Administrator

Administrator

  አድማስ ዩኒቨርስቲ 14ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በማግኖሊያ ሆቴል ያካሂዳል። ዩኒቨርስቲው ለዘንድሮው ጉባኤ የመረጠው የጥናትና ምርምር ርዕስ “የከፍተኛ ትምህርት ጥራት፣ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ” የተሰኘ ሲሆን ለአንድ ሀገር ወሳኝ የሆነውን የትምህርት ጥራትና ከዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮ አንዱና ዋነኛው የሆነውን የማህበረሰብ አገልግሎት ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካ ቀንድን የሚዳስስ የጥናትና ምርምር ወረቀት በጉባኤው እንደሚቀርብ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ሞላ ጸጋ (ዶ/ር) ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል።ፕሬዚዳንቱ አክለውም ባለፉት 13 ዓመታት ዩኒቨርስቲያቸው የትምህርት ጥራቱን ማዕከል ያደረገና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ጉባኤ ሲያካሂድ መቆየቱን አስታውሰው በዚህ ረገድ ሃላፊነታቸውን ሲወጡ መቆየታቸውን ተናግረዋል። በዘንድሮውም የጥናትና ምርምር ጉባኤ ከላይ በተመረጠው ርዕስ ዙሪያ ምሁራን ጥናትና ምርምር ስራቸውን እንዲያቀርቡ በመጋበዝና ከቀረቡት ውስጥ የተሻለ ይዘት ያላቸውን በማወዳደር ለጉባኤው ማቅረባቸውን የገለጹት ሞላ ፀጋ (ዶ/ር) በዚህም ዘርፍ እየታየ ያለውን ክፍተት ለመሙላት መፍትሄ ጠቋሚ የሆኑ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። በዚህ ጉባኤ ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና  ከባለ ድርሻ አካላት ተወከሉ ሃላፊዎች እንደሚታደሙ ፕሬዚዳንቱ አብራርተዋል።አድማስ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ ካምፓሶቹ ከ20 ዓመታት በላይ በርካታ ዜጎችን በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በማስተማር በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ባለሙያ ከማድረጉም በላይ በሀገሪቱ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሃይል እጥረት በመሙላት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ያለ ተቋም ነው ተብሏል።

 ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ከATX ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (አፍሪካ ቴክ ኤክስፖ) የፊታችን ረቡዕ ጳጉሜ 2 ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ በስካይላይት ሆቴል ይከፈታል።
በተከታታይ ለሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤክስፖ በቴሌኮም፣ በፋይናንሻል ክፍያ፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ፣ በሶፍትዌር ግንባታ፣ በኤሌክትሮኒክስ፣ በሶላር ቴክኖሎጂ፣ በሳይበር ደህንነት፣ በባንክና ኢንሹራንስ፣ በሜትር ታክሲ፣ በኮንሲዩመር ቴክኖሎጂና በግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፎች የተሰማሩ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡
 መንግስት ለቴክኖሎጂው ዘርፍ የሰጠውን ልዩ ትኩረት ታሳቢ በማድረግና ይህንንም  ፖሊሲ ውጤታማ ለማድረግ እንደተዘጋጀ በተነገረለት በዚህ ዓለም አቀፍ ኤክስፖ፤ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጪ ኩባንያዎች እንደተሳተፉበትና በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት አዘጋጁ ጆርካ ኢቨንት ኦርጋናይዘር አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢንቨስትመንት ኮሚሽን እውቅናና አድናቆት የተቸረው  የቴክኖሎጂ ኤክስፖ፤ በእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሀገር ገፅታ ግንባታ፣ በኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሁም ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራ አዎንታዊ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነው ተብሏል፡፡
በመክፈቻው ዕለትም ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢኖቬሽንና ቴክሎጂ ሚኒስቴር፣ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢንቨስትመንት ኮሚሽንና ከሌሎችም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተጋበዙ ሚኒስትሮችና ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች እንደሚገኙም ታውቋል።

