Wednesday, 13 December 2023 10:40

“የኛ ምርት” አውደ ርዕይና ባዛር በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያዘጋጀውና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አካል የሆነው “የኛ ምርት” የተሰኘ አውደ ርዕይና ባዛር በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ፡፡

አውደ ርዕዩና ባዛሩ “ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል፣ እስከ ታሕሳስ 7 ቀን 2016 ዓም ድረስ እንደሚቆይ  ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በመክፈቻው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አምራቹን ዘርፍ ለማነቃቃት የተለያዩ ንቅናቄዎች ተጀምረው ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል፤ የዚህ ንቅናቄ አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኤግዚቢሽንና ባዛር፣ አምራቾችን ከሸማቾች ጋር በማገናኘት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን በማስተዋወቅና የኑሮ ውድነቱን በማረጋጋት ሰፊ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው፤ አምራች ዘርፉን መደገፍ ኢትዮጵያ ለምታደርገዉ የብልጽግና ጉዞ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ አውደ ርዕይና ባዛር ላይ ከ85 በላይ የሀገር ዉስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች የተሳተፉ ሲሆን፤ ከ50 ሺ በላይ ሰዎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል ተብሏል፡፡

Read 1092 times