Administrator
Thursday, 13 November 2025 00:00
በጂንካ ከተማ የተከሰተውን በሽታ "ሲያክሙ የነበሩ" ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ሞቱ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጂንካ ከተማ በተከሰተው በውል ያልታወቀ በሽታ ለተያዙ ሰዎች "ሕምክና ሲሰጡ የነበሩ" ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ለቢቢሲ ገለጸ። የበሽታውን ምልክታ ባሳዩ ታካሚዎች ላይ "በፍጥነት የኩላሊት ሥራ የማቆም (fail)" ሁኔታ እንደታየም ተገልጿል።
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጂንካ ከተማ "ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሔሞራጂክ ፊቨር" በሽታ መከሰቱን ያስታወቁት ትናንት ረቡዕ ሕዳር 3/2018 ዓ.ም. በጋራ ባወጡት መግለጫ ነው። በሽታው መከሰቱን ያመለከቱት "የቅኝት መረጃዎች" መሆናቸውን የገለጸው መግለጫው፤ ስምንት ሰዎች "በበሽታው እንደተጠረሩም" ገልጿል።
"በሔሞራጂክ ፊቨር" የተያዘው የመጀመሪያው ሰው ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የመጣው "ከሦስት ሳምንት ገደማ" በፊት እንደነበር የሕክምና ተቋሙ ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሰላሙ ታደሰ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የወባ በሽታ እንደሆነ በመጠርጠሩ በሌላ የጤና ተቋም ሕክምና ሲያገኝ እንደነበር የገለጹት ዶ/ር ሰላሙ፤ ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የመጣው ሁኔታው "በጣም ከባድ" ሲሆን መሆኑን አስረድተዋል።
ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተሩ እንደሚናገሩት ታካሚው ወደ ሆስፒታሉ ከመጣ በኋላ ሕመሙ "አስጊ" ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን ቀጥሎም በሆስፒታሉ "አንድ ቀን ገደማ" ከቆየ በኋላ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ከተፈጠረ ከአንድ ሳምንት በኋላ ደግሞ ከግለሰቡ ጋር ንክኪ የነበራቸው ሰዎች ተመሳሳይ ምልክቶችን አሳይተው ለሕክምና መምጣታቸውን ገልጸዋል።
"ከሳምንት በኋላ፤ ከዚያ ታካሚ ጋር በተለያየ ምክንያት ጉርብትና፣ አንድ ላይ የነበሩ ጓደኞቹ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ምልክት ማሳየት ጀመሩ" ሲሉ ያጋጠመውን ተናግረዋል። በሌሎች ታካሚዎች ላይ ተመሳሳይ ምልክት መስተዋሉን ተከትሎ ሆስፒታሉ ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ መላኩን አስረድተዋል።
ዶ/ር ሰላሙ እንደሚገልጹት የዚህን በሽታ ምልክት በማሳየታቸው በሆስፒታሉ ሕክምና የተደረገላቸው "ስምንት ገደማ ሰዎች" ናቸው። ከእነዚህ ታካሚዎች ውስጥ ለበለጠ ሕክምና ወደ ሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከተማዎች የተላኩ እንዳሉበት ጠቅሰዋል።
ታካሚዎች ሪፈር የተደረጉበት አንዱ ምክንያት በግለሰቦቹ የታየው "ኩላሊት በፍጥነት የመክሸፍ (ፌል)" የማድረግ ሁኔታ እንደሆነ አስረድተዋል። "የኩላሊት ሁኔታቸው በጣም ቶሎ ነበር ሥራ የማቆም (fail) የማድረግ ደረጃ የደረሰው። አንዳንዶቹ normal range የነበሩት ሰዎች በሁለት በሦስት ቀን ስታይ 4፣ 5 የመሆን፤ ከዚያም ሰባት የመሆን [ነገር ነበር]። ከሚጠበቀው በላይ ኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ነበር" ሲሉ በታካሚዎች ላይ የታየውን ሁኔታ አስረድተዋል።
"ከሳምንት በኋላ፤ ከዚያ ታካሚ ጋር በተለያየ ምክንያት ጉርብትና፣ አንድ ላይ የነበሩ ጓደኞቹ ከእርሱ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ምልክት ማሳየት ጀመሩ" ሲሉ ያጋጠመውን ተናግረዋል። በሌሎች ታካሚዎች ላይ ተመሳሳይ ምልክት መስተዋሉን ተከትሎ ሆስፒታሉ ናሙናዎችን ወደ አዲስ አበባ መላኩን አስረድተዋል።
ዶ/ር ሰላሙ እንደሚገልጹት የዚህን በሽታ ምልክት በማሳየታቸው በሆስፒታሉ ሕክምና የተደረገላቸው "ስምንት ገደማ ሰዎች" ናቸው። ከእነዚህ ታካሚዎች ውስጥ ለበለጠ ሕክምና ወደ ሐዋሳ እና ወላይታ ሶዶ ከተማዎች የተላኩ እንዳሉበት ጠቅሰዋል።
ታካሚዎች ሪፈር የተደረጉበት አንዱ ምክንያት በግለሰቦቹ የታየው "ኩላሊት በፍጥነት የመክሸፍ (ፌል)" የማድረግ ሁኔታ እንደሆነ አስረድተዋል። "የኩላሊት ሁኔታቸው በጣም ቶሎ ነበር ሥራ የማቆም (fail) የማድረግ ደረጃ የደረሰው። አንዳንዶቹ normal range የነበሩት ሰዎች በሁለት በሦስት ቀን ስታይ 4፣ 5 የመሆን፤ ከዚያም ሰባት የመሆን [ነገር ነበር]። ከሚጠበቀው በላይ ኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ነበር" ሲሉ በታካሚዎች ላይ የታየውን ሁኔታ አስረድተዋል።
ቫይራል ሔሞራጂክ ፊቨር ምንድን ነው?
የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ቫይራል ሔሞራጂክ ፊቨር (Viral haemorrhagic fever) ለተለያዩ የቫይረስ ሕመም ዓይነቶች የተሰጠ የወል ስም ነው። ቢጫ ወባ፣ የደንጊ ትኩሳት (dengue fever) እና ኢቦላ ተጠቃሽ ናቸው።
ክሪሚያን-ኮንጎ ሔሞረጂክ ፊቨር (Crimean–Congo haemorrhagic fever) እና ሪፍት ቫሊ ፊቨር (Rift Valley fever) የተባሉት በሽታዎችም እዚህ ውስጥ እንደሚካተቱ የዓለም የጤና ድርጅት በድረ ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያስረዳል።
ሔሞራጂክ ፊቨር፤ በዋናነት የሰውነትን የደም ዝውውር (vascular system) የሚጎዳ እና ሰውነት ራሱን የሚቆጣጠርበትን አቅም የሚያሳጣ ነው። ሕይወትን እስከመቅጠፍ የሚደርስ ሕመም እንደሆነም ተገልጿል።
የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ትናንት ባወጡት መግለጫ፤ በጂንካ ከተማ የተከሰተው ሔሞረጂክ ፊቨር "ምንነቱ በመረጋገጥ" ላይ እንደሆነ አስታውቀዋል።
የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወካይ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶ/ር ሰላሙም በተመሳሳይ በጂንካ የተከሰተው የትኛው የበሽታው ዓይነት እንደሆነ የሚታወቀው በኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገ በኋላ መሆኑን አስረድተዋል።
"[ምርመራው] እየተሠራ ነው፤ የትኛው እንደሆነ ይፋ ይደረጋል። እኛም በትዕግስት እየጠበቅን ነው" ብለዋል።
የጤና ሚኒስቴር እና ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም "የላብራቶሪ ምርመራዎች" እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል። በተጨማሪም፤ "የበሽታውን መንስኤ ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭትን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጩ ቡድን ወደቦታው በመላክ" የመስክ ግምገማ እንደሚያደረግ ገልጸዋል።
የፌደራል መንግሥት ተቋማቱ የተላከው ግብረ ኃይል በዛሬው ዕለት ጂንካ ከተማ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዶ/ር ሰላሙ አስረድተዋል።
የሕመሙ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
ሁለቱ የፌደራል መሥሪያ ቤቶች ባወጡት መግለጫ ላይ የሕመሙ ምልክቶች እንደሆኑ ከዘረዘሯቸው ውስጥ "በአፍ፣ አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች መድማት" የሚለው ይገኝበታል። "ትኩሳት፣ ማስቀመጥ እና ማስመለስም" በምልክትነት ተጠቅሰዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ድንገተኛ የጡንቻ ሕመም፣ ራስ ምታት እንዲሁም እና ከደም መፍሰስ ጋር የተያያዘ ሾክን በተጨማሪ ምልክትነት አስፍሯል። ሕመሙ የሰውነት ክፍሎችን መደበኛ ሥራ የሚያስተጓጉል (organ failure የሚያስከትል) እንደሆነም የተቋሙ መረጃ ያሳያል።
የሕመሙ የመጀመሪያ ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ድካም፣ የጡንቻ ሕመም እና ምቾት አለመሰማት ናቸው። ሕመሙ እየተባባሰ ሲሄድ የሆድ ሕመም፣ ማስመለስ፣ ማስቀመጥ፣ የቆዳ መቆጣት እንዲሁም ፊት እና ደረት ላይ የሚሰማ ሙቀት ያስተዋላል።
ሕመሙ በተባባሰባቸው ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ ደም መፍሰስ (haemorrhaging) ይከሰታል። ከአፍ እና ከአፍንጫ እንዲሁም ከሌሎች የሰውነት ክፍሎችም ደም ይፈሳል።
የሕመሙ የመጀመሪያ ምልክቶች ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ ድካም፣ የጡንቻ ሕመም እና ምቾት አለመሰማት ናቸው።
ሕመሙ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ከፍተኛ ደም መፍሰስ እና ሞት ያስከትላል።
እንዴት ይተላለፋል?
የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፤ በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ጋር ቀጥተኛ የአካል ንክኪ ወይም በበሽታው ከተያዙ ሰዎች ሰውነት የሚወጣ ፈሳሽ ወይም ደም መንካት ሕመሙ እንዲተላለፍ ያደርጋል።
ክሪሚያን-ኮንጎ ሔሞረጂክ ፊቨር እና ሪፍት ቫሊ ፊቨር በተባሉት የሕመሙ ዓይነቶች በበሽታው የተያዙ እንሰሳትን ጥሬ ሥጋ እና ወተት መመገብ ለበሽታው እንደሚያጋልጥ ተጠቅሷል።
እንደ ሪፍት ቫሊ ፊቨር እና ደንጌ ፊቨር ባሉት የሕመሙ ዓይነቶች ደግሞ የወባ ትንኝ ንክሻ በሽታውን እንደሚያስተላልፍ ተገልጿል።
'rodents' የተባሉት የአይጥ ዝርያዎችም በሽታውን እንደሚያስተላልፉ ተጠቅሷል።
ሕመሙን እንዴት መከላከል ይቻላል?
ትናንት ማምሻውን የወጣው መግለጫ፤ "ምልክት ከታየበት ሰው ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም" እንደሚያስፈልግ አሳስቧል። "ሁልጊዜ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በውሃ እና ሳሙና በመታጠብ ማጽዳት" እንደሚያሻም ተገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት 'viral haemorrhagic fevers' ወይም በምጽሐረ ቃሉ 'VHFs' በሚል አጠቃላይ መጠሪያ የጠቀሰውን ሕመም "በመላው ዓለም እየተባባሰ የመጣ ስጋት ነው" ሲል ይገልጸዋል።
አጠቃላይ የሕመሙን ዓይነቶች ለማከም የሚውል መድኃኒት እንደሌለ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።
ሆኖም ግን የቢጫ ወባ እና ኢቦላ ክትባቶች የሕመሙን ዝርያዎች ለመከላከል እንደሚረዱ ተገልጿል። በሕመሙ የተያዙ ሰዎች ትኩሳታቸው እንዲቀንስ በማድረግ፣ የመተንፈሻ አካላቸው በአግባቡ እንዲሠራ ኦክስጅን በመስጠት እና በሌሎችም መንገዶች የሕክምና እርዳታ ይሰጣቸዋል።
BBC
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
Published in
ዜና
Tagged under
Thursday, 13 November 2025 00:00
"ሿሿ” ሲፈፅሙ የተያዙ 7 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራው ቀጥሏል
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው የሞባይል ስልክ ስርቆት ፈፅመው ለማምለጥ ሲሞከሩ በተያዙ 7 ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ስራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተለምዶ "ሿሿ” የተባለውን ወንጀል በመፈፀም ሞባይል ስልክ ሰርቀው ለማምለጥ ሲሞከሩ በተያዙ 7 ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ስራው መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ናትናኤል አለሙ ፣ አቤል ኮርሳ ፣ ዕድላዊት መላከ፣ መቅደስ አቡሽ፣ ኢዛና ባህሩ፣ ፀጋ ታደሰ እና መቅደስ አምዴሳ የተባሉ ሲሆኑ፤ ሽፈራው ገበየሁ በተባለ ግለሰብ ላይ ወንጀሉን የፈፀሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኮዬ ቂሊንጦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡
ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ተጠርጣሪዎቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- 89261 ኦ.ሮ በሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው የግል ተበዳይን ጭነው እየተጓዙ ሞባይል ስልኩን ከኪሱ ከሰረቁ በኋላ፣ "ትራፊክ ይቀጣናል ጋቢና ግባ ብለው" እንዳስወረዱትና ከወረደ በኋላ ጥለውት እንዳመለጡ ተገልጿል፡፡
በግል ተበዳይ ላይ ወንጀል እንደተፈፀመ የተመለከቱ የህብረተሰብ ክፍሎችና ፖሊስ በጋራ ባደረጉት ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 5 ሴቶች እና 2 ወንዶች ሳሪስ አቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከተሽከርካሪው ወርደው ሊሰወሩ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በወቅቱ በተሽከርካሪው ላይ በተደረገ ፍተሻ ከተለያዩ ግለሰቦች ላይ በተመሳሳይ መልኩ የተሰረቁ ዘጠኝ ሞባይል ስልኮች የተያዙ ሲሆን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የጀመረውን የምርመራ ስራ አጠናክሮ መቀጠሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡
በተጠቀሰው ተሽከርካሪ እና በተያዙት ተጠርጣሪዎች ተመሳሳይ ወንጀል ተፈፅሞብኛል የሚል ግለሰብ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ ከተያዙት ስልኮች መካከል የእሱ ንብረት ስለመኖሩ በማረጋገጥ እንዲወስድና ለፖሊስ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል፡፡
መሰል የወንጀል አፈፃፀሞችን ለመከላከል በየጊዜው የሚገለፁ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ተግባራዊ በማድረግ በከተማችን ሊፈፀሙ የሚችሉ ወንጀሎችን አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር እንደሚቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውሶ፤ አጠራጣሪ ነገር ሲያጋጥም ህብረተሰቡ ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ተባባሪነቱን ማጠናከር እንደሚጠበቅበት ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።
Published in
ዜና
Tagged under
Friday, 14 November 2025 12:25
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች በእስራኤል የ6 ቀናት ጉብኝት ያደርጋሉ
ከተለያዩ የኢትዮጵያ ሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ 20 የሚደርሱ ጋዜጠኞችና አዘጋጆች በእስራኤል የ6 ቀናት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ፡፡
የፊታችን እሁድ ወደ እስራኤል ቴልአቪቭ የሚጓዙት ጋዜጠኞቹ፣ በቆይታቸው የሦስት ትላልቅ ሃይማኖቶች እምብርት በሆነችው ኢየሩሳሌም የሚገኙ ቅዱስ ሥፍራዎችን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡ ጉብኝቱ የድንበር አካባቢዎችንም የሚያካትት ሲሆን፤ ጋዜጠኞቹ ከኦክቶበር 7ቱ የሃማስ ጥቃት በህይወት ከተረፉ እስራኤላውያን ጋር የመገናኘት ዕድል ያገኛሉ፡፡
በተጨማሪም፣ የሚዲያ ቡድኑ የእስራኤል ፓርላማን እንዲሁም አንጋፋ የእስራኤል ሚዲያ ተቋማትንም ይጎበኛል፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል ምክትል አምባሳደር ቶመር ባር-ቪ አንደተናገሩት፤ የእስራኤል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂም የጋዜጠኞቹ የጉብኝት አካል ነው፡፡
በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ዶ/ር አቭረሃም ንጉሴ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ሚዲያ ልኡክ ጉብኝት የእስራኤል የህዝብ ለህዝብ ዲፕሎማሲ አካል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የጉብኝቱ አንዱ ዓላማ ላለፉት ሁለት ዓመታት በሰባት የተለያዩ የጦር ግንባሮች ስትዋጋ የዘለቀችው እስራኤል አሁናዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል ጋዜጠኞች በዓይናቸው አይተውና አረጋግጠው እውነቱን እንዲረዱና እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው ብለዋል - አምባሳደር አቭራሃም፡፡
የኢትዮጵያ ሚዲያ ልኡክ ጉብኝት የተዘጋጀው በእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካኝነት ሲሆን፤ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጋዜጠኛ ቡድን ወደ እስራኤል ሲጓዝ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:40
"ወደ ካምፕ ኑ ስቴዲየም መመለስ እፈልጋለሁ"
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ እድሳት የተደረገለትን ካምፕ ኑ ስቴዲየምን ጎብኝቷል።
የወቅቱ የኢንተር ማያሚ አማካይ፣ ብዙ ታሪክ የሰራበትን ስቴዲየም በጎበኘበት ሰዓት ወደ ካምፕ ኑ መመለስ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
የ38 