ልብ-ወለድ

Saturday, 28 June 2014 11:06

መፈንቅለ - እ’ግዜር

Written by
Rate this item
(3 votes)
የአጭር አጭር ልብ ወለድ በግጥምከዕለታት ባንዱ ቀን እንዲህ ሆነ . . . እባብ ድንገት መነኮሰ ቆዳ ቀዶ ማቅ ለበሰእንዲህ ሲሰብክ ተደመጠ . . . «በመጀመሪያ ፈጣሪ ወደገነት ደጅ ወረደ፤ ፀሐይን ከነሙቀቷ፣ ጨረቃን ከነድምቀቷ፣ ሔዋንንም ከነሳቋ ፈጠረና፤ ሰማይን በብርሃን አጣፈጠው ሌላውን…
Saturday, 14 June 2014 12:22

ለማሸነፍ

Written by
Rate this item
(10 votes)
ጋሻው በጠባቧ ስቱዲዮ ውስጥ በዘረጋት አነስተኛ አልጋ ላይ በጀርባው ተንጋሎ ይቃትታል፡፡ በእልህ ይቃጠላል ፣ በብሽቀት ይወራጫል፣ በምኞት ይንጠራራል . . . እንደተንጋለለ ዓይኑን ፊት ለፊቱ በሰቀለው ፎቶ ግራፍ ላይ ወረወረ፡፡ እይታው እዚህ ትልቅ ባለቀለም ፎቶ ግራፍ ላይ ካረፈ በቀላሉ አይነሳም፡፡…
Saturday, 07 June 2014 14:11

ሙሉ

Written by
Rate this item
(2 votes)
የጠላ ደንበኛዋ ናቸው፡፡ ኮረፌ ጠላ ሲወዱ ለጉድ ነው፡፡ እሱን እየጠጡ ነግቶ ቢመሽ ግድ የላቸውም፡፡ እሳቸው ካሉ፣ ኮረፌ ጠላው ካለና አንድ ሌላ ሰው ካልጠፋ መንደሩ ሁሉ እዚያች ጠላ ቤት ያለ እስኪመስል ይደምቃል፡፡ የሚወራው፣ የሚሳቀው፡፡ እሚጨበጨበው…ሁሉ እንደ መንደር ሙሉ ነው፡፡ እሷ ነጋዴዋ…
Rate this item
(8 votes)
(ተውኔቱ የሚካሄደው የናት አኬርማን ባለ ሁለት ፎቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው፡፡ መጋረጃው ከግድግዳው ጥግ እስከ ጥግ ተንጠልጥሏል፡፡ ትልቅ አልጋና የመልበሻ ጠረጴዛ ይታያል፡፡ ግድግዳው ላይ የተለያዩ ስዕሎችና እምብዛም ማራኪ ያልሆነ የነፋስ ግፊት (ባሮ ሜትር) ተንጠልጥሏል፡፡ መጋረጃው ሲገለጥ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ይንቆረቆራል፡፡…
Rate this item
(3 votes)
‹‹አክስቴ አሁን ትመጣለች›› አለች፤ ፍፁም ረጋ ያለችው የአስራ አምስት ዓመቷ ኮረዳ፡፡ ‹‹እስከዚያው ብቻዎትን እንዳይሆኑ ደግሞ ከእኔ ጋ ብንጨዋወት አይከፋም እ?››እንግዳው፤ቅንነት ለተመላበት ንግግሯ አፀፋ የሚሆን ርዕሰ ጉዳይ ፈጥሮ እያወጉ ቢቆዩ፤ ወዲያውም አክስቷን በማስጠራት ከማስቸገር፤ በራሷ ጊዜ ተመልሳ እስክትመጣ ለመጠበቅም ጥሩ ይሆናል…
Rate this item
(4 votes)
ከግቢዬ በውጪው በኩል የኮሽም አጥሬ አጠገብ ካለችው ግራር ሥር ተቀምጬ፣ ባሻገር ያለውን መስክ እየተመለከትሁ ነው። ከፊቴ አርባ ወይም ሃምሳ ክንድ ያህል ከእኔ ራቅ ብሎ አንድ ትልቅ የሾላ ዛፍ ይታያል። ዕድሜ ጠገብ በመሆኑ የግንዱ ዙሪያ ስፋት የሁለት ሰው እቅፍ ያህል ነው።…