አሌክስ ዴ ዎል የተባለ ፀሐፊ “አዲስ ተግዳሮት በአፍሪካ ቀንድ” በሚል ዐቢይ ርዕስ ሥር- “አፍሪካ ቀንድ እና ቀይ ባሕር”- በሚል ንዑስ ርዕስ የሚከተለውን አስፍሯል። ምንጊዜም የማይበርደው የአፍሪካ ቀንድ ጉዳይ ዛሬም ለያዥ ለገራዥ እንዳስቸገረ አለ።
የአፍሪካ ቀንድ በታሪክ ራሱን እንደ አንድ ክልል አረጋግጦ ተቀምጦ አያውቅም። በአካላዊና በሰብዓዊ መልክዐ-ምድር ረገድ እጅግ መጠነ- ሰፊ ሲሆን፣ የክርስቲያኑንም የሙስሊሙንም ህብረተሰብ በማይተናነስ ቁጥር የሚነካ ነው። ህዝቦቹ´ኮ አፍሪካ ከመካከለኛው ምሥራቅ እና ከሕንድ ውቂያኖስ፣ በቅርቡ ደግሞ ከአውሮፓና ከአሜሪካ የተሳሰረ ነው። ያም ሆኖ እንደ አፍሪካ  ቀንድ ህዝብ ራሱን አያይም። ይልቁንም የአፍሪካ ቀንድ ከግዛቱ ውጪ ባሉ ሰዎች ነው በቅጡ የሚገለጠው። በተለይም በዓለም ታላላቅ ኃይሎች እንደ ችግር ፈጣሪ እየተቆጠረች ነው። የዛሬዋ አፍሪካ ቀንድ አሳሳቢ አባዜ፣ በዓለም አቀፉ የሥልጣን ትግል የደምበኛና የአቅራቢ ዓይነት እንዳይሆን ነው። ያ ደግሞ የገዛ ራስዋ ያልሆነ ጣጣ ነው።
የአፍሪካ ቀንድ ዋንኛ ዕዳ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጡ ነው። የስዊስ ካናል በ1869 እ.ኤ.አ ሲከፈት ቀይ ባሕር ከዋና ዋናዎቹ የንግድ ደም ስሮች አንዱ ሆነ። የዓለም ኃያላን መንግስታትም የባሕር መርከብ እንቅስቃሴ ደህንነት ጉዳይ ዋና ጉዳያቸው ሆነ እንጂ ውስጡን የማስተዳደሩ ነገር አላሳሰባቸውም ነበር። በግዛቱ አዲስ የጂኦ - ስትራቴጂ ፍላጎት ባደረ ቁጥር እንደ ሁልጊዜው ያንኑ ዓይነት ውጥረት ይከሰታል። ይሄ በ1950ዎቹ በስዊስ ካናል ላይ በቀዝቃዛው ጦርነት ጅማሮ ላይ ታየ። እንደገና ደግሞ በ1970ዎቹ የዐረብና እስራኤል ጦርነት ሊፋፋም አናቱ ላይ ሲደርስና በኃያላን ፍጭት፣ በምሥራቅ አፍሪካ ቀንድና በየመን ሲያጥጥ ፈጥጦ ወጥቷል።
ከዚያ የተከተለው እንግዳ የሆነ ታሪካዊ ሲላሲሎ ነው። አሊያም አፆለሌ ልንለው የምንችለው አዙሪት ነው! ለሩብ ምዕተ ዓመት ያህል የግዛቱ አገሮች የራሳቸውን አጀንዳ ሲያቀነቅኑ ነበር። ዓለም አቀፍ ፍላጎቱ ባይቆምም የስትራቴጂው ፋይዳ እየቀነሰ መጥቶ የሰብዓዊ ደህንነት -ማለትም እንደረሃብን ማቆምና ጅምላ ጭፍጨፋን መግታት አጀንዳ ሆኑ። ያም አሁን እያተለወጠ ነው። የኤደን ባሕረ-ሰላጤ ከአስርት ዓመታት በፊት፣ ለአጭር ጊዜ በሶማሊያ ድንበር በባህር ዘራፊዎች ስጋት ላይ ወድቆ ነበር።
አሁን ደግሞ የባሰ ቁም ስቅል የሚታይበት ጊዜ መጥቷል። የዐረባዊ ፔኒንዙላው አልቃይዳ የየመንን የተወሰነ የባሕር ዳርቻ ተቆጣጠረ። የመርከብ ኢንሹራንስ አሳሳቢ ነው። በሳውዲ የሚመራው የአገሮች ኅብረት፣ በየመኑ እርስ በርስ ጦርነት ጣልቃ መግባቱ አልቀረም። ሊፈረካከስ የደረሰውን ሁኔታ ይብስ ለማናጋት ለሱማሌ ተስፈንጣሪ ቡድኖች ገንዘብ ይረጫሉ። የኤርትራንም መነጠል ለማፍረስ የወታደራዊ ሰፈር ይመሰርታሉ።
የአዳዲስ ጦርነት መቀፍቀፍ ስጋት እያኮበኮበ ነው። የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት ውጥረትና ወታደራዊ አየር እየነፈሰበት ነው። በወታደራዊ ንቅናቄ በተነሳሳች በአዲስ መልክ ልብ በገዛች ኤርትራና በተቆጣች ኢትዮጵያ መካከል የሚኖረው ጠብ መጫር ሊናቅ አይገባውም። ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች ዓለማቀፋዊ ትኩረት እየሳቡ ነው፡-
አንደኛው- የባህር ደህንነት ጉዳይ ነው። ከሞላ ጎደል የአውሮፓና ኢስያ የንግድ እንቅስቃሴ በቀይ ባሕር ላይ የሚያልፍ ነው። በዓመት 700 ሚሊዮን ዶላር ያህል ነው። ቀላል አይደለም!
ሁለተኛው- በኃይል የተደገፈ ከባድ ጽንፈኝነት መኖሩ ነው- የአልሻባብ አደጋ የዋዛ አይደለም። የአፍሪካ ሕብረት ለዚህ የሰጠው ምላሽ የጸረ-ሽብርተኞች መቋቋሚያ ኃይል ነው። ያም በሰላም ጠባቂዎች ኃይል መልክ ነው።
እነዚህ አሸባሪዎችን ሲዋጉ በአንጻሩ ሳውዲና ኳታር ዋሐቢዝምን ለማስፋፋት የሙስሊም ጽንፈኝነትን ማጠናከሪያ ብር ያፈስሳሉ።
የመጨረሻና ሦስተኛው ጉዳይ ስደት ነው። ከሶርያውያንና ከአፍጋኖች ቀጥሎ ግፈኛ መንግስታቸውን በመሸሽ ከአገር የሚሰደዱና አውሮፓ የሚገቡ ህዝቦች ኤርትራውያን ናቸው። በተስፋ መቁረጥ የአውሮፓ ህብረት ለኤርትራ ዕርዳታ ይሰጣል። ቀቢፀ ተስፋ ነው ግን! ምንም ካለማድረግ ይሻላል ነው ነገሩ።
የአፍሪካ ኅብረት ይሄንን ስትራቴጂያዊ ገዋ መድፈን አለበት። የባህረ-ሰላጤውን ኅብረት ምክር ቤት ጋር አጋርነት  ፈጥሮ መንቀሳቀስ አለበት!

