Saturday, 04 November 2023 00:00

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ከጸብ አጫሪነት ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሜሪካ አሳሰበች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

   በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የቀጠለው ግጭትም አሣስቦኛል ብላለች።ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጠብ ከሚያጭሩ ድርጊቶች በመቆጠብ የአካባቢውን አገራት ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ማክበር እንዳለባቸው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን ገለፁ ። ውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ አክለውም በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ሌሎች ክልሎች ያለው ግጭት አገራቸውን እንዳሳሰባት ገልጸው እየተፈጸሙ ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጥላቻዎች የሀገሪቱን እና አካባቢውን ወደ አለመረጋጋት የሚያስገባ ነውም ብለዋል፡፡

በአገሪቱ በተለያዩ ወገኖች የቀጠለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና ጥቃት፣ “የመርዛማ ንግግሮች” መስፋፋ በጦርነቱ ምክንያት የሳሳውን ማኅበራዊ ትስስር የበለጠ እየሸረሸረው ነው ያሉት ብሊንከን ለዚህም አስተማማኝ የሽግግር ፍትሕ፣ ሐቀኛ እና አካታች ብሔራዊ ምክክር በመላዋ አገሪቱ ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች የሚካሄዱትን ግጭቶች ለመፍታት ውይይት እንዲደረግ ጥሪ ቅርበዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እንዲሁ በደፈናው አገራቱ የሁሉንም የአካባቢውን አገራት ሉዓላዊነት በማክበር ከግጭት እንዲቆጠቡ መጠየቃቸው፣ የኤርትራ ኃይሎች በትግራይ ውስጥ መቆየት እና ከኢትዮጵያ በኩል የባሕር በር ጥያቄ መነሳቱን ሁለቱን ወገኖች ወደጦርነት ሊያስገባቸው ይችላል የሚል ስጋት አለ ።

ሰሜን ኢትዮጵያ ለሁለት ዓመት የነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲቆም ምክንያት የሆነው የሰላም ስምምነቱ አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ አሜሪካ በውጪ ጉዳይዋ በኩል ባወጣችው መግለጫ ስምምነቱ ጦርነቱ እንዲቆም ከማድረጉ በላይ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀድሞ ቤታቸው መመለስ መጀመራቸው እና ተቋርጠው የነበሩ አገልግሎቶች እንዲጀመሩ ማድረጉን ገልጻለች፡፡ህወሃት ከባድ መሳሪያዎችን መመለስ መጀመሩ፣ ጊዜያዊ አስተዳድር መዋቀሩ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች መቀጠላቸው፣ ተጎጂዎችን ለመካስ የሽግግር ፍትህ ስርዓት ለመዘርጋት ሂደት መጀመሩ በአንድ ዓመት ውስጥ የተፈጸሙ ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሆኑም በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል፡፡ይሁንና የኤርትራ ጦር ከኢትዮጵያ አሁንም ሙሉ ለሙሉ ከትግራይ ክልል አልወጡም ያለው የብሊንከን መግለጫ ሁለቱ ሀገራት አንዳቸው የአንዳቸውን ሉዓላዊነት እንዲያከብሩ፣ ከአላስፈላጊ ጸብ አጫሪነት ድርጊት እንዲታቀቡም አሳስቧል፡፡

በኢትዮጵያ እውነተኛ እና ተበዳዮችን ማዕከል ያደረገ የሽግግር ፍትህ ስርዓት እንዲሰፍንም ጠይቃለች ። እውነተኛ እና አሳታፊ ብሄራዊ ውይይት እንዲደረግ አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግም አስታውቃለች፡፡

Read 717 times