Administrator

Administrator

ሉላ ገዙ፣ የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆነች

 የኢቢኤስ ፕሮግራም አቅራቢዋና የማስታወቂያ ባለሙያዋ ሉላ ገዙ፤ የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆና ተመረጠች፡፡

ሉላ ገዙ፤ ለቀጣዮቹ  4 ዓመታት የሮያል ፎምና ፈርኒቸር ብራንድ አምባሳደር ሆና ለመሥራት በዛሬው ዕለት ከሮያል ግሩፕ አመራሮች ጋር   በይፋ  ተፈራርማለች።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተኩስ አቁሙ ትክክለኛ እና በቀጣናው የሚፈለገውን መሻሻል ለማምጣት ሚናው ከፍተኛ ነው ሲሉ አወድሰዋል፡፡

የተሰኩስ አቁሙ በዋናነት በሥፍራው የሚገኙ ንጹሃን ዜጎችን ከአካባቢው እንዲሸሱ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈም በቦታው ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊውን የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረሰ እንደሚያስችል ተመላክቷል፡፡

የእስራኤል ጦር ከዚህ በፊት በጋዛ ለሚኖሩ ንጹሃን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ “ታክቲካል የተኩስ አቁም” እንደሚያደርግ ማስታወቁን ቢቢሲ በዘገባው አስታውሷል፡፡


የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ጎበኙ።
መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች በጉባ ጉብኝታቸው፤ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል።
ውሃው ተርባይኑን መትቶ ወደ ተፈጥሮአዊ ፍሰቱ የሚመለስና በአባይ ወንዝ ተፋሰስ ሀገራት የሚያመጣው ችግር እንደሌለ መመልከታቸውንም ወታደራዊ አታሼዎቹ በአስተያየታቸው ገልጸዋል።
ከዘጠና ሰባት መቶኛ በላይ የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ ባለፈ በከፍተኛ የሀይል እጥረት የምትታወቀውን አፍሪካ ልማት የሚያፋጥንና ለቀጠናዊም ሆነ አህጉራዊ የኢኮኖሚ ትስስር የራሱን በጎ ሚና የሚጫወት አቅም እንደሆነም ነው በጉብኝቱ የተገለጸው።
ኢትዮጵያ ገና በጥቅም ላይ ያልዋሉ እምቅ የተፈጥሮ ሃብት እንዳላት የተናገሩት አስተያየት ሰጪ ወታደራዊ አታሼዎቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆና ግዙፉን የህዳሴ ግድብ እውን ማድረግ መቻሏ ሙሉ ለሙሉ የተሟላ ሰላም ካሰፈነች በፍጥነት ማደግ የምትችል ስለመሆኗም ነው የተናገሩት።
ጉብኝቱን ያመቻቸው የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ሲሆን ወደ ስልሳ የሚጠጉ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ግድቡን ጉብኝተዋል።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

በቢኒያም አቡራ የተዘጋጀውና "ወደ ፍቅር ጉዞ" የተሰኘው፣ የአንጋፋውን ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን የዘፈን ግጥሞች የሚዳስሰው መጽሐፍ ዛሬ ከ11፡30 ጀምሮ በወመዘክር አዳራሽ እንደሚመረቅ ደራሲው ለአዲስ አድማስ አስታውቋል፡፡

መጽሐፉ በስድስት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ206 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን፤ በ320 ብር  ለገበያ ቀርቧል ተብሏል።

ቢኒያም አቡራ፤ ከዚህ ቀደም የተወዳጇን ድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው የዘፈን  ግጥሞች የሚዳስስ “ባለቅኔዋ ሶሪት” የተሰኘ  መጽሐፍ ማሳተሙ  አይዘነጋም።     