Saturday, 27 August 2022 11:47

የግንቦት 7 ልዩ ኮማንዶ

ወያኔዎችን ምን እንዳስጨነቃቸው አላውቅም። ያደረጉትን ለምን እንደሚያደርጉትም አልገባኝም። ከቤተሰቦቼ መሃል ከአባቴ በስተቀር ሌላ ማንም እስር ቤት እንዳይጎበኘኝ አድርገዋል። ጉብኝቱንም በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ ብቻ እንዲሆን ወስነዋል። የተሰጠን ጊዜም ግማሽ ሰዓት ብቻ ነው።
ማንም ሌላ እስረኛ እንዲህ አይነት ገደብ የለበትም። አባቴ ሊጎበኘኝ ሲመጣ እንደሌላው ጎብኚ ከሌሎች ጠያቂዎች ጋር አልቀላቀልም። እኔም ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅዬ አልጎበኝም። አባቴና እኔ የማንገናኘው የቃሊቲው አስተዳዳሪ ቢሮ ውስጥ መሆኑን ቀደም ብዬ ተናግሬለሁ። በየሳምንቱ አባቴን ለማግኘት ስንቀሳቀስ ሃምሳ ሜትር እርዝማኔ የሌለው መንገድ፣ መኪና ቀርቦልኝ እንደምወሰድም ጠቅሻለሁ።
ከሁሉ ያልገባኝ ነገር በመኪና መወሰዱ ሳይሆን የሚደረገው ጥንቃቄ ነው። መሳሪያ የያዘ ወታደር መኪናው ውስጥ አብሮኝ መግባቱ የተለመደ አሰራር ሊሆን ይችላል። እስረኛ ያለአጃቢ ስለማይንቀሳቀስ። ከዚህ አልፎ ግን እኔ በምንቀሳቀስበት ቀንና ሰዓት መንገዱን በሙሉ ከእስረኛ ብቻ ሳይሆን ከራሱ ከቃሊቲ ፖሊሶች ማጽዳት ለምን እንደፈለጉ ወይም እንደተገደዱ ነው አልገባ አለኝ።
ቅዳሜ ቀን ቃሊቲ በጣም ብዙ እንቅስቃሴዎች የሚታይበት ቀን ነው። ብዙ እስረኛ በቤተሰብ የሚጠየቀው ቅዳሜ ቀን ነው። እስረኛውም ገንዘብ የሚያገኘውም የሚያጠፋውም ቅዳሜ ነው። አሳሪዎቼ ብቻ ከነገሩኝ ተነስቼ ሳይሆን አንድ ቅዳሜ እኔም በመኪና ስወሰድ ያየሁት ነው። ትርምስ ነው። ወደ ላይ ወደ ታች የሚሉ ሸቀጥ የያዙ በወታደሮች የታጀቡ ሴትና ወንድ እስረኞች አይቻለሁ። ፖሊሶች ምግብ የሚበሉባቸውና ቡና የሚጠጡባቸው ዳስ ነገሮች በፖሊሶች ተሞልቶ አይቻለሁ። ይህን ያየሁት አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
ከዛ ቀን ውጭ በምንቀሳቀስበት ወቅት በምሄድበት መንገድ ወፍ ዝር እንዳይል ይደረጋል። መኪናው ወደ አስተዳደሩ ቢሮ እስከሚዞር በርቀት ዋናውን የግቢውን በር ማየት እችላለሁ። በዛ መንገድ ላይ እንኳን እስረኛ ፖሊስም እንዳይታይ ተደርጎ ነው የሚያንቀሳቅሱኝ። አንዳንድ ጊዜ ከታሰርኩበት ግቢ በራፍ ላይ እንድቆም ተደርጎ መንገዱ በሙሉ መጽዳቱን ብርሃኔ ጠይቆ ነው መኪና ላይ የምጫነው።
በዚህ ጉዞ አልፎ አልፎ ብርሃነና ሌሎች ፖሊሶች የሚጨቃጨቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። መንገዱ ጸድቷል ተብሎ ስንወጣ ከሆነ አሳቻ ስፍራ ብቅ ብቅ የሚሉ ፖሊሶች ነበሩ። እኔን ለማየት እንደሚፈልጉ ግልጽ ነው። ወደ መኪናው እያዩ የሚጠቋቆሙበትን ሁኔታ አይቻለሁ። ብርሃነ እነዚህን ፖሊሶች ወደ ወጡበት እንዲመልሱ ትእዛዝ ይሰጣል። እነሱም በፈቃደኝነት እሺ ብለው አይመለሱም። ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸውም በዝግታ እያጉረመረሙ ይመለሳሉ።
ሴት ፖሊሶች ተሰብስበው ቡና የሚጠጡበትን በቆርቆሮ የተሰራ ዳስ አልፈን ነው ወደ አስተዳደሩ ቢሮ የምንሄደው። አንድ እለት ብርሃነ እዛ ክፍት ዳስ ውስጥ ቡና ይዘው የሚያያቸውን ፖሊሶች በተመለከተ፣
“እኛ ወደዚህ ስንመጣ ነው እንዴ የእነዚህ ሴቶች የቡና ሱስ የሚቀሰቀሰው፤አሁን ስንወርድ እኮ  ቦታው ባዶ ነበር።” አለ። መኪና የሚነዳው የብርሃነ አገር ሰው ሴቶቹን በተመለከተ የሰጠው ኋላ ቀር አስተያየት አስደነገጠኝ። ከእነዚህ ቡና ከሚጠጡ ሴት ፖሊሶች መሃል በድፍረት ወታደራዊ ሰላምታ የምትሰጠኝ አንዲት ፖሊስ ነበረች። ማንም ቢያያት አትፈራም። እንዴት ዝም ይሏታል እያልኩ፣ በፈገግታ ሰላምታዋን ተቀብዬ አልፍ ነበር።
እኔንም ለማንቀሳቀስ ወያኔ በሚያደርገው ጥንቃቄ በመገረም ጉዳዩን በዝርዝር ለእንግሊዝ መንግስት ጎብኝዎቼ ነገርኳቸው።
“የግንቦት 7 ልዩ ኮማንዶ ከቃሊቲ መንጭቆ ያወጣኛል ብለው ይሰጋሉ መሰለኝ፤ ሲያንቀሳቅሱኝ ከምክንያት ያለፈ ጥንቃቄ ያደርጋሉ” አልኩ። በመሃከላችን ተቀምጦ የነበረው የደህንነት ሰው ተናደደ።
ጥንቃቄ የሚደረገው ስጓጓዝ ብቻ አይደለም። ከውጭ ሰው አምጥተው እታሰርንበት ግቢ ውስጥ የሚያሰሩት ነገር ካለ፣ “እቤት ውስጥ ግቡ” እንባላለን። ስራው እስኪያልቅ ይቆለፍብናል። ሽንት ቤትና እጅና እቃ መታጠቢያው ገንዳ አካባቢ የሚሰራ ስራ ካለም እንዲሁ ይቆለፍብናል።
ቃሊቲ ከገባሁ በኋላ ብዙ ጊዜ የተለያዩ የጤና መታወኮች ገጥመውኛል። መጀመሪያ ሰሞን የቃሊቲ እስር ቤት ሃኪሞች እንዲያዩኝ አልተፈቀደላቸውም ነበር። ለተብርሃን ተፈልጋ መጥታ ነው፤ እንደገና ለተቀሰቀሰብኝ ኪንታሮት በሽታ መድሃኒት የሰጠችኝ። እሷ ስትመጣ አሰፋና ዳዊት እቤት ውስጥ ይዘጋባቸዋል። ለተብርሃን ምርመራ የምታደርግልኝ ግቢው ውስጥ እደጅ ነው። የኪንታሮት ምርመራ ደጅ ማድረግ አልቻለችም። የነገርኳትን ብቻ ሰምታ መድሃኒት አዘዘችልኝ።
