Administrator

Administrator

• ከ585ሺ 882 ተፈታኞች 48,929 ተማሪዎች አልፈዋል
• 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም
በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 8.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ይህን ያስታወቁት በዛሬው ዕለት ከ9 ሰዓት ጀምሮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
585 ሺህ 882 ተማሪዎች ፈተናውን መፈተናቸውን የጠቆሙት ፕሮፌሰር ብርሃኑ፤ ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 48,929 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸውን ገልጸዋል፡፡
50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ካስመዘገቡት መካከል የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 5.2 በመቶ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደግሞ 11.4 በመቶ እንደሆኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ጠቅሰዋል፡፡
ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡም በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፦ 591 ወንድ ተማሪ ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት፤ 579 ሴት ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት ሲሆኑ፤በማህበራዊ ሳይንስ ፦562 ወንድ ከአምቦ ቦርዲግ ትምህርት ቤት ፤ 548 ከሴት ከሴንት ጆሴፍ ትምህርት መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል። 50 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል ብለዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
• 445 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ ተገምቷል
ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ረጅሙን ባለ 62 ፎቅ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ለመገንባት እንዳቀደች የተዘገበ ሲሆን፤ ይህም የአገሪቱን የዝመና ጥረት አጉልቶ ያሳያል ተብሏል።
በዓለማቀፉ አማካሪ ቡድን ዳር አል-ሃንዳሳህ የተነደፈው ህንጻው እስከ 1,074 ጫማ ከፍታ ያለው ሲሆን፤ ከጆሃንስበርጉ ሊዮናርዶ ህንጻ በመላቅ በክልሉ ከሚገኙ ህንጻዎች ረጅሙ ያደርገዋል ሲል ግሬት አፍሪካ ዲጂታል ሚዲያ ዘግቧል፡፡
445 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ የተገመተው ፕሮጀክቱ፣ ጥብቅ የጨረታ ሂደትን ያካተተ ሲሆን፤ ይህም ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ኮንትራክተሮችን እንደሚፈልግ ማሳያ ነው ተብሏል።
በአዲስ አበባ ቂርቆስ ወረዳ ውስጥ የሚገነባው ሕንፃው፤ የሰማይ ላይ መናፈሻና ሬስቶራንት የሚያካትት ሲሆን፣ ቢዝነስን ከመዝናኛ ጋር የሚያጣምር እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
ኢትዮጵያ፣ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ለእስራኤል ፍልስጤም ግጭት የኹለት አገራት መፍትሄ ተፈጻሚ እንዲኾን ባለፈው አርብ ምሽት በአብላጫ ድምጽ ባጸደቀው ውሳኔ ላይ ድምጸ ተዓቅቦ አድርጋለች።
አስገዳጅነት የሌለውን ውሳኔ 142 አገራት ሲደግፉት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ 12 እገራት ድምጸ ተዓቅቦ አድርገዋል። እስራኤልና ፍልስጤም ኹለት አገራት እንዲኾኑ የሚያስችሉ "ተጨባጭ"፣ "በጊዜ ገደብ የታሠሩ" እና "የማይቀለበሱ" ርምጃዎች እንዲወሰዱ በውሳኔው የጠየቀው ጠቅላላ ጉባኤው፣ የፍልስጤሙን ሐማስንም ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ አውግዟል።