 የቴሌግራም ቻናልችንን  በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas                                  

የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር እና የዩኔስኮ ብሄራዊ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኔስኮ አጠቃላይ ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ከአለም አቀፍ የትምህርት ቢሮ (UNESCO-IBE) ቦርድ ፕሬዝዳንት ስቪን ኦስትቬት ጋር በፈረንሳይ በሚገኘው የዩኔስኮ ዋና መስሪያቤት የጎንዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይታቸውም ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን የትምህርት ሥርዓት ለማሻሻል እና ለማዘመን ያከናወናቸውንና በመተግበር ላይ ያሉ የለውጥ ተግባራትን አቅርበዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ኢትዮጵያ በተለይም በዘርፉ በተለዩ የትምህርት መስኮች ላይ የውጭ ልምድ እንደሚያስፈልጋት በአጽናኦት የተናገሩ ሲሆን የዩኔስኮ-አይቢኢ የቦርድ ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው የትምህርት ስርዓቱን በአዲስ መልክ ለማሻሻልና ለማዘመን ሚኒስቴሩ የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀው ቢሮው ጥረታቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።
H.E. Professor Berhanu Nega discusses with the President of the UNESCO-IBE Board, Svein Osttveit
_______________________
H.E. Professor Berhanu Nega, the Minister of Education of the Federal Democratic Republic of Ethiopia and the President of the National Commission for UNESCO discusses at a sideline meeting with the President of the International Bureau of Education (UNESCO-IBE) Board, Svein Osttveit at the UNESCO headquarters office in Paris, France.
During the conference, Professor Berhanu Nega presented the steps the Ethiopian Ministry of Education has done to improve the curriculum and reform the educational system.
H.E. the Minister emphasized that the country needs foreign experience in the fields under consideration. President Svein Osttveit, for his part commended the Ministry's dedication to restructuring the educational system and stated that the Bureau is prepared to support the Ministry in its efforts to update the curriculum and enhance the educational system.
 ዋና ዋና የጥቁር አዝሙድ የጤና ጥቅሞች
 
1️⃣ ለካንሰር በሽታ
የክሮሺያ ሳይንቲስቶች በጥቁር አዝሙድ ዘይት ውስጥ ስለሚገኙ ሁለት ፋይቶ ኬሚካሎች እንዴት ካንሰርን እንደሚከላከሉ ጥናት አድርገው ነበር።
በጥናታቸውም መሠረት እነዚህ በጥቁር አዝሙድ ዘይት ውስጥ የሚገኙ ሁለት ኬሚካሎች (ታይሞኪውኖን እና ታይሞሃይድሮኪውኖን) ካንሰርን የሚያስከትሉ ቲውመር ሴሎችን በ 52% (በሃምሳ ሁለት ፐርሰንት) መከላከል እንደሚችሉ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡
በሁለቱ ኬሚካሎች መበልፀጉ ጥቁር አዝሙድን የተለየ ያደርገዋል ይህም ካንሰርን በተለያዩ መንገዶች ለመከላከል እና ለማከም ይረዳል፡፡
2️⃣ ለጉበት ጤንነት
ጉበት ለሰውነታችን በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የሰውነት ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡
ወደ ሰውነታችን የገባ ማንኛውም መርዛማ ነገር በጉበት አማካይነት ይረክሳል፤ ከጉበት የሚገኘው የሃሞት ፈሳሽ፤ ስብን ወይም ፋትን በመፍጨት እንዲሁም አእምሮና ሰውነታችን ደስተኛና ጤናማ በማድረግ ቁልፍ የሆነ ሚና በመጫወት ይጠቅመናል፡፡
በመድሃኒቶች ምክንያት የሚከሰት የጎንዮሽ ጉዳት፣ በአልኮል መጠጦችና በተለያዩ በሽታዎች ጉበታቸው ለተጎዳ ወይም ስራውን ለቀነሰባቸው ሰዎች፤ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጉበት ለማገገም ወይም ለመዳን የሚያደርገውን ሂደት በሚገርም ሁኔታ ያፋጥናል፡፡
3️⃣ ለስኳር በሽተኞች!
በህንድ የህክምና ቡድን ተጠንቶ ለህትመት የበቃው ጥናት እንደሚሳየው የጥቁር አዝሙድ ዘይት የጣፊያ ቤታ ሴሎች በፍጥነት እንዲያገግሙ ያደርጋል።
በደም ውስጥ በዝቅተኛ መጠን የሚገኘውን የኢንሱሊን መጠን እንዲጨምር እና በደም ውስጥ ጨምሮ የሚገኝውን የስኳር መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
እንደሚታወቀው ኒጌላ ሳቲቫ (Nigella Sativa) በተክሎች ላይ ከሚገኙ ጥቂት ንጥረ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን ዓይነት 1 እና ዓይነት 2 የስኳር በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳናል፡፡
4️⃣ የሰውነት ክብደት ለመቀነስ!
ፀረ-ውፍረት ባህሪ ያላቸው ተክሎች የትኞቹ እንደሆኑ ለመለየት የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው የጥቁር አዝሙድ ዘይት ውጤታማ ተፈጥሮአዊ የውፍረት መከላከያ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
የጥቁር አዝሙድ ዘይት የሰውነት ክብደትን ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን በመግታት ወይም በማስተካከል ይረዳናል። ከእነዚህም መካከል:-
???? የምግብ ፍላጎት
???? ግሉኮስን በአንጀታችን ውስጥ መምጠጥ
???? የደም ስኳር መጠን
???? ኮሌስትሮል እና
???? ትራይግላይሴራይድስ ናቸው።
5️⃣ ለፀጉር መሳሳት!
ከብዙዎቹ ልዩ የሆኑ የጥቁር አዝሙድ ጥቅሞች ውስጥ አንዱ የፀጉር መሳሳትን ወይም መመለጥን መከላከሉና በፍጥነት እንዲያገገም ማድረጉ ነው፡፡
ይህ እንዴት እንደሆነ የሚታወቅ ባይሆንም ለመገመት ግን በጣም ቀላል ነው።
ይህም ጥቁር አዝሙድ ከፍተኛ የሆነ ፀረ-ኦክሲዳንት እና ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው ነው፡፡
6️⃣ ሜላኒን እንዳይጎዳ ይከላከላል!
ሜላኒን የቆዳ ቀለም ሲሆን ቆዳችን ጉዳት እንዳይደርስበት በመከላከል ይጠቅመናል፡፡
ለአይናችን፣ ለቆዳችን እንዲሁም የራሳችን ቀለም እንዲኖረን በማድረግ ከፍተኛ የሆነ ሚናን የሚወጣ ኬሚካል ነው፡፡
ከሜላኒን ጋር የተያያዙ የቆዳ በሽታዎች እንዲያገግሙ ይረዳናል፡፡
7️⃣ ኢንፌክሽንን ለመከላከል!
ኢንፌክሽን አለም አቀፍ ስርጭት ያለውንና ሜቲሲሊን ረዚስታንት ወይም በሜቲሲሊን መድሃኒት የማይሞተው ስታፋሎኮከስ አውረስ (Staphylococcus aureus) የተባለውን ባክቴሪያ፤ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በመግደልና በማጥፋት ይጠቅመናል፡፡
ጽሑፉን ከወደዱት (Like) በማድረግ ለሌሎችም (share) ያድርጉት፡፡ ቸር እንሰንብት
 