ከለተብርሃን በኋላ አስናቀች የምትባል የጤና መኮንን ተተካች። አስናቀች የቃሊቲ ሃኪም ናት። ስሟን ያወቅሁት ከተዘጉበት ክፍል በቀዳዳ አሾልቀው ካዩዋት ቁራኛዎቼ ነው። አስናቀች የትግራይ ተወላጅ አይደለችም። እንደ ለተብርሃን ሩህሩህ መሆኗ ያስታውቃል። ከበሽታዬ አልፋ እንደ ለተብርሃን ስለ ሌላ ነገር ግን አታናግረኝም። እንኳን ለሌላ ወሬ ከህክምና ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ለመናገርም ድፍረት ያላት አትመስልም። ፖሊሶቹን፤ “ከዚህ ዞር በሉ፤ ሃኪምና በሽተኛ ብቻቸውን መሆን (ፕራይቬሲ) ያስፈልጋቸዋል” አትላቸውም። “ለምንድነው እዚህ ካፊያ እያካፋ፣ እውጭ ምርመራ የማደርግለት” አትልም።
ቃሊቲ ከአምስት ጊዜ በላይ ጥርሴን በጣም ታምሜአለሁ። በህመሙ የተነሳ ፊቴ በተደጋጋሚ ክፉኛ አብጧል። ተስቦ፣ ቁርጠት፣ ተቅማጥ፣ የመሳሰሉት የጤና መታወኮች በተደጋጋሚ ገጥመውኛል። አንድ ሰሞን  ጉንፋን ደንበኛው አድርጎኝ ነበር። ሁሉም በሽታ በህመም ማስታገሻና በጸረ ባክቴሪያ መድሃኒት እንዲታለፍ ተደርጓል።
ጥርሴ እንዲነቀልልኝ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቤአለሁ። የሰማኝ አልተገኘም። የሚታዘዝልኝንም መድሃኒት በአንዴ ለመስጠት ፈቃደኛ  አይደሉም። ሰአቱ በደረሰ ቁጥር ጠዋት፣ ምሳ ሰዓትና እራት ሰዓት ላይ እየተቆነጠሩ ይሰጡኛል። ይህ አሰራር ቀድሞ ያልነበረ አሰራር ነው። ማታ ማታ እነ አብርሃም በሩን ቆልፈው ከሄዱ ለኔ ብለው አይመለሱም። በዚህ የተነሳ የህመም ማስታገሻ መድሃኒት ታዞልኝም መድሃኒቱ በእጄ ስለማይሰጠኝ እየተሰቃየሁ ማደር እጣዬ ነው።
እኔን ውጭ አውጥቶ ከሌላ ሃኪም ጋር ማገናኘት የማይታሰብ ነው። ቁራኛዎቼ ለትንሹም ለትልቁም ቃሊቲ ወደ አለው የጤና ክሊኒክና በአካባቢው ወዳለ ጤና ጣቢያ ይወስዳሉ። ከዛም አልፎ እስከ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና አግኝተዋል። ምንም ያህል ቢያመኝ ይህንን መብት ወያኔዎች ለኔ አልሰጡም።
አስናቀችም አንድም ቀን የሃኪምነት የሥነምግባር ግዴታዋን ተጠቅማ “ሌላ ቦታ ተወስዶ ይመርመር” የሚል ጥያቄ አቅርባ አታውቅም። የደረት ማዳመጫውንና የደም ግፊት መለኪያውን ይዛ መጥታ እዛው ጸሃይ ወይም ዝናብ ላይ የምታደርገውን አድርጋ ትሄዳለች። የደም ግፊቴን ስትለካ ግን ግፊቱ በትንሹም ቢሆን ከፍ የሚያደርግ ነገር ታስከትልብኝ እንደነበር ሳትረዳ ተለያየን።
ሌላው ከወያኔ ጥብቅ ቁጥጥር ጋር ተያይዞ የተነፈግኩት መብት ጸጉር የመስተካከል መብት ነው። እኔ ይህን መብት እንዳልጠይቅ በታፈንኩበት ወቅት ቦርሳዬ ውስጥ ያገኟትን የጸጉርና የጢም ማስተካከያ ተሰጥቶኛል። የራሴ ማስተካከያ ባይኖረኝ ኖሮ በጠርሙስ ይላጩኝ ነበር? ወይም ማስተካከያ ይገዙልኝ እንደነበር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው።
ቃሊቲ እንደገባሁ በዚህ ጸጉር ማስተካከያ ዳዊትና አሰፋን ጠይቄ ጸጉሬን እንዲያስተካክሉኝ ማድረግ ጀምሬ ነበር። በዛውም እነሱንም ተራ በተራ በዚሁ ማስተካከያ አስተካክላቸዋለሁ። እርስ በርስ በመጨቃጨቃቸው የተነሳና ጠባያቸውም እየተበላሸ ስለሄደ ሁለቱንም ማስተካከሌን አቆምኩ። እንዲያውም “ደጁን ማያ ሰበብ ይሆናችኋል። እነ ብርሃነ እየወሰዱ ሌላ ጋር እንድትስተካከሉ ያድርጉ” አልኳቸው። አሳሪዎቻቸውም ሳይወዱ በግድ እነአሰፋን ሌላ ዞን እየወሰዱ ማስተካከል ጀመሩ። ተስተካክለው እስኪጨርሱ ሌላ እስረኛ ማስተካከያው ክፍል እንዳይገባ ይደረግ ነበር። እነ ዳዊት ለአስተካካዮቹ አንድ ቃል እንዳይተነፍሱ ብርሃነ ወይም በሪሁ እዛው ተቀምጠው፣ ጠብቀው ሲጨርሱ ይዘዋቸው ይመለሳሉ።
ቁራኛዎቼ የትም ቦታ ሲወሰዱም በሻምበል በሪሁ ወይም በሻለቃ ብርሃነ ታጅበው ነው። ለህክምና እንደሚወሰደው እንደሌላው እስረኛ፣ ከሌላው እስረኛ ጋር ተቀላቅለው በአንድ መኪና አይሄዱም። የሚንቀሳቀሱት ለብቻቸው አንድ መኪና ተመድቦላቸው ነው።
ቤተሰብ ጥየቃም ሲሄዱ በሪሁ ወይም ብርሃነ ሳያጅቧቸው አይሄዱም። በተለይ የአሰፋ ቤተሰቦች የሚመጡበትን አስቀድመው ስለማይናገሩ እነ ብርሃነ ተፈልገው እስከሚገኙ ቤተሰቦቹ ለረጅም ሰዓታት የሚጉላሉበት ጊዜ ነበር። ዳዊት በሶስት ዓመት ዘመዶቹ ሊጎበኙት የመጡት አንድ ጊዜ ብቻ ስለሆነ ችግር አልነበረበትም። አንዷንም ጊዜ ቢሆን ዘመዶቹ ብዙ ተንገላተው የደም እንባ አንብተው ነው ሊያገናኙት የቻሉት። አሰፋና ዳዊት ከምግብ ጠባቂዎች ጋር በቀጥታ እየተገናኙ ምግባቸውን እንዳይቀበሉ የተደረገው ከመጋቢዎች ጋር እንዳያወሩ ተፈርቶ ነው።
ይህንና ሌሎችም ፈጽመው ቅጥ ያጡ ቁጥጥሮች ለማድረግ ወያኔ ለምን እንደተገደደ እስከ ዛሬ ለኔ ሚስጥር ነው።
(ከአንዳርጋቸው ጽጌ “የታፋኙ ማስታዎሻ” መጽሐፍ የተቀነጨበ፤2012 ዓ.ም)

