ኪነ-ጥበባዊ ዜና

Rate this item
(1 Vote)
የአፍሪካ ሞዛይክ የፋሽንና የባህል ትርኢት በሚቀጥለው አርብ ምሽት በሸራተን አዲስ የሚካሄድ ሲሆን በዝግጅቱ አለማቀፍ የፋሽን ሞዴሎችና ዲዛይነሮች ይሳተፋሉ፡፡ የአፍሪካን ሞዛይክ ዳይሬክተር አና ጌታነህ እንደገለፀችው፤ አስራ አምስት የውጪና የሀገር ውስጥ ዲዛይነሮች በሚሳተፉበት ትርኢት፤ እውቅ የዘርፉ ባለሞያዎች ከኒውዮርክ፣ ከደቡብ አፍሪካና ከሴኔጋል ይመጣሉ፡፡…
Rate this item
(9 votes)
በእናቱ ኢትዮጵያዊ፣ በአባቱ ሆላንዳዊ በሆነው ዳንኤል ጁፕሁክ የተፃፈውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “አመፀኛው ክልስ” የተሰኘ መጽሐፍ ሰሞኑን በገበያ ላይ ዋለ፡፡ ደራሲው በ12 ዓመት የእስር ቤት ቆይታው ያሳለፈውን ህይወት ከወህኒ ቤት ከወጣ በኋላ በደች ቋንቋ እንደፃፈው፣ ከዚያም ወደ አማርኛ በመተርጎም እንዳሳተመው…
Rate this item
(1 Vote)
በአሚር ዩኒስ ረሐስ የተፃፈው “የምሥራቅ ፈርጦች” የተሰኘ ታላላቅ የሐረሪ ተወላጆችን ታሪክ የያዘ መፅሃፍ ባለፈው ሳምንት ለንባብ በቅቷል፡፡ ስምንት የሚደርሱ የሐረሪ ሊቃውንቶችና የታሪክ ምሁራንን የሚያስተዋውቀው መፅሃፉ፤ መታሰቢያነቱን የሥነ ጽሑፍ ባለሙያ ለነበሩት ለአብዱል ሐፊዝ ከሊፋ መሐመድ እና ለመሐመድ ኢብራሒም ሱሌይማን አድርጓል፡፡ በመጽሐፉ…
Rate this item
(2 votes)
በዶ/ር ጌታቸው ተድላ የተፃፉትና ከዚህ በፊት ታትመው በነፃ የተከፋፈሉት “ከትዝታ ጓዳ” እና “እንደወጡ የቀሩት ኢትዮጵያዊ” መፃህፍቶች በድጋሚ ታትመው፣ ለሜቄዶንያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በስጦታ ተበረከቱ፡፡ ዶ/ር ጌታቸው በሜቄዶንያ በጐ ፈቃደኛ ሆነው እያገለገሉ ሲሆን ታህሳስ 13 ቀን 2006 ዓ.ም ማዕከሉ…
Rate this item
(0 votes)
በሰዓሊ ደረጀ ደምሴ የተዘጋጀው “ዑደት” የተሰኘ የስዕል አውደርዕይ የፊታችን ማክሰኞ ከምሽቱ 11 ሰዓት ተኩል በብሄራዊ ሙዚየም ይከፈታል፡፡ ኑቢያ አርት ስቱዲዮ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአውደርዕዩ የሚቀርቡት ስዕሎች የምንኖርበት አካባቢ በማንነት፣ በባህል እና በአኗኗር ላይ ያለውን ተፅዕኖ ያንፀባርቃሉ። “ዑደት” የስዕል አውደርዕይ ለተከታታይ…
Rate this item
(0 votes)
የግማሽ ሚሊዮን ብር ሽልማት የተዘጋጀለት የኮካ ኮላ ሱፐር ስታርስ ሁለተኛ ዙር “የተሰጥኦ ውድድር” መጀመሩ ተገለፀ፡፡ የኮካ ኮላ ብራንድ ማኔጀር አቶ ምስክር ሙሉጌታ ባለፈው ሐሙስ በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ እንደተናገሩት፤ ውድድሩ ከ13-29 አመት እድሜ ያላቸውን የሚያሳትፍ ሲሆን አዲስ አበባን ጨምሮ በዘጠኝ…