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ23ተኛው ዙር ውድድር ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ከፍተኛ የሆነውን የአትሌት አሸናፊዎች ሽልማት ሊሸልም ነው፡፡
ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፡- የ2016 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. በሁለቱም ፆታ ላሉ አትሌቶች የ812,000 ብር ሽልማት ሊሸልም ነው፡፡ ካለፈው አመት በአጠቃላይ ከ30 በመቶ በላይ ብልጫ ያለውም ሽልማት ነው ተብሏል፡፡
በ ውድድሩ ላይ የወንድ እና የሴት አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 200,000 ብር 100,000 እንዲሁም 50,000 ብር 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ለሚወጡ በቅደም ተከተል የሚሸለሙ ይሆናል። ያለፈው ዓመት ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት መጠን 150,000 እንደነበር ይታወቃል፡፡
ውድድሩን በቅርብ ጊዜ ካሸነፉ ወንድ አሸናፊዎች መካከል ሰለሞን ባረጋ (2010) ሀጎስ ገብረህይወት (2011)፣ በሪሁ አረጋዊ (2012) እና አቤ ጋሻው ሶስት ጊዜ በማሸነፍ ብቸኛ ወንድ አትሌት ሲሆን በሴቶች በኩል ያለምዘርፍ የኋላው ባለፉት ዓመታት (2012 እና 2014) ውድድሩን ሁለት ጊዜ ስታሸንፍ ሌሎች አሸናፊዎች ዘይነባ ይመር (2010)፣ ፎይት ተስፋዬ (2011) እና ጽጌ ገብረሰላማ (2013) ይገኙበታል።
የዘንድሮው ውድድር በግሎባል ስፖርት ኮሙኒኬሽን ስር ያሉ ሶስት ወጣት ዩጋንዳውያን አትሌቶችን ጨምሮ ጠንካራ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።
ጁሪ ቫን ደር ቬልደን ይህንን ውድድር “ለአትሌቶቻችን ጠቃሚ የመማሪያ ቦታ እና ማበረታቻም እንደሆነ እናምናለን” በማለት ገልፀውታል።
በዘንድሮው ውድድር የሚወዳደሩ ታዋቂ አትሌቶች ስም ዝርዝር ማክሰኞ ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ይሆናል።
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. (1994-2016) ስለነበሩት ምርጥ ውድድሮች፡-
• በ1994 የመጀመርያው የሩጫ አሸናፊዎች ኃይሌ ገብረስላሴ እና ብርሃነ አደሬ ነበሩ። ባለፈው አመት የ22ኛ ዙር አሸናፊዎች አቤ ጋሻው እና ትግስት ከተማ ነበሩ።
• ሁለት አትሌቶች ገነት ጌታነህ (በ1997 እና 1998) እና ውዴ አያሌው (በ2000 እና 2001 ዓ.ም.) ብቻ የውድድር ዘመናቸውን በተሳካ ሁኔታ አስጠብቀዋል።
• ሁሉም የዚህ ውድድር አሸናፊዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሆነዋል። የኬንያ አትሌቶች በወንዶች ውድድር አንድ ጊዜ በሴቶች ደግሞ ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል።
• ዉዴ አያሌዉ እና አቤ ጋሻው በውድድሩ ሶስት ጊዜ ያሸነፉ አትሌቶች ናቸው፡፡ ዉዴ በ2000፣ 2001 እና 2007 እና አቤ በ2009፣ 2013 እና 2015 ብቻ ናቸው።
• በወንዶች ፈጣን የማሸነፍ ጊዜ በ1999 (28፡18) በደሪባ መርጋ እና በሴቶች ያለምዘርፍ በ2014 (31፡17)
የ2016 የሶፊ ማልት ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ 10 ኪሎ ሜትር እሁድ ህዳር 19 ቀን 2023 ይካሄዳል። 45,000 ሯጮች ለውድድሩ ተመዝግበዋል።
ውድድሩ በ EBC የቀጥታ ስርጭት በ8፡18 ሰአት (ወንዶች) እና 8፡23 ሰአት (ሴቶች) በሃገር ውስጥ ሰአት አቆጣጠር (GMT + 3) እየተካሄደ ነው።
Tuesday, 03 October 2023 00:00