Saturday, 27 August 2022 11:18

Vacancy

Company: SAS Ethio Import & Export PLC
Job Title: Deputy Admin Manager
Job Type: Permanent
Education: -Minimum of Bachelor's degree in Human Resources Management, Business Administration or related fields
Experience:  Minimum of 6 years or Master's degree with 3 years in multi Business Environment
Salary: As per company scale
Deadline: September 05 2022
Apply on This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.


Company: SAS Ethio Import & Export PLC
Job Title: Secretary & Receptionist
Job Type: Permanent
Education: -Minimum of Bachelor's Degree in secretarial science, Office Management & other relatedor Diploma /Level 3/ in Secretarial andOffice Management
Experience: Minimum of 2 years’ or with 4 years’
Salary: As per company scale  
Deadline: September 05 2022
Apply on This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Company: SAS Ethio Import and Export
Job Title: General Services Head
Job Type: Permanent
Education: - Bachelor's Degree in Business Administration, Procurement & Supplies management or related field.
Experience: - Minimum of 5 years in the General Service activities in a Multi Business environment
Desirable Skills: -   Background in Logistics, Supply Management, Mechanics, and Electricity
Salary: As per company scale
Deadline: September 05 2022
Apply on This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Company: SAS Ethio Import and Export
Job Title: Chief Internal Auditor
Job Type: Permanent
Education: - Minimum of Bachelor's degree in accounting or related field plus Professional
Certification: - IIA, CPA or ACCA
Experience: -6 years' or Master's Degree and 4 years' of related
Salary: As per company scale
Deadline: September 05 2022
Apply On This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.


Company: SAS Ethio Import and Export
Job Title: Customer Relationship Manager
Job Type: Permanent
Education: -Minimum of Bachelor's Degree in Marketing, Management, Business Administration or related field
Experience: -Minimum of 4 years in the Marketing of pharmaceuticals Products and Digital marketing with at least 2 years at supervisory/ Managerial level or Master’s Degree with 2years
Salary: As per company scale
Deadline: September 05 2022
Apply On This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

Company: SAS Ethio Import and Export
Job Title: Online Sales Manager
Job Type: Permanent
Education: - Minimum of Bachelor's Degree in Marketing Management, Business Administration or related field
Experience: - Minimum of 4 years in Marketing of Pharmaceuticals Products and Digital Marketing or Master’s degree with 2 years
Salary: As per company scale
Deadline: September 05 2022
Apply On This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 ህዝቡ ራሱን ከኢላማዎቹ እንዲያርቅ ጥሪ ቀርቧል

        የህወሓት ታጣቂ ቡድን የተኩስ አቁም ስምምነቱን በይፋ በማፍረስ የጀመረውና እስከአሁንም በዘለቀው ጦርነት ጉዳት ማድረስ መቀጠሉን የገለፀው የፌደራል መንግስት፤ በታጣቂ ቡድኑ ወታደራዊ ተቋሞች ላይ እርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በትግራይ ክልል ውስጥ በተለይም የታጣቂ ቡድኑ ወታደራዊ መሳሪያዎችና ማሰልጠኛዎች ባሉበት ስፍራዎች የሚኖሩ ወገኖች ራሳቸውን ከኢላማዎቹ እንዲያርቁም መንግስት መክሯል፡፡
በተያያዘ ዜና፤ የመንግስት  ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ዓለማቀፍ ማህበረሰብ፣ ህውሃትን ወደ ሰላም መንገድ እንደሚያመጣው ጥሪ ለሰላማዊ መንገድ እንዲያዘጋ ዓለማቀፍ ማህበረሰብ ህውሃትን ወደ ሰላም ለመንገድ እንዲያመጣው ጥሪ ያቀረበ ሲሆን ይህ ካልሆነና ህውሃት በጥቃቱ ከቀጠለ መንግስት በህግ የተለበትን ግዴታ ለመወጣት ሲል ማንኛውንም እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቋል። ጽ/ቤቱ ትናንት ባወጣው መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፤ ህውሓት ለሰላም የተከፈቱ በሮችን ሁሉ በመዝጋት የመከላከያ ሃይሉ ይዞ በቆየባቸው ቦታዎች ላይ ጥቃትፐ
 እየፈጸመ መሆኑን ገልጾ አለማቀፉ ማህበረሰብ “ሁለቱ ወገኖች” ከሚል ፍርደ ገምድል  ጥሪ ተላቆ ህውሓት መንግስት ወደያዘው የሰላም አማራጭ እንዲመጣ ግፊት ያደርግ ዘንድ ጠይቋል።


