Tuesday, 28 November 2023 19:58

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል አገልግሎትን በጅግጅጋ ከተማ በይፋ ገበያ ላይ አዋለ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

ኢትዮ ቴሌኮም የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል
አገልግሎትን በጅግጅጋ ከተማ በይፋ ገበያ ላይ አዋለ


ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት፣ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባና አዳማ በይፋ ለአገልግሎት ያበቃውን የዘመናችንን የመጨረሻ የ5ኛ ትውልድ የሞባይል አገልግሎት፤ በምስራቅ ምስራቅ ሪጂን፣ በጅግጅጋ ከተማ በመዘርጋት በይፋ ገበያ ላይ ማዋሉን አስታውቋል፡፡


በዚህም መሰረት በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት አስተዳደር ቢሮ፣ ሆደሌይ (ቤተ-መንግስትና አየር መንገድ)፣ በሸህ አብዱሰላም ት/ቤት፣ በክልሉ ም/ቤት (ፓርላማ) አዳራሽ፣ በክልሉ ገቢዎች ቢሮ፣ በአሮጌው ታይዋንና በኢትዮ ቴሌኮም የምስራቅ ምስራቅ ሪጂን ጽ/ቤት አካባቢዎች አገልግሎቱን ማስጀመሩን ጠቁሞ፤ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ በጅግጅጋ ሸህ ሐሰን ያባሬ ሪፈራል ሆስፒታል፣ በአዲሱ ታይዋን፣ ቀበሌ 06 (አህመድ ጉሬይ ት/ቤት) እና ጀላባ አካባቢዎች ደግሞ በቅርቡ አገልግሎቱን እንደሚያስጀምር አስታውቋል፡፡


”የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት እስከ 10 ጊ.ባ በሰከንድ (Gbs) የሚደርስ ከፍተኛ ፍጥነት ያለው፣ ዳታ የማስተላለፍ መዘግየትን እጅግ በላቀ ሁኔታ በመቀነስ (Ultra-low latency) ወደ 1 ሚሊ ሰከንድ የሚያደርስ ሲሆን፤ በተጨማሪም በአንድ ካሬ ኪሎሜትር ውስጥ እስከ 1 ሚሊዮን የሚደርሱ በርካታ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን እርስ በርሳቸው ለማገናኘት የሚያስችል ዓለማችን የደረሰበት ዘመናዊ የገመድ አልባ ኔትወርክ ቴክኖሎጂ ነው፡፡“ ብሏል፤ኩባንያው በመግለጫው፡፡


ኩባንያው በማከልም፤ “5ጂ አገልግሎት በተለይም ወሳኝ ተልዕኮ ላላቸው (Mission Critical) እና በተመሳሳይ ወቅት (real time) መከናወን የሚፈልጉ አገልግሎቶችን ለአብነትም የማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ግብርና፣ ህክምና ለመሳሰሉ ኢንዱስትሪዎች እጅግ የላቀ ፋይዳ ያለው ሲሆን፤ እንደ ሹፌር-አልባ ተሽከርካሪዎች (self-driving vehicles) ፣ Internet of Things የመሳሰሉ ቴክኖሎጂዎች በተግባር እውን እንዲሆኑ የሚያስችል አስተማማኝ የዘመኑ ቴክኖሎጂ ነው፡፡” ሲል አብራርቷል፡፡

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

Read 1425 times