የአጥንት መሳሳት

አጥንት ከሰዉነት ክፍል ጠንካራዉ አካል ነዉ። እንደ ጥንካሬዉ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ለጉዳት በሚዳረግበት አጋጣሚ ወደቀድሞ ይዞታዉ ለመመለስ ቀላል አይሆንም። አጥንት ከአካል እድገትና ከእድሜ መጨመር ጋ እያደር እያደገና እየጠነረ ሄዶ በጉርምስና እድሜ ማብቂያ ላይ እድገቱን ያቆማል።

አጥንት ጠንካራ የሰዉነት አካል መሆኑ ቢታወቅም በተለያዩ ምክንያቶች አቅም የሚያጣበትና ለስብራትም ሆነ ለመሰንጠቅ የሚጋለጥበት ሁኔታ አለ። የጥንካሬዉን ያህል ታዲያ እክል ሲገጥመዉ በቀላሉ ላይጠገንም ይችላል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለዉ ከወንዶች ይልቅ የሴቶች የአጥንት ጥንካሬ ከእድሜ አኳያ እየቀነሰ ይሄዳል። ጥንካሬዉ የቀነሰ አጥንት ደግሞ ለመሰበርም ሆነ ለመሰንጠቅ አደጋዎች እጅግ የተጋለጠ ነዉ። እንደድርጅቱ የሚያጋጥመዉ የአጥንት መሰንጠቅ አደጋ ከእድሜ አኳያ ይበረታል፤ ከ50 ዓመት በላይ ከሆኑ ሴቶች 40 በመቶዉ ለዚህ ችግር ይዳረጋሉ።