 ተኩስ እንዲቆምና ንግግሩ እንዲቀጥል ጠይቀዋል

         በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም የተቀሰቀ  በሰው ጦርነት አስደንግጦኛልም አሳዝኖኛልም ያሉት የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ፤ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና ንግግሩ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ያሳሰቡት ዋና ፀሀፊው፤ የሰብአዊ እርዳታዎች እንዳይስተጓጎሉ እንዲሁም ችግሩ በውይይትና ድርድር የሚፈታበት መንገድ ላይ ሁለቱም ወገኖች እንዲያተኩሩም በአፅንኦት ጠይቀዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ማለዳ ላይ ትግራይን በደቡብ በኩል በአማራ በሚያዋስኑ አካባቢዎች ለተጀመረው ጦርነት የፌደራል መንግስት ህወሓትን በተንኳሽነት ተጠያቂ ሲያደርግ፣ የህወሃት ቡድን በበኩሉ የፌደራሉን  መንግስት ተጠያቂ ማድረጉን ያነሱት ጉቴሬዝ፤ ከአምስት ወራት የተኩስ  ማቆም አቋም ሂደት በኋላ ድንገት ግጭት መቀስቀሱ እጅግ አስደንጋጭ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ በበኩላቸው፤ ግጭቱ በአስቸኳይ ቆሞ በንግግር ብቻ መፍትሄ እንዲመጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት በቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ በኩል ድርድር የሚፈጠርበትን ሁኔታ በማመቻቸት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰውም፤ ሆኖም ነገር ግን በህወሓት እምቢተኝነት እንዳልተሳካ ሊቀ መንበሩ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡
አሁንም የአፍሪካ ህብረት ጦርነቱ በሚቆምበት ሁኔታ ላይ አበክሮ እንደሚሠራ፣ ለዚህም ሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ከህብረቱ ተወካይ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ጋር  እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ላለፉት 5 ወራት የነበረው የተኩስ አቁም የበርካቶችን ህይወት መታደጉንና እርዳታ እንዲደርስ ማስቻሉን ያወሱት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት አሜሪካንን ስጋት ውስጥ እንደከተታት ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስና በመጨረሻም ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ብሊንከን ጥሪ አቅርበዋል።
“እንደገና ወደ ጦርነት መግባት የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ በሚጥሩት ላይ ሚና እንደሚጫወት፣ የሰዎችን መጠነ ሰፊ ስቃይ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣና ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ያስከትላል” ብለዋል-ብሊንከን።
አንቶኒ ብሊንከን አክለውም “አሜሪካ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅና ለአገሪቷ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ቁርጠኛ አቋም  አላት። አገሪቷ ያጋጠማትን ሁለንተናዊ ተግዳሮቶች፤ ታሪካዊ ድርቅን ማሸነፍና ክልላዊ ደህንነትን ማስፈንን ጨምሮ ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ ነን።” ብለዋል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይና  የአውሮፓ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳት ጆሴፍ ቦሬል በበኩላቸው፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት ማገርሸቱን የሚገልፁ ሪፖርቶች የሰላም ተስፋ ላይ ጥላቸውን ያጠላሉ ብለዋል።
ሁሉም ወገኖች ሁኔታው ይበልጥ ከመባባሱ በፊትና ወደለየለት ጦርነት ሳይገባ ግጭቱን እንዲያረግቡም ጠይቀዋል።
“ወቅቱ ለሰላም ውይይት የሚደረግበት ጊዜ ነው” ብለዋል-ቦሬል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ግጭት መቀስቀሱ እንደሚያሳስባት የገለጸችው እንግሊዝ በበኩሏ ሁኔታው ወትሮም አስከፊ ነበረውን የሰብአዊ ሁኔታ ይበልጥ ያባብሰዋል ብላለች።
የኢትዮጵያ መንግስትና የህወሓት ግጭት እንዲያቆሙና የፖለቲካ መፍትሄ ይመጣ ዘንድ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ድርድር እንዲመጡ እንግሊዝ አሳስባለች።
ቱርክ በበኩሏ በፌደራል መንግስት ለሰብአዊነት ሲባል የተኩስ አቁም ከታወጀ በኋላ ድግም ግጭት መቀስቀሱን የሚገልፁ ሪፖርቶች መውጣታቸው እንዳሳሰባት ገልጻ፤ ሁለቱም ወገኖች ግጭት በዘላቂነት እንዲቆም ለማድረግና በአገሪቱ ሰላና መረጋጋት እንዲሰፍን ወደ ንግግር እንዲመለሱ ጠይቃለች።
በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥልም ቱርክ ገልጻለች።


      - የዘረፈውን ነዳጅ በአስቸኳይ እንዲመልስ ተጠይቋል
        -“ለዓለም ምግብ ድርጅት ያበደርኩትን ነው መልሼ የወሰድኩት”

