በ“ስኮቲሽ” ደርቢ 19 እኩል ትኩረት ሳበ
ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ዛሬ በአንፊልድ ከሊቨርፑል የሚያደርጉትን ጨዋታ ከኤልክላሲኮ በላይ ነው ብለው ተናገሩ፡፡ ፈርጊ የሊቨርፑልና የማን ዩናይትድ ጨዋታ የፕሪሚዬር ሊጉ ብቻ ሳይሆን የምንዜም የዓለማችን ምርጥ ደርቢ ብለው ሲናገሩ ምናልባትም የሚመጣጠነው ሁለቱ የስኮትላንድ ክለቦች ሬንጀርስና ሴልቲክ የሚያደርጉት ፍልሚያ ነው በማለትም ተናግረዋል፡፡ የሁለቱ ክለቦች አሰልጣኞች የስኮትላንድ አገር ዜግነት ግጥሚያውን የስኮቲሽ ፍልሚያ አስብሎታል፡፡ ባለፈው የውድድር ዘመን ማን ዩናይትድና ሊቨርፑል የተገናኙበትን ጨዋታ በኦልድትራፎርድ ከ75ሺ በላይ ተመልካች ታድሞት የነበረ ሲሆን በዛሬ ጨዋታ የበለጠ ታዳሚ በአንፊልድ ሮድ ሊታደም እንደሚችል ተነግሯል፡፡
የአዲስ አበባ ዋንጫ በተመልካች ተሟሙቋል
7 ክለቦች እየተሳተፉበት የሚገኘው የአዲስ አበባ ዋንጫ በተመልካች ብዛት የተሟሟቀ ቢመስልም የቡድኖች አቋም ብዙም እንዳላረካቸው ስፖርት አፍቃሪዎች ገለፁ፡፡ ውድድሩ ዕረቡ እለት ሲጀመር ከምድብ አንድ በመክፈቻው ጨዋታ መብራት ሃይል 3ለ1 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ ደደቢት ኢትዮያ ቡናን 2ለ1 ረትቶታል፡፡ ሃሙስ እለት መከላከያና ከመድን ተጫውተው ሁለት እኩል ተለያይተዋል ፡፡
የቴቬዝ ጉዳይ አለየለትም
የአፍሪካ ህብረት የጋዳፊን ክፍተት በማን ይሞላው ይሆን?
* ጋዳፊ ለህብረቱ በዓመት 40 ሚ.ዶላር ይደጉሙ ነበር
የሊቢያው ህዝባዊ አብዮት አሁን ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ የአማጽያኑ ወታደሮች የጋዳፊ ታማኞች የመጨረሻ ይዞታና የጋዳፊ የትውልድ ከተማ የሆነችውን የሲርት ከተማን ለመቆጣጠር ተቃርበዋል፡፡ በህዝባዊ ምርጫ ስልጣን እስከሚያስረክብ ድረስ የሽግግር ምክር ቤቱ ተቀናቃኝ አልባ የሊቢያ መሪ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ አንድ ያልተመለሰ ጥያቄ ግን አለ፡፡ ለመሆኑ ኮሎኔል ጋዳፊ የት ነው ያሉት? ይህ ጥያቄ የሚሊዮን ዶላር ጥያቄ ነው፡፡ ለምን ቢባል የእሳቸው ደብዛና እንቅስቃሴ ካልታወቀና ተገቢውን እርምጃ ካልተወሰደ በቀር የሊቢያን ህዝባዊ አብዮት በአስተማማኝ መልኩ ማረጋገጥ አይቻልም፡፡
ሶርያ የተሰራችውእንዲህ ነው!