እግር ወይም እጅ የመሠበር አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፤ በእርግጥ ይህ በተገቢዉ ህክምና ሊጠገንና ወደቦታዉ እንዲመለስ ሊደረግ ይችላል። እንዲህ ያለዉ ችግር የሚወሳሰበዉ ግን አንድም አጥንቱ ሲሳሳ አለያም አቅም አጥቶ ለመሰንጠቅ ሲዳረግ ነዉ። ይህ ችግር በአብዛኛዉ በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚታይ ሲሆን በተለይ ሰዎቹ እንደልብ የማይንቀሳቀሱ ከሆነ ሌላ ተጨማሪ የጤና እክልም ሊያስከትል ይችላል። እንደሃኪሞች ግምትም ከ50 ዓመት በላይ ከሆናቸዉ ሴቶች ከሶስት አንዷ ወይም ከዚያ በላይ የወር አበባ ዑደት ከቆመ በኋላ በሚከሰት የሆርሞን ለዉጥ የአጥንት መሳሳት ወይም የመሰንጠቅ ችግር ይገጥማቸዋል። እንዲህ ዓይነቱን ችግር ለመከላከል ይላሉ እዚህ ጀርመን ባድ ኖየንሃር የሚገኘዉ የአጥንት ህክምና ኪሊኒክ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቶማስ ካዉሽ፤ ከተቀመጡበት ሲነሱ በጥንቃቄ መቆም ተገቢ ነዉ፤

«ብዙም የማይንቀሳቀሱ ከሆነ እና ተስተካክሎ የመቆም እርግጠኝነት ከሌለ በመዉደቅ የሚመጣዉ መዘዝ ከፍተኛ ነዉ። እንዲህ ባለ ሁኔታ ላለ ሰዉ መንቀሳቀስ እጅግ ወሳኝ ነዉ። አጥንቱ በእንቅስቃሴዉ ሊነቃቃ እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል፤ ይህም የተዳቀቀዉ አጥንት እንዲጠናከር የማድረግ አስተዋፅኦ አለዉ።»

የአጥንት መሳሳት ወይም አቅም ማጣት የሚያጋጥማቸዉ ሰዎች ለረዥም ጊዜ ምንም ዓይነት የጤና እክል እንዳለባቸዉ ሊያዉቁት አይችሉም። ለአስር ወይም አስራ አምስት ዓመታት ያለምንም እንከን ሊንቀሳቀሱበት ይችላሉ። የከፋ ችግር መኖሩን የሚረዱት ልክ እንደወ/ሮ ሬጊና ብሩወር ባልታሰበ ሁኔታ ስብራት ሲያጋጥማቸዉ ይሆናል።

«ከሥራ እረፍት በነበርኩበት ወቅት ነዉ፤ ምግብ ቤት ዉስጥ የወለሉ ንጣፍ አንሸራቶኝ ወደቅኩ። ታፋዬ ላይና ትከሻዬ ላይ ተሰበርኩ። ዶክተሮቹ የትከሻሽ ስብራት ቀጥተኛ በመሆኑ ተጋጥሞ የመዳን ተስፋ አለዉ አሉኝ። እናም አጥንቱን ስበዉ አያያዙት እንጂ የተፈረካከሰ እንጨት መስሎ ነበር።»

ከዚያም የ69ዓመቷ ወይዘሮ ባድ ኖየንሃር በሚገኘዉ የማገገሚያ ክሊኒክ ለሶስት ሳምንታት እንዲቆዩ ተደረገ። እዚያም በየሠዓቱ በተዘጋጀላቸዉ መርሃግብር መሠረት በየቀኑ የስነልቦና ምክር አገልግሎትን ጨምሮ የሰዉነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ከረሙ። በቆይታቸዉም ታማሚዋ አንድ ሰዉ ለመዉደቅ አደጋ ሲጋለጥ እንዴት መዉደቅ እንደሚኖርበት ስልት እንዲያጠኑ ተደርጓል። መዉደቅ ድንገተኛ በመሆኑ አንድ ሰዉ አወዳደቅን እንዴት ሊያስተካክል ይችላል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፤ የስነልቡናዉ የምክር አገልግሎት ሚናዉ ይሄ ነዉ። አጥንት ጥንካሬ ከሌለዉ የሚገጥመዉ አደጋ የተለያዩ መዘዞችን ማስከተሉ ግድ ነዉ። ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም በመዉደቅም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከሚደርሱ ስብራቶች በተለይ አንገት ላይ የሚያጋጥም ስብራት ለህልፈተ ህይወት ሊዳርግ ይችላል። ዶክተር ቶማስ ካዉሽ ምክንያቱን ያስረዳሉ፤