አሜሪካና እስራኤል ጠቅላላ ጉባኤው ይህን ውሳኔ ማሳለፉን አውግዘዋል።
ጠቅላላ ጉባኤው ይህን ውሳኔ ያሳለፈው፣ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ቤልጂዬም፣ ካናዳና አውስትራሊያ በተያዘው ወር ለፍልስጤም አገርነት በይፋ እውቅና ለመስጠት እየተዘጋጁ ባሉበት ዋዜማ ላይ ነው።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የተደረገ አንድ ጥናት፣ እያንዳንዱ እንደ ኮካ ኮላ ያለ ስኳር የበዛበት መጠጥ ጤናማ ህይወትን በ12 ደቂቃ ያህል እንደሚቀንስ አረጋግጧል።
ተመራማሪዎች ከበሽታ ነፃ በሆነ የህይወት ዘመን ላይ ያላቸውን ተጽእኖ ለመለካት 5,800 ምግቦችንና መጠጦችን ተንትነዋል።
ስኳር የበዛባቸው መጠጦች ለውፍረት፣ ለስኳር ህመምና ለልብ ህመም ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸው ሲሆን፤ ይህም ጤናማ ህይወትን እንደሚያሳጥሩ ያብራራል።
አንድ ስኳር ያለበት መጠጥ ወዲያውኑ ከህይወት ላይ ደቂቃዎችን ይቀማል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን አዘውትሮ መጠጣት የረጅም ጊዜ ጤናን እንዴት እንደሚጎዳ ያሳያል።
ውሃ ወይም ጣፋጭ ያልሆኑ መጠጦችን መምረጥ ጤናማ ህይወትን ሊያረዝም እንደሚችል ማሰብ ተገቢ ነው፡፡
ይህ ጥናት በየቀኑ የስኳር መጠንን መከታተልና ጤናማ ለውጦችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ኹነኛ ማሳያ ነው፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ፣ በከተማዋ በመንግሥትና በግል አጋርነት ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ፕሮጀክቶች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ አቶ አደም ኑሪ እንደተናገሩት፣ በአሁኑ ወቅት 60 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር የገቡ ሲሆን፣ ሌሎችም በቅድመ ጥናት ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ከፕሮጀክቶቹ መካከል የገበያ ማዕከሎች (ሞሎች)፣ የወንዝ ዳር ልማት አካል የሆኑ ፕላዛዎችና የመዝናኛ ስፍራዎች ተጠቃሽ መሆናቸው ተመላክቷል።
ድርጊቱ ሩሲያ ጦርነቱን እያሰፋች እንደሆነ የሚያሳይ ነው- ዘለንስኪ
በሩሲያና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት፣ ሩሲያ በዩክሬን መሠረተ ልማቶች ላይ በምትሰነዝረው ድንገተኛ የድሮን ጥቃት ምክንያት፣ በሮማኒያ አየር ክልል ላይ ጥሰት እንደተፈጸመ የአገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህን ተከትሎም የኔቶ አባልአገር የሆነችው ሮማኒያ፣ ሁኔታውን ለመከታተል ተዋጊ ጄቶቿን ማሰማራቷን ገልጻለች፡፡
የመከላከያ ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፣ ሁለት F-16 ተዋጊ ጄቶች ወደ አየር ከተላኩ በኋላ፣ በሮማኒያ አየር ክልል ውስጥ የነበረ አንድ ድሮን መለየታቸውንና ከራዳር እስኪጠፋ ድረስ መከታተላቸውን አስታውቋል።
የዩክሬኑ ፕሬዚዳደንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በጉዳዩ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ የሩሲያ ድሮን ከሮማኒያ ግዛት እስከ 10 ኪሎ ሜትር ዘልቆ መግባቱንና ለ50 ደቂቃ ያህል በኔቶ አየር ክልል ውስጥ እንደቆየ መረጃዎች እንደሚያሳዩ ጠቅሰዋል።
ፕሬዚዳንቱ ይህንን ድርጊት ሩሲያ ጦርነቱን እያሰፋች እንደሆነ የሚያሳይ ነው ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል።
ይህ ክስተት ፖላንድ የሩሲያን ድሮኖች አየር ክልሏን ከጣሱ በኋላ የኔቶን ምስራቃዊ ድንበር ለመከላከል ዕቅድ መያዙን ካስታወቀች ከጥቂት ቀናት በኋላ መከሰቱ፣ በአካባቢው ያለውን ውጥረት የበለጠ አባብሶታል ሲል መናኸሪያ ሬዲዮ ዘግቧል።
May be an image of aircraft
 
