቁርጥ ጉዳይ ከመጣ ህይወታቸውን ገብረውም ቢሆን እንደ አባቶቻቸው አገር ስለሚያስቀጥሉ ኢትዮጵያን የማፍረስ ፕሮጀክት አይሳካም ብለዋል፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ሰሞኑን ከሶማሌ፣ አፋር፣ ሐረሪ፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልሎችና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡

ድሮ እኛ እንዳንገነጠል ትሰጉ ነበር፤ አሁን እኛ እየሰጋን ነው አገራችንን እንዳትበትኗት እንዳታፈርሷት የሚል ተገቢ ስጋት ከሶማሌ ክልል መነሳቱን የጠቆሙት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያን ማፍረስ የሚፈልጉ ብዙ ሃይሎች ቢኖሩም ኢትዮጵያ ግን አትፈርስም ብለዋል፡፡

ማፍረስ ቢችሉማ ዓምናም ካቻምናም፣ የዛሬ 20 ዓመትም ሞክረው ነበር፤ ግን አይችሉም ብለዋል - ጠ/ሚኒስትሩ፡፡

ለምንድን ነው ኢትዮጵያ ላይ ጠላቶቻችን የሚረባረቡት ያላችሁ እንደሆነ ተስፋ ስላላት ነው፤ ሲሉም አስረድተዋል፡፡

ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሁሉም መንገድ ሞክረዋል፣ የትኛውም ሙከራ ግን ኢትዮጵያን ማፍረስ አይችልም ያሉት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፤ ኢትዮጵያውያን ሃገራቸውን ስለሚወዱና የመጨረሻው የቁርጥ ጉዳይ ከመጣ ህይወታቸውን ገብረውም ቢሆን እንደ አባቶቻቸው አገር ስለሚያስቀጥሉ ኢትዮጵያን የማፍረስ ፕሮጀክት አይሳካም ብለዋል፡፡

Read 777 times