«ይህ ከመንቀሳቀስ ጋ የተገናኘ ነዉ፤ በተወሰነ እድሜ አንድ ሰዉ ረዥም ሰዓታት አልጋ ላይ የሚተኛ ከሆነ እና የማይንቀሳቀስ ከሆነ በቀላሉ ለተለያዩና ተያያዥ በሽታዎች ይጋለጣል። ማለትም የደም መርጋት፤ የሳንባ መታፈን፤ የልብ ምትና የደም ዝዉዉር ችግር የመሳሰሉት ሁሉ ያጋጥማሉ። እናም እነዚህ ተባብረዉ ህመምተኛዉን ለህልፈት ይዳርጋሉ።»

የአጥንትን ጥንካሬ ማጣት በዘመኑ ህክምና ቀድሞ ሊደረሰብበት እንደሚችል ነዉ የሚታመነዉ። የዘርፉ ሃኪሞች በኤክስሬይ ወይም ራጅ በማንሳት የአጥንቱን ክብደትና ጥንካሬ መመዘን ይችላሉ። ዶክተር ካዉሽ የሚያገለግሉበት የባድ ኖየንሃር ክሊኒክ በየዓመቱ ወደስምንት መቶ የሚደርሱ ይህን መሰል ምዘናዎችን ያካሂዳል። ሃኪሞቹ በሚያደርጉት በዚህ ምርመራ በተመረጠዉ የሰዉነት አጥንት አካባቢ ምን ያህል የካልሲየም መጠን እንዳለ ማወቅ ይችላሉ። በተለይ በዳሌ አካባቢ በሚገኘዉ አጥንት ላይ ነዉ ይህ ምርመራ በብዛት የሚደረገዉ። ይህ የሆነበት ምክንያትም ከሌላዉ አካባቢ ይልቅ በዚህ ስፍራ የሚገኘዉ አጥንት በቀላሉ ሊሰበር ስለሚችል ነዉ። እናም በምርመራዉ በተባለዉ አካባቢ ዝቅተኛ የካልሲየም መጠን የሚኖር ከሆነ አጥንቱ ጥንካሬ የጎደዉ መሆኑ አያጠራጥርም፤ ያም ዉሎ አድሮ በቀላሉ ለጉዳት ይዳረጋል። አንዳንድ መድሃኒቶች አጥንት የመጉዳት ባህሪ አላቸዉ ይላሉ ዶክተር ቶማስ ካዉሽ፤

«ለምሳሌ ሄፓሪን ያለባቸዉ፤ ለሚጥል በሽታ የሚወሰዱ መድሃኒቶች፤ ለሆድ ህመም እና ለጨጓራ የሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች፤ ለረዥም ጊዜ የሚወሰዱ ከሆነ በጊዜ ሂደት ይህን ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህ ማለት ግን ለምሳሌ በሳምንት ሁለቴ በመዉሰድ ማለት አይደለም። ነገር ግን አንድ ሰዉ እንዲህ ያሉ መድሃኒቶችን በተከታታይ ለሁለትና ከዚያ በላይ ዓመታት የሚወስድ ከሆነ ይህ የጎንዮሽ ችግር አይቀሬ ነዉ።»

ከዚህም ሌላ ኮርቲዞን የተሰኘዉም የአጥንትን ጥንካሬ እንደሚጎዳ ነዉ ያመለከቱት። ይህ በተለይ የሪህ ህመምተኞችን ይመለከታል፤ ኮርቲዞንን ለመዉሰድ ይገደዳሉናል። ለካንሰር ህክምና የሚደረገዉ ኬሞቴራፒም እንዲሁ ለዚህ ሊያጋልጥ እንደሚችል ይታመናል። ወ/ሮ ሬጊና ብራወር የዛሬ 11 ዓመት የሆድ ካንሰር አጋጥሟቸዉ እጢዉ በቀዶ ጥገና ወጥቶላቸዋል። ከቀዶ ጥገናዉ በኋላ ኬሞቴራፒዉ ቀጠለ። ይህም የተገመተዉን የአጥንት መዳከም አስከተለ። በማገገሚያዉ ክሊኒክ ዕለት በዕለት ከሚሠሩት የሰዉነት እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የአመጋገባቸዉ ሁኔታም ከፍተኛ ክትትል ይደረግበታል፤ ከየዕለቱ ምግባቸዉ ዉስጥ በቂ ካልሲየም የሚያገኙባቸዉ የሚበረክቱ ሲሆን ቫይታሚን ዲም ይወስዳሉ። ዶክተር ካዉሽ ቫይታሚን ዲ ለአጥንት ስለሚሰጠዉ ጥቅም እንዲህ ይላሉ፤

