Saturday, 23 December 2023 10:45

በአለማቀፋዊ ተቋማት ላይ እየተወሰደ ያለው ተገቢ ያልሆነ እርምጃ ከባድ ዋጋ ያስከፍላል ተባለ

Written by  መታሠቢያ ካሣዬ
Rate this item
(0 votes)

የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቢሮውን ሊዘጋ እንደሚችል አስጠንቅቋል
                      

          መንግስት በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ አለም አቀፍ ተቋማትና በዲፕሎማሲያዊ ማህበረሰብ አባላት ላይ እየወሰደ ያለው ተገቢ ያልሆነና አለማቀፋዊ ህጎችን የጣሰ ድርጊት ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍልው እንደሚችል የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዳዮች ምህሩ ዶክተር አንተነህ ተስፋዬ ገለፁ።
የአፍሪካ ልማት ባንክ አለማቀፍ ሠራተኞቹን ለእስርና ለጥቃት የዳረገው ክስተት ሙሉ በሙሉ የማይፈታ ከሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ግንኙነት እንደሚሻክር በመግለጽ፤ በአገሪቱ የሚገኙ አለም አቀፍ ሠራተኞቹን በአስቸኳይ ከአገሪቱ እንደሚያስወጣ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ባንኩ በዚሁ መግለጫው፤ ሁለት ሠራተኞቹ በአዲስ አበባ ከተማ ከህግ ውጪ በፀጥታ አካላት ታስረው አካላዊ ጥቃት የደረሰባቸው መሆኑን አስታውሶ፤ ሰራተኞቹ የተፈቱት ጉዳዩን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ካሳወቀ በኋላ መሆኑን አመልክቷል። ይህ ህገ-ወጥ እርምጃ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ባደረገችው የአስተናጋጅ አገር ስምምነት ውስጥ ያለውን የዲፕማሲያዊ ያለመከሰስ መብትና ልዩ ጥቅሞችን የኢትዮጵያ መንግስት የምርመራ ውጤቱንና በጥፋተኛ አካላት ላይ ወሰደውን እርምጃ ለህዝብ ይፋ እስሚያደርግ ድረስ አለም አቀፍ ሰራተኞቹን ከአገር እንደሚያስወጣ አስታውቋል። ኢትዮጵያውያን ሰራጠኞቼ ግን በስራቸው ላይ ይቆያሉ ብሏል።
አገሪቱ በአለማቀፋዊ ተቋማት ላይ እየወሰደች ያለው ተገቢ ያልሆነ እርምጃ እንድትመረምርና ራሷን እንድትፈትሽ የሚያደርጋ እርምጃ እንደሆነና ከአለማቀፍ ማህበረሰብ ጋር ያላትን ግንኙነት አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት መሆኑን ዶ/ር አንተነህ ይናገራሉ።መንግስት እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ካሉ ለአገሪቱ እጅግ መሠረታዊ የሆነ የእርዳታና ብድር አገልግሎት ከሚሰጡ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያደረገ ያለው እሰጥ አገባና ግጭት ገሪቱን ከባድ ዋጋ ያስከፍላታል ብለዋል።“በተለይ እንደሆኑ አገሪቱ በተለያዩ ውስጣዊ ችግሮች እያታመሰች ባለችበት ወቅት የሚደረጉ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች መሻከር በቡሃ ላይ ቆረቆር እንደማለት ነው ያሉት ምሁሩ፤ ይህ ሁኔታ አገሪቱን  በዘላቂነት  ሊጎዳት ወደሚችል ችግር እየጎተቱ መክተት ነው ብለዋል።አለም አቀፍ የእርዳታ ሰጪ ተቋማት ወደ አገራችን የላኩትን የሰብአዊ እርዳታዎች ሰርቀን በመሸጥ የተሰጠን አሳፋሪ ስም ሳይቀየርና ከአጎዋ  ተጠቃሚነታችን ተሰርዘን ባለበት በዚህ ጊዜ በሌላ ችግር ውስጥ መግባቱ ለከፋ ችግር ይዳርገናል ያሉት ምሁሩ፤ እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ ያሉ አለማቀፍ የፋይናንስ ተቋማት በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከሚያሳድሩት ተጽእኖ አኳያ ትኩረት ሲሰጣቸውና በአግባቡ ሊያዙ ይገባል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪም አለማቀፍ የዲፕሎማሲያዊ መብቶችና ህጎችን ማክበር ግዴታችን ነው ብለዋል።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ውሰጥ 1.24 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ 22 ፕሮጀክቶችን እንደሚያከናውን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ላይ  ማስታወሱን የተናገሩት ዶ/ር አንተነህ፤ ይህ ገንዘብ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያለው አስተዋፅኦ እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል። ከዚህ አንጻር መንግስት ከአለማቀፍ ተቋማት ሊያስተካክል ይገባል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
በ1963 ዓ.ም ሱዳን ካርቱም ላይ በተካሄ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስብሰባ ላይ የተቋቋመው የአፍሪካ ልማት ባንክ፤ በ1967 የኢትዮጵያ ቅርንጫፉን ክፍቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፤ አገሪቱ ለምታከናውናቸው የመሰረተ ልማት ግብርና ሌሎች የልማት ስራዎች የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ላይ  የሚገኝ ተቋም ነው።

Read 1024 times