      የዓለም የምግብ ፕሮግራም ለእርዳታ ማጓጓዣ  ያጠራቀመውን 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ ህውሓት መዝረፉ ከዓለማቀፍ ተቋማትና ተቆርቋሪዎች ውግዘትን አስከትሎበታል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ቃል አቀባይ  ስቴፋን ዱጃሪክ ከትናንት በስቲ ማለዳ ከጀኔቫ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ነሐሴ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ማለዳ ህውኃት በመቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን 12 ታንከሮችና 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉን ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤትና የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማትና፣ የሰብአዊ መብት  ተቆርቋሪዎች ድርጊቱን ክፉኛ አውግዘዋል። ቃል አቀባዩ በሰጡት መግለጫ፣ ህውሐት የዘረፈው 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ በክልሉ ለእርዳታ ማሰራጨት ተግባር ማሳለጫ፣ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች ማዳበሪያና የተለያዩ ግብአቶች ማሰራጫ ሊውል የነበረ መሆኑን ጠቁመዋል። ነዳጁ መሰረቁ የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ተግባር በእጅጉ የሚያደናቅፍ በመሆኑ ህውሐት የዘረፈውን ነዳጅ አንድም ሳያስቀር በአስቸኳይ እንዲመለስ ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው አሳስበዋል።
ህወሃት በሰጠው ምላሽ፤ ለዓለም ምግብ ድርጅት ከወራት በፊት ያበደርኩትን ነዳጅ ወሰድኩ እንጂ አልዘረፍኩም ሲል አስተባብሏል።ህውሐት ነዳጁን ከመዝረፉም ባሻገር በመጋዘኑ የነበሩ አለማቀፍ የእርዳታ ሰራተኞችንም ማሰሩን መረጃዎች አመልክተዋል።በአሁኑ ወቅት በትግራይ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የእለት ደራሽ እርዳታ ጠባቂ  መሆናቸው ይታወቃል።ከዕለታት አንድ ቀን፣ የዱር አራዊት ሁሉ ንጉሥ አያ አንበሶ ታሞ አልጋ ላይ ይውላል፡ የጫካው አውሬዎችና እንስሳት በሙሉ ሊጠይቁት ይመጣሉ፡፡  ከቀበሮ በስተቀር፡፡
ተኩላ የቀበሮን አለመምጣት ተመልክቶ አጋጣሚውን ሊጠቀም ፈለገ፡፡ የረዥም ጊዜ ቂሙን ለመወጣት አስቦ ነው፡፡ ስለዚህም ወደ አያ አንበሶ ጠጋ ብሎ፤
«የዱር አራዊት ሁሉ የእርሶ ጤንነት አሳስቧቸው ሊጠይቁዎት ሲመጡ፣ ቀበሮ ግን ምን ንቀት አድሮበት እንደሆን አይታወቅም በአካባቢውም የለች፡፡ በጣም የሚገርም ነገር ነው» አለ፡፡
አያ አንበሶም፤
«የሆነ ችግር ገጥሟት ይሆን?» ሲል ጠየቀ፡፡ ሁሉም አራዊት፤ «እረ ምንም ችግር የገጠማት አይመስለንም» አሉ፡፡
ተኩላ እንደገና ለማጠናከር፤
«ደን ውስጥ በመዝናናት ወዲያ ወዲህ ስትል ታይታለች፡፡ የሷ ሽርሽር ከጌታዬ ከአያ አንበሶ ጤና ይብሳል እንዴ? ንቀት ነው እንጂ!» አለ፡፡
አያ አንበሶ ተናደደና ፈልጋችሁ ጥሯት ብሎ አዘዘ፡፡
ተኩላ ቀጥሎ፤ «መች እሺ ብላ ትመጣለች፡፡ ልቧ አብጧልኮ፡፡ ጥግብ ብላለች» እያለ አሁንም ነገር በማባባስ ላይ ሳለ፤ ቀበሮ መጣች፡፡ የመጨረሻውን የተኩላን ንግግር ሰምታለች፡፡
አያ አንበሶ በቁጣ፤
 «የት ቆይተሽ ነው እስካሁን?! የኔ ጤንነት ነገር ምንም አያሳስብሽም ማለት ነው?»
ቀበሮ ነገሩ ስለገባት በጣም በመለማመጥና በልመና አንደበት፤
«ጌታዬ አያ አንበሶ፤ የዘገየሁበትን ምክንያት ላሳውቅና የፈለጉትን እርምጃ ይውሰዱብኝ”
አያ  አንበሶም፤ «አጥጋቢ ምክንያት ካልሆነ ግን በክርኔ ደቁሼ አደቅሻለሁ» አለ፡፡
ቀበሮም፤
«ምክንያቴ በቂ መሆኑን አልጠራጠርም» አለች፡፡
«ቀጥይ በይ ተናገሪ» ተባለች፡፡
ቀበሮ እንዲህ ስትል ገለፀች:-
«ጌታዬ አያ አንበሶ፤ ከዱር አራዊት ሁሉ ለእርሶ ጤንነትና ደህንነት የተጨነቅሁ እኔ ነኝ። እዚህ ከመምጣት ይልቅ በየቦታው እየተዘዋወርኩ ለርሶ መድሐኒት እንዲነግሩኝ ሐኪሞች ሳነጋግር ነው የቆየሁት»
«እና ምንድነው መድሐኒቱ አሉሽ? አገኘሽ መድሐኒቱን?» አለና አያ አንበሶ በጉጉት ጠየቀ፡፡
«አዎን ጌታዬ፡፡ ከብዙ ድካም በኋላ አንድ አዋቂ ሀኪም አገኘሁ፡፡ እሱም ‹ለአያ አንበሶ መድሐኒት የሚሆናቸው አዲስ የተገፈፈ የተኩላ ቆዳ ለብሰው ሽፍንፍን ብሎ መተኛት ነው፡፡ በነጋታው ያላንዳች ሕመም ተነስተው መንቀሳቀስ ይችላሉ› አለኝ» ስትል አስረዳች ቀበሮ፡፡
አያ አንበሶ ይህን ሲሰማ ያላንዳች ማመንታት የተኩላውን አናት በክርን ብሎ ዘረረውና፤ «በሉ ቆዳውን ግፈፉልኝ» አለ፡፡
ቀበሮም በሆዷ «በሌላው ላይ ክፉ ማሰብ እንዲህ የራስን ክፉ ያሳያል» አለች፡፡
***
ክፉ አስቦ የራሱን ክፉ ከሚያይ ይሰውረን፡፡ እርስ በርስ ከመጠላለፍ ያድነን፡፡ ሣር ፈልጐ አሣር ከሚገጥመው ይሰውረን፡፡ ከክፉ መድሐኒተኛ ያድነን፡፡ ትምህርታችንን ለበጐ እንጂ ለተንኮል እንዳናውል ልቡናውን ይስጠን፡፡ ተመክሮአችንን ሌላውን ለማጥቂያ እንዳንጠቀምበት ታሪክ ይምከረን፡፡ በሸረኞች ተመክረን እርጥብ የተኩላ ቆዳ ከመልበስ ያድነን፡፡ የፖለቲካም፤ የኢኮኖሚም የባህልም ተስፋችን በቅንና በጐ ልቦና የሚታሰብ መሆኑን ለማየት ዐይናችንን ይግለጥልን፡፡
ከቶውንም፤ ከፖለቲካ ጭካኔ፣ ከኢኮኖሚ ምዝበራ፣ ከባህላዊ ድንቁርና ይሰውረን ዘንድ የነጋ-ጠባ ጉዟችንን ያለወገናዊነት እንመርምር፡፡ ያወጅናቸውን አዋጆች፣ ያወጣናቸውን መመሪያዎች  እኛው አፍራሽ እንዳንሆን እንጠንቀቅ፡፡ እንግሊዞች A LAW – MAKER IS A LAW - BREAKER የሚሉት እንዲህ አይነቱን ነው፡፡ ከዚያ ይሰውረን፡፡ አንድ ወደፊት ሁለት የኋሊት እንዳንሄድ ፍሬን ይኑረን፡፡ አንድ ችግር ለመፍታት ከመተኮሳችን በፊት ተጓዳኞቹን ችግሮች ለማየት ማስተዋል ይገባናል፡፡
«አጋዘን ሳድን መጀመሪያ ብቅ ያለው ላይ አልተኩስም፡፡ መንጋዎቹ እስኪሰበሰቡ እጠብቃለሁ።» ይለናል ኦቶ ማን ቢስማርክ፡፡
የከተማንና የገጠርን ዕድገት ማጣጣምና ማዋሃድ ከብዙ ውጣ ውረድ ያድነናል፡፡ በትምህርት፣ በጤና፣ በመሠረተ-ልማት ወዘተ. . .፡፡ ተመጋጋቢ እድገት ካልፈጠርን እየናጠጠ ከሚሄደው የህዝብ ብዛትና እየተስፋፋ ከመጣው የኑሮ ውድነት ጋር የነገ ተስፋችን እንዳይቀጭጭና ብርሃናችን እንዳይጭለመለም ዛሬ መጠንቀቅ ያባት ነው፡፡ በገጣሚ ፀጋዬ ገ/መድህን የከርሞ ሰው ውስጥ፣ አብዬ ዘርፉ የተባሉ ገፀ-ባህሪ የገጠሬና ከተሜ ነገሮች ሲዛቡባቸውና የልባቸው ሳይደርስ ሲቀር:-
«…ተስፋዬ እንደጉም መንጥቃ
ምኞቴ እንደጉድፍ ወድቃ
የወንድሜን ልጆች እንኳ፤
 ለርስታቸው ሳላበቃ
 የእኔ ነገር በቃ በቃ!» ይሉናል፡፡
The “far future” is already upon us ይላሉ፤ የሃይድሮ ኤሌትሪክ ሊቃውንት፡፡ ሩቁ ነገ ዛሬውኑ ተጭኖብናል እንደማለት ነው፡፡
ተስፋችን፡-
 ፍትሕ ርትዕ የሰፈነባት የሰማች አገር እንድትኖረን ነው፡፡
ምኞታችን፡-
 የፕሬስ ነፃነት የሚከበርባት አገር እንድትኖረን ነው፡፡
ተስፋችን፡-
“በቸሃ ዳፋ እነሞር ተደፋ´፣” (አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ)  የሚለው ተረት ዕውን እንዳይሆን ነው፡፡
ምኞታችን፡-
“በህግ ከተወሰደ በሬዬ፣ ያለህግ የተወሰደች ጥሬዬ” የሚለው ተረት ዕውን እንዳይሆን ነው፡፡ ተስፋችን፡- ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች የሚከበሩባት አገር እንድትሆን ነው፡፡ ተስፋችን፡- ተስፋ የማንቆርጥባት አገር እድትኖረን ነው፡፡
“የሀገራችን ፖለቲካ ችግር በአንድ አቅጣጫ መክረሩ ነው፡፡´ አሉና፣ ሊብራላይዝ´ መደረግ አለበት፤” አሉ፡፡
አንድ በሳል ሰው፤
“ሊብራሊዝሙንም አታጥብቁት” አሏቸው አሉ፡፡
ከአንድ ፅንፍ አንድ ፅንፍ በመሄድ ማክረር አደገኛ ነው፡፡ እጅግ ማክረርም፣ እጅግ መላላትም የየራሳቸው አደጋ አላቸው፡፡ ሚዛናዊ አካሄድን መልመድ አለብን። የወረት ጉዞን መናቅ አለብን፡፡ የችኮላን ውሳኔና ድምዳሜን መራቅ አለብን፡፡ አንድን ጥፋት የፈፀምነው አዲሱ መሀንዲስ በቀደደው መንገድ ግራ ግራውን ብቻ በመሄዳችን ከሆነ፤ ሌላው መሀንዲስ የቀደደው መንገድ ደግሞ ቀኝ ቀኙን ብቻ ሂድ፤ የሚል ከሆነ፤ ሁለቱም የፅንፍ መንገድ ይሆንና ሁለተዜ ጥፋት ሊሆን ይችላል፡፡ “የተረገመችን እግር  በቅሎ ነስቶ ጫማ ይሰጣታል” ማለት እንግዲህ ይሄ ነው። ቆም ብለን መካከለኛ መንገድ እናይ ዘንድ ዐይናችንን ይክፈትልን! የዐባይን ሁለት ሶስተኛ ውሃ የምትጠቀመው ግብፅ፣ አንድ ሶስተኛ ውሃ የምትጠቀመው ሱዳንና፣ ምንም የማትጠቀመው ኢትዮጵያ፤ አንድም ሶስትም ናቸው፤ የሚለውን እንመረምር ዘንድም ልቦናውን ይስጠን!!