«ቫይታሚን ዲ በአጥንት አወቃቀር እና በካልሲየም ክምችቱ ላይ ቀጥተኛ የሆነ ተፅዕኖ ያደርጋል፤ ያለ ቫይታሚን ዲ ይህ ነዉ የሚባል የአጥንት ገጽታ አይኖርም።»

እድሜን ተከትሎ የአጥንት መሳሳት ችግር በብዛት ሴቶችን ያጋጥማል ቢባልም ወንዶችም ለችግሩ የሚጋለጡበት ሁኔታ መኖሩ ግልፅ ነዉ። በነገራችን ላይ በዳሌ አጥንት ላይ የሚደርስ መሰንጠቅ ከባድና አብዛኛዉን ጊዜ ሃኪም ቤት ተኝቶ ለመታከም ግድ የሚል፤ ሲከፋም ለአካል ጉዳት የሚዳርግ እንደሆነ ነዉ የዓለም የጤና ድርጅት የሚያመለክተዉ። በጎርጎሪዮሳዊዉ 1990ዓ,ም 1,7 ሚሊዮን ሰዎች በዓለም ዙሪያ የዳሌ አጥንት መሰንጠቅ እንዳጋጠማቸዉ ተመዝግቧል። የዓለም የጤና ድርጅት እንደሚለዉም በመጪዉ 2050ዓ,ም ከህዝብ ብዛትና የአኗኗር ሁኔታ አኳያ ቁጥሩ ከፍ ብሎ 6 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል።

Wednesday, 01 November 2023 00:00

በየቀኑ አጥንትዎን ይገንቡ

በየቀኑ አጥንትዎን ይገንቡ

በቀን ውስጥ የሚያስፈልገንን የካልሲየም መጠን ከወተትና እርጎ እንዲሁም ሰፕሊመንት እንክብሎች በመዋጥ ለማግኝት ይሞክሩ።

አጥንትዎ ጠንካራ ሆኖ እንዲቆይ ያደርጋል። ማስታወስ ያለብን ነገር ከሰላሳ (30) ዓመት በኋላ የአጥንት እፍግታ (Density) እየቀነሰ ይሄዳል።

ስለዚህ ቢያነስ በየቀኑ 200 ሚሊ ግራም ካልሲየም ያስፈልግዎታል። ይህን ከማግኒዚየም ጋር በማቀናጀት መውሰድ ተገቢ ነው።

የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas

*በሶማሊያ ክልል፣ ጎርፍ ብዙ ሺዎችን አፈናቅሏል፤3ሺ የቁም እንስሳትን ገድሏል

የኢትዮጵያ አርታኢያን ማህበር፣ ሳምንታዊ የቁርስ ላይ ስብሰባውን ዛሬ ጠዋት በሂልተን ሆቴል ያካሄደ ሲሆን፤ የእለቱ የውይይት ርእሰ ጉዳይም፤ "The Role of Media in Climate Change Communications፡ Why should Editors Care?" የሚል ነበር፡፡

 በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረበችው ለረዥም ዓመታት በጋዜጠኝነት ሙያ ላይ የሰራችውና አሁንም በአንጋፋው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ በአዘጋጅነት እየሰራች የምትገኘው ጋዜጠኛ መታሰቢያ ካሣዬ ናት፡፡

የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ብክለት ጉዳይ፣ በአገራችን ሚዲያና ጋዜጠኞች እንዴት እየተዘገበ ነው የሚል ጥያቄ በማንሳት የጀመረችው ጋዜጠኛ መታሰቢያ ካሣዬ፤ በርካቶቹ ሚዲያዎች የአየር ንብረት ለውጥን አጀንዳ አድርገው እንደማይዘግቡና ለርዕሰ ጉዳዩ ፍላጎት እንደሌላቸው ጠቁማለች፡፡

ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት ያቀረበችው አንድም የዕውቀት ክፍተትን (እንዴት እንደሚዘገብ አለማወቅ) ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ  በቂ መረጃ ያለማግኘት ችግርን ነው።

