Sunday, 20 November 2016 00:00

የ‹‹ኢትዮ-ምህዳር›› ጋዜጣ ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

 የ‹‹ኢትዮ ምህዳር›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጌታቸው ወርቁ፣ የ1 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት መውረዱን ተከትሎ፣ የጋዜጣው ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል የተባለ ሲሆን ጠበቃው በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡
ዋና አዘጋጁ በሳምንታዊው ‹‹ኢትዮ - ምህዳር›› ጋዜጣ፣ በግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም እትሙ፤ ‹‹በፓትርያርኩ መቀመጫ በቅድስት ማርያም ገዳም፣ ምርመራ እንዲካሄድ ተጠየቀ” በሚል ርዕስ በሰራው ዘገባ፣ የገዳሙን ስም አጥፍቷል በሚል በቀረበበት ክስ፣ የ1 ዓመት እስራትና  የ1500 ብር መቀጮ የተወሰነበት ሲሆን  የጋዜጣው አሳታሚ ድርጅት 10 ሺህ ብር እንዲቀጣ ተፈርዷል፡፡
የዋና አዘጋጁን መታሰር ተከትሎ የጋዜጣዋ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን  የጠቆሙት የሙያ ባልደረቦቹ፤ የጋዜጣው ህትመት እንዲቀጥል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡
ጋዜጠኛ ጌታቸው ወርቁ፤ የቅጣት ውሳኔው ከተላለፈበት በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ፤ “ይህ የተደረገው ጋዜጣዋን ለማፈን ነው” ሲል ደጋግሞ ተናግሯል፡፡
የጋዜጠኛው ጠበቃ አቶ በኃይሉ ተስፋዬ፤ የፍርዱን ግልባጭ ከመዝገብ ቤት እንዳገኙ በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቁ አስታውቀዋል፡፡

Read 1070 times