ቱኒዚያን ከሀያ አመታት በላይ ሠጥ ለጥ አድርገው ሲገዙ የነበሩትን አበዲን ቤን አሊን ለስደት፤ ግብጽን ለአርባ አመታት በማይበገር የብረት ክንድ ጨብጠው በአምባገነንነት ያስተዳደሯትን ሞሀመድ ሆስኒ ሙባረክን ከሥልጣን መንበር አባሮ ለፍርድ ያበቃው፤ ሊቢያን በፍፁም ፈላጭ ቆራጭነት ከአርባ ዓመት በላይ ሲገዙዋት የነበሩትን ኮሎኔል ሙአመር ጋዳፊን ደግሞ ከሚያፈቅሩት የስልጣን ወንበራቸው ነቅሎ በነፍሴ አውጭኝ የገቡበትን ያሰወረው አዲሱ የአረብ አብዮት ሶሪያንም መለብለብ ከጀመረ እነሆ መንፈቅ ሞላው፡፡
የማህጸን ፈሳሽ..Vaginal Discharge…
“እኔ የ28 አመት ሴት ነኝ፡፡ ከአንድ አመት ወዲህ የወንድ ጓደኛ አለኝ፡፡ ከጓደኛዬ ጋር መገናኘት በጀመርኩ በስድስት ወር ገደማ አንድ የማያስደስት ነገር ገጠመኝ፡፡ ከማህጸኔ አይቼው በማላውቀው መንገድ ፈሳሽ ይፈሰኝ ጀመር፡፡ የፈሳሹ መልክ የዘንጋዳ ውሀ እንደሚሉት ይመስለኛል፡፡ ጠረኑ ደግሞ ጥሩ አይደለም፡፡ የፈሳሹ መጠን የውስጥ ሱሪዬን ስለሚያረጥብብኝ በአንድ የውስጥ ሱሪ ቀኑን ሙሉ መዋል አልችልም፡፡ የግድ ግማሽ ቀን ላይ ሌላ የውስጥ ሱሪ መለወጥ ይጠበቅብኛል፡፡ ከማህጸኔ በሚፈሰው ፈሳሽ ምክንያትም ከጓደኛዬ ጋር ቀጠሮ መያዝ አቅቶኛል፡፡ ስለዚህም ጓደኛዬ እንገናኝ በሚለኝ ጊዜ ምክንያት እየፈጠርኩ ቀጠሮውን ስለማዛባ... በቃ... አትወጂኝም ማለት ነው ወደሚል አስተያየት እየመጣ ስለሆነ ከእሱም ልለያይ ነው ማለት ነው፡፡ በእርግጥ እኔም እወደዋለሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ችግር ምን ብዬ ልንገረው?... ሁኔታው ስለጨነቀኝ ነው ወደ እናንተ ይህንን መልእክት የላክሁት፡፡ እባካችሁ ባለሙያ አነጋግራችሁ መልሱን ንገሩኝ፡፡”
የገጣሚነት ጣጣ
ስለ ፍላጐት
1/ በክፍል ውስጥ እየተማርኩ ወረቀት ላይ ስሞነጫጭር ብዙ ጊዜ በመምህሮቼ እጅ ከፍንጅ እየተያዝኩ የዘለፋ እና የወቀሳ ቅጣቶች ተፈጻሚ ሆነውብኛል፡፡
2/ ታክሲ ላይ ወይም አውቶብስ ውስጥ ወይም መንገድ ላይ ድንገት በሚፈነዳ አስበርጋጊ ድምጽ የማደንቃቸውን ገጣሚዎች ግጥም ሳነበንብ ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ የሰው ሰላም በማናጋት ሙከራ ተገምቼ ግልምጫዎችን አስተናግጃለሁ፡፡
3/ የመንግስት ሰራተኛ እያለሁ አማርኛ ቋንቋ አስተምር ነበር፡፡ የተማሪዎችን ክፍለ ጊዜ ድርሰት በማንበብ ማባከኔ በልዩ አጣሪ ኮሚቴ ጥልቅ ምርመራ እና ፍተሻ ተደርጐ ስለደረሰበት በተማሪ፣ በወላጅ እና ወዘተረፈ ፊት እንደ ስጋ ከብት ተገምግሜያለሁ፡፡
4/ በ1996ቱ የመምህራን ኮንፍረንስ ላይ የተኮማተሩ የመምህራን ፊቶችን መፍታቴ፤ የተሰላቹ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎችን ልቦና ማደሴ፣ በመምህራን ጉሮሮ ውስጥ የተንጐረጐሩ ነጠላ ዜማዎችን በይፋ መዝፈኔ ይህንንም ሳደርግ ኪነትን እንደ መሳሪያ መጠቀሜን የወረዳው ካቢኔ ባደረገው ከፍተኛ ጥናትና ምርምር ስላረጋገጠ የካቢኔው ሰብሳቢ ከአስተዳደሩ የተበረከተልኝን የማባረሪያ ደብዳቤ ለግሶኛል፡፡
