Monday, 05 December 2016 08:45

4ኛው “አዲስ አግሮ ፉድ ኤግዚቢሽን” ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 እስከ ሰኞ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል
                                  
     ኢቲኤል አድቨርታይዚንግና ኮሚዩኒኬሽን ከላዲን ፌይር ኤንድ ኮንግረስ ኦርጋናይዘር ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 4ኛው ዙር “አዲስ አግሮ ፉድ ኤግዚቢሽን” ትላንት በኤግዚቢሽን ማዕከል የተከፈተ ሲሆን እስከ ሰኞ ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የግብርና ውጤቶች፣ ማሽነሪዎች፣ ምግቦች፣ የምግብ ቴክኖሎጂዎችና ማሸጊያዎች እንዲሁም  ከግብርና እና ከምግብ ጋር የተያያዙ ሌሎች እቃዎችና ቴክኖሎጂዎች ለእይታ ይቀርባሉ ተብሏል፡፡
 የኢቲኤል አድቨርታይዚንግ ባለቤትና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ወይዘሪት ሀይማኖት ተስፋዬ ሰሞኑን በካሌብ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በኤግዚቢሽኑ ላይ ከ60 በላይ የተለያዩ አገራት ነጋዴዎች የሚሳተፉ ሲሆን ከነዚህም መካከል የቱርክ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ቱኒዚያ፣ ኬንያ፣ ስዊድን፣ ፊንላንድና ሌሎችም ይገኙበታል ብለዋል። ከአገራችንም በዘርፉ የተሰማሩ 10 ያህል ድርጅቶች የሚሳተፉ ሲሆን የሀገራችን ነጋዴዎች ከሌላው ዓለም ነጋዴዎች ጋር የልምድ ልውውጥና የቴክኖሎጂ ሽግግር መድረኮችን የሚፈጥሩበት አጋጣሚ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡ አገራችን እንዲህ አይነት ኤግዚቢሽኖችን ባዘጋጀች ቁጥር የውጭ ምንዛሬ ከማግኘታችንም በላይ በሆቴልና መስተንግዶ የተሰማሩ ድርጅቶችም ተጠቃሚ ይሆናሉ ያሉት ወይዘሪት ሀይማኖት፤ በአጠቃላይ በአገር ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ውጤት እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ ከኢቲኤል ጋር ኤግዚቢሽኑን ያዘጋጀው ላዲን የንግድ ትርኢትና ጉባኤ አደራጅ፣ በዓለም ከ52 አገራት በላይ በመዘዋወር የግብርና፣ የኮንስትራክሽንና ተዛማጅ ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት ይታወቃል፡፡

Read 766 times