Saturday, 22 April 2023 19:11

ጠ/ሚኒስትሩ የሸኔ ሸማቂዎች በሰላም እንዲገቡ ጥሪ አቀረቡ

Written by  መታሠቢያ ካሣዬ
Rate this item
(4 votes)

ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳና ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ጋር ወደ ነቀምት የተጓዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ በክልሉ የተለያዩ ዞኖች እየተዘዋወሩ፣ በንጹሃን ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ የሚገኙትን የሸኔ ቡድን አባላት “ከዛሬ ጀምሮ በሰላም መግባት ትችላላችሁ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሸማቂ ቡድኑ አባላት በሰላም ገብተው ሃሳባቸውን ለህዝብ መግለጽ እንደሚችሉና ሰላማዊ ኑሮአቸውን መቀጠል እንደሚችሉም አስገንዝበዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከትናንት በስቲያ በክልሉ ነቀምት ከተማ ውስጥ ከአራቱም የወለጋ ዞኖች ማለትም ከምስራት ወለጋ ዞን ነቀምት፣ ከምእራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ፣ ከሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ሻምቡና፣ ከቄሌሞ ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተሞች ከተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡በዚሁ ውይይት ላይ ጠ/ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፤ ከሸኔ ቡድን አባላት ጋር ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ፈትቶ ፊትን ወደ ልማት ማዞር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተወያዩት የማህበረሰቡ ተወካዮች፣ የምእራብ ወለጋ ችግር የሰሜኑ የአገሪቱ ችግር በተፈታበት መንገድ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ ሰሞኑን በምክር ቤቱ ቀርበው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ከፈረጀው የሸኔ ቡድን ጋር ያሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልፀው የነበረ ሲሆን የሸኔ ቡድን በበኩሉ እስከሁን የተጀመረ የሰላም እንቅስቃሴ የለም ማለቱ ይታወሳል፡፡

Read 2108 times