Saturday, 10 January 2015 09:42

መሠረት የበጎ አድራጐት ድርጅት ለ480 ቤተሰቦች የገና ስጦታ አበረከተ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

መሠረት የበጎ አድራጐት ድርጅት 480 ችግረኛ ቤተሰቦች የገና በዓልን በደስታ እንዲያከብሩ  የዶሮና የእንቁላል ስጦታ ማበርከቱን ገለፀ፡፡
ለእያንዳንዱ ቤተሰብ አንድ ዶሮና ስድስት እንቁላል፣ በአጠቃላይ 480 ዶሮዎችንና 2880 እንቁላሎች የተበረከተ ሲሆን 64ሺ ብር እንደፈጀም ታውቋል፡፡
ለችግረኛ ቤተሰቦች የተበረከተው ስጦታ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ከ5 ብር ጀምሮ ባደረጉት መዋጮ እንደሆነ መሰረት በጎ አድራጎት አስታውቋል፡፡
ይሄ ድጋፍ የተደረገበትን ዓላማ ያስረዱት የበጎ አድራጎቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሰረት አዛገ፤ “የባህል እሴቶቻችን ተጠብቀው ሁሉም ቤተሰብ ከልጆቹና ከጐረቤቱ ጋር ባህሉን በደስታ እንዲያከብርና ማንም ሰው ደሀ በመሆኑ ምክንያት በአሉን በችግር እንዳያሳልፍ ለማድረግ ነው” ብለዋል፡፡ መስራቿ፤ ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ለረዷቸው የተለያዩ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ለበጐ ፈቃድ አገልጋዮች፣ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
መሠረት የበጐ አድራጐት ድርጅት፤ በድህነት ለሚኖሩ ሴቶችና ህፃናት የተለያዩ ድጋፎችና ዕድሎች በመስጠት በማብቃት የሚተጋ የበጐ አድራጐት ድርጅት ነው፡፡  

Read 1186 times