Saturday, 20 August 2022 14:01

የማለዳ እንጉርጉሮ

    የማለዳ እንጉርጉሮ

አንዳንዴ ደግሞ ጎህ ቀዶ
አብሮኝ ያደረው ደወል ፥ ከራስጌየ ተጠምዶ
ከወፍ ቀድሞ ሲያመጣልኝ፥ ነግቶብሀል የሚል መርዶ
ብትት ብየ ደንብሬ፥
ግማሽ ፊቴን፥ ትራሴ ውስጥ ቀብሬ
“ እኮ ዛሬም እንደ ወትሮ
ካውቶቢስ ወደ ቢሮ
ከኬላ ወደ ኬላ
ዛሬም በግንባሬ ወዝ ልበላ
እሺ ከዚያስ በሁዋላ
እያልሁ ስሞግት ልቤን፥ መልሱን አያመለከትተኝ
ይሄን ያህል ነው የታከተኝ።
ጉዞየ ካዋላጅ እቅፍ፥ እስከ ገናዦች አልጋ
ባራት እግር ተጀምሮ፤ ባራት ሰው ሸክም እስኪዘጋ
መንገዱ መንገድ እየሳበ
ትንንሹ ዳገትም፤ ለትልቁ እያስረከበ
እንደ ሐረግ ስጎተት፥ እንደ ጥንቸል ስፈጥን፥
ምን ሽልማት ታሰበልኝ ?” ይህ ልፋቴን የሚመጥን፥
እያልሁኝ ሳውጠነጥን ፥
አንዳንዴ ደግሞ ሲመረኝ፥
እንደ ለማዳ ፈረስ ፥ ሞትን በፉጨት መጥራት ሲያምረኝ፥
ዛፉን የተቀማ አሞራ
በኮረንቲ ምሶሶ ላይ፥ ቤቱን ባዲስ መልክ ሲሰራ
ማሯን የተዘረፈች ንብ፥ በያበባው ስትሰማራ
አይና
እንዲህ እንዲህ እላለሁኝ፤ ራሴን በራስ ሳጽናና
‘ ሺህ ጊዜ ብትራቀቅ፥ ቃላት መርጠህ ብትገጥም
ከዚህ አሞራ አታንስም፥ ከዚች ንብም አትበልጥም
ተፈጥሮ ትግልን እንጂ፥ የድል ዋስትናን አትሰጥም’’
ቻለው!
(በእውቀቱ ስዩም)

Page 4 of 620