“ወንሕነሰ ተንሣእነ ወረታዕነ፡፡ እኛ ግን ተነስተን ፀንተንም ቆምን፡፡”
የተሸከምነው ክብደት ፍቅር ነው
ሙሉነት ተሰማኝ፡፡ የመጉድል ፍላጐት በፅኑ አደረብኝ፤ ለመፃፍ ተነሳሁ፡፡ መጉደል ማለት ማጣት አይደለም፡፡ የሀሳብ ደም በመጉደል የሚተካ ነው፡፡ መሆኑ ራሱ የፍቅር ባህርይ አለው፡፡
መቶ ቢሊዮን ፀሐዮች በእኛ ጋላክሲ ውስጥ፣ መቶ ቢሊዮን የኒውሮን ህዋሶች ደግሞ በእኔ የራስ ቅል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ምን ያህል የተራራቅን እና የተለያየን ነገሮች እንደሆንን ፀሐይ እና እኔ ወይንም ጋላክሲዋ (ሚልኪ ዌይ) አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ሙሉነት እንደዚህም ሆኖ ተሰምቶኛል፡፡ ሙሉነት የተነጣጠሉ ማንነቶችን እና ተቃርኗቸውን በአንድነት የሚሽር ልዕለ ተአምር ነው፡፡ የተአምሩ ስም “ፍቅር” ይባላል፡፡
የአንጋፋው አርቲስት ልደት በትያትር ምረቃ ተከበረ
አንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም አዲስ ትያትር እንዲመርቅ በክብር እንግድነት በተገኘበት ልደቱ ተከበረ፡፡ የአንጋፋው አርቲስት 55ኛ ዓመት ልደት የተከበረው ረቡዕ ጥቅምት 1 ምሽት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ትያትር ነው፡፡ የዘካርያስ ብርሃኑ ድርሰትና ዝግጅት የሆነው “ዕጣ ፈለግ” ትያትር የክብር እንግዳ አርቲስት ፍቃዱ፤ ለተዋናዮቹና ለትያትሩ እዚህ መድረስ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን በአዘጋጆቹ አቅራቢነት ከሸለመ በኋላ ሳይነገረው የትያትሩ አቅራቢ ሚሙ ፕሮዳክሽን ያዘጋጀለትን ኬክ ቆርሷል፡፡ ዝግጅቱ ሲፈፀም ስለልደቱ አከባበር የጠየቅነው አርቲስቱ፤ አራት ኪሎ አካባቢ መወለዱንና በልጅነቱ ወላጆቹ ያከብሩለት እንደነበር አስታውሶ ያሁኑን ግን ሳያስበው በማዘጋጀት እንዳስደመሙት ነግሮናል፡፡ የትያትሩ ደራሲና አዘጋጅ ዘካርያስ ብርሃኑ በበኩሉ “ባለቀ ሰዓት ትያትሩ ሊከፈት 90 ደቂቃ ሲቀረው በማወቃችን እንጂ እጅግ የምናከብረውን አርቲስት ልደት ሰፋ ባለ ዝግጅት ከዚህ በበለጠ ድምቀት ማክበር እንፈልግ ነበር” ብሏል፡፡
“ትዝታ ዘአለቃ ለማ” ውይይት ይደረግበታል
የፀሐፌ - ተውኔት መንግስቱ ለማ መጽሐፍ በሆነው “ትዝታ ዘለአለቃ ለማ” በሚዩዚክ ሜይደይ ኢትዮጵያ ውይይት ይካሄድበታል፡፡ ነገ ከቀኑ ስምንት ሰዓት አምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ የሚካሄደውን ውይይት ጋዜጠኛና የታሪክ ባለሙያ አቶ ኃይለመኮት አግዘው ይመሩታል፡፡