ባለፉት ዓመታት፣ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ በስፋት መዘገቧን የገለጸችው ጋዜጠኛ መታሰቢያ፤ በአንዳንድ አካባቢዎች የመንግሥት ሃላፊዎች እንኳንስ በቂ መረጃ ሊሰጡ ቀርቶ በጋዜጠኛው ጥረት የተሰባሰቡ መረጃዎችና ምስሎችን ቀምተው ከአካባቢው የሚያስወጡበት ሁኔታ እንዳለ የራሷን ተሞክሮ በምሳሌነት አቅርባለች።

በአፍሪካ ባለፉት 50 ዓመታት፣ 170 የተፈጥሮ አደጋዎች መከሰታቸውንና ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ማጣታቸውን በጽሁፏ የጠቀሰችው ጋዜጠኛዋ፤ ይሄ የሚያሳየው የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ፣ በህይወት የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ መሆኑን ነው ብላለች። ለዚህም ነው ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ለጉዳዩ ትልቅ ትኩረት መስጠት ያለባቸው ስትልም አስረድታለች፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በቂና ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን ያገኝ ዘንድም ከሁሉም አስቀድሞ ኤዲተሮችና ሪፖርተሮች በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየመጣ ያለውን አደጋ በበቂ ሁኔታ መገንዘብ ይኖርባቸዋል ስትልም በአፅንኦት ተናግራለች፡፡

ኤዲተሮች በአየር ንብረት ለውጥ አጀንዳ ላይ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው ጉዳዩ የመኖርና ያለመኖር ወሳኝና አንገብጋቢ ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ ነው ብላለች፤ ጋዜጠኛዋ፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት አብዛኞቹ የማህበሩ አባላት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ  በቂ  የሚዲያ ሽፋን እያገኘ አይደለም የሚለውን የጋዜጠኛ መታሰቢያ ሃሳብ ይጋራሉ፡፡

አንድ የማህበሩ አባል በሰጡት አስተያየት፤ የአየር ንብረት ለውጥን ወይም የአካባቢ ብክለትን በደረቁ ከመዘገብ ይልቅ የሚያስከትለውን ወይም እያስከተለ ያለውን የጤና እክል አያይዞ መዘገብ የተሻለ ትኩረት እንዲያገኝ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ሌላዋ አስተያየት ሰጪም ተመሳሳይ ሃሳብ ሰንዝረዋል፡፡ ስለ አየር ንብረት ለውጥ ስንዘግብ በዳታ የታጨቀ ብቻ ከሚሆን ከሰው ህይወት (ጤና) ጋር አያይዘን ብንዘግበው የበለጠ ትኩረትና ተነባቢነት ሊያገኝ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

አንድ የማህበሩ አባል ደግሞ የአቅም ግንባታ ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግ  ተናግረዋል፡፡ ለዚህም ጋዜጠኞችና ኤዲተሮች በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ላይ  አጫጭር ስልጠናዎች የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠርና ማመቻቸት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል - ስልጠናው ጋዜጠኞችና ኤዲተሮች ጉዳዩን በበቂ እውቀትና ግንዛቤ እንዲዘግቡት አቅም እንደሚያስታጥቃቸው በመጠቆም፡፡

 ከሰሞኑ በሶማሊያ ክልል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውንና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የጠቆመችው ጋዜጠኛ መታሰቢያ፤ ሆኖም ግን አብዛኛዎቹ ሚዲያዎች ክስተቱን እንዳልዘገቡት መታዘቧን ተናግራለች፡፡ ይህም ሚዲያዎች ለአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በቂ ትኩረትና ሽፋን እየሰጡ አይደለም የሚለውን መነሻ ሃሳቧን ያጠናክርላታል፡፡  

 ባለፈው ሳምንት፣ በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ፣ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ፣ 24 ሰዎች መሞታቸውንና 23ሺ አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ የመንግሥት ሃላፊዎች የገለጹ ሲሆን፤ በተጨማሪም የጎርፍ አደጋው በአጠቃላይ 10ሺ ሄክታር የሰብል መሬት ማውደሙንና 3ሺ የቁም እንስሳትን መግደሉንም አመልክተዋል፡፡

በእርግጥም የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ የሚዲያዎችን ትኩረት ማግኘት አለበት የሚባለው በህይወት የመኖርና ያለመኖር አንገብጋቢ ጉዳይ በመሆኑ ነው፤ እንደ ሰሞኑ የሶማሌ የጎርፍ አደጋ፡፡