 
 
 
"በአገር ቤት የነበረኝ የፖለቲካ ተሳትፎ ምንም አልረዳኝም"
ከኢትዮጵያ ወደ ኖርዌይ ከሄደ አስር ዓመት ሆኖታል። ኢትዮጵያ ሳለ በጅማ ዩኒቨርስቲ ለ11 ዓመታት የቋንቋ እና ሥነ ልሳን መምህር ነበር። የሦስተኛ ዲግሪውን ለመሥራት ነበር ወደ ኖርዌይ ያመራው። በእርግጥ በኢትዮጵያ ሳለ ለፖለቲካ ባዕድ አልነበረም። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባል በመሆን በፓርቲው የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳትፏል።
ቢቢሲ እንደዘገበው፤ ወደ ኖርዌይ ለትምህርት ሲሄድ በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ውስጥ የተቃዋሞ እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ ነበር። የቀድሞው የጅማ ዩኒቨርስቲ መምህር አማኑዔል ራጋ ወደ አገሩ መመለስ ስጋት ሲፈጥርበት በኖርዌይ ኑሮውን አደረገ። በኖርዌይ ዜግነት አግኝቶ መኖር ከጀመረ ወዲህ ደግሞ ፖለቲካ ውስጥ በመምረጥም ሆነ በመመረጥ መሳተፍ እንዳለበት ወሰነ።
ከዚያም በኋላ የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ አባል ሆኖ መሳተፍ ጀመረ። ከሁለት ዓመት በፊት ፓርቲውን ወክሎ ለኦስሎ ከተማ ምክር ቤት ተወዳድሮ ነበር። ያ ተሳትፎ በፈጠረለት ዕድል የኦስሎ አንድ ክፍለ ከተማ የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። በዚያውም በአካባቢው የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ አስተዳደር አባል መሆን ቻለ።
ኖርዌይ ወደ አገራዊ ምርጫ ስታመራ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ፓርቲው እንዲሁም ግለሰቦችም ፓርቲውን ወክሎ እንዲወዳደር መረጡት። አሁን ደግሞ በአገራዊ ምርጫ ላይ ፓርቲውን ወክሎ እየተሳተፈ ነው።
የኖርዌይ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ እጅጉን የተለየ ነው የሚለው አማኑዔል፤ በአገር ቤት የነበረው የፖለቲካ ተሳትፎ ምንም እንዳልረዳው ይናገራል።
"ዲሞክራሲና አካታች የሆነ መንፈስ መፍጠርን፣ ተቃዋሚ ቢመጣ እንደ ጠላት ማየት ሳይሆን የራሱ ዕይታ ያለው የአገሪቱ ዜጋ መሆኑን መቀበልን የተማርኩት እዚህ ነው" ሲል ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ወቅት ተናግሯል።
በአገሪቱ ውስጥ በርካታ ዕድሎች አሉ የሚለው አማኑዔል፤ "ቁጭ ብሎ ከመመልከት ይልቅ በመሳተፍ የበኩሌን አስተዋጽኦ በማድረግ የምፈልገውን ለመለወጥ መጣር እንዳለብኝ ወሰንኩ" ይላል።
አማኑዔል በኖርዌይ ፖለቲካ ውስጥ ሰፊ አንቅስቃሴ የሚያደርጉ ፓርቲዎች ቢኖሩም የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲን የመረጠበት ምክንያት በቤተሰብ ዕሴቶች፣ በሰው ልጆች መብትና በሰብዓዊነት ላይ አተኩሮ ስለሚሠራ መሆኑን ለቢቢሲ ተናግሯል።
 
 
 
 
 
 
 

አሁን ሁሉም አፍሪካውያን ወደ ቡርኪናፋሶ ለመግባት ቪዛ አያስፈልጋቸውም ተብሏል፡፡ የቡርኪናፋሶ መንግሥት ማንኛውም አፍሪካዊ ያለቪዛ ወደ አገሪቱ መግባት እንደሚችል አስታውቋል፡፡

ጋና ከአሜሪካ የሚባረሩ ሰነድ አልባ የምዕራብ አፍሪካ ዜጎችን ለመቀበል በተስማማችው መሰረት፣ 14 የምዕራብ አፍሪካ ዜጎችን መቀበሏ ተዘግቧል፡፡
14 ግለሰቦችን ያካተተው የመጀመሪያው ቡድን አክራ መድረሱም ተሰምቷል። ከነዚህም መካከል ናይጄሪያውያንና ቢያንስ አንድ ጋምቢያዊ ይገኙበታል ተብሏል።
የጋና ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ውሳኔው በከፊል በ ECOWAS የነፃ እንቅስቃሴ ፕሮቶኮል ምክንያት ነው ብለዋል - በፕሮቶኮሉ መሰረት ምዕራብ አፍሪካውያን ያለ ቪዛ ወደ ጋና መግባት ይችላሉ።
ጋና ከአሜሪካ የምትቀበላቸውን ሰነድ አልባ የምዕራብ አፍሪካ ዜጎች ቁጥር አልገለጸችም።
ኬንያና ሩዋንዳ እስራኤል ባለፈው ማክሰኞ በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ባወጡት መግለጫ አወገዙ።
የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ሐሙስ መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፤ “ጥቃቱ የኳታርን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጣስ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና እና ለአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ከፍተኛ ስጋት ይፈጥራል” ብሏል።
ሩዋንዳ በበኩሏ ትናንት ባወጣችው መግለጫ፤ "እስራኤል መሠረታዊ የግዛት ሉዓላዊነትን ያለአግባብ መጣሷ አደገኛ ነው፤ ይህም ዓለምን ወደ ሥርዓት አልበኝነት እየመራት ነው" ብላለች።
የሁለቱ አገራት መግለጫዎች የተሰሙት ቀደም ሲል ሌሎች እንደ ናይጄሪያ፣ግብፅ፣ሞሮኮ፣አልጄሪያና ሶማሊያ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በተመሳሳይ እስራኤል በኳታር ላይ የፈጸመችውን ጥቃት ማውገዛቸውን ተከትሎ ነው።
 
 
 
 
 
Page 9 of 791