Saturday, 22 May 2021 11:57

በትግራይ ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል ተባለ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

             በትግራይ ያለው ግጭት የከፋ ረሃብ እያስተከተለ መሆኑን የተናገሩት የዩኤስአይድ ዋና ዳይሬክተር፤ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡
የቀድሞ በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ አምባሳደር የአሁኑ የአሜሪካ እርዳታ ድርጅት (USAID) ዳይሬክተር ሳማንታ ፓወር እንዳመለከቱት፣ ተቋማቸው በሰራው የአደጋ ጊዜ ትንተና መሰረት ተጎጂዎች ወደ ረሃብ የተጠጋ ችግርን እየተጋፈጡ መሆኑን መገንዘቡን አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በከፋ የረሃብ አደጋ ውስጥ የሚገኙትን ጨምሮ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ይፈልጋሉ፡፡ ለእነዚህ ዜጎች እርዳታውን ለማቅረብም ሁኔታዎች አመቺ አለመሆናቸውን የዳሬክተሯ መግለጫ  አመልክቷል፡፡
ዜጎች ከከፋ የረሃብ አደጋው ለመከላከል መንግስት ሃላፊነት ተሰምቶት በአካባቢው ያለው ግጭት በሚቆምበት ሁኔታ ላይ እንዲሰራ ዳሬክተሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተለይ ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች ያለው የዜጎች ስቃይ የከፋ መሆኑን ዳሬክተሯ አስገንዝበው፣ መንግስት አወንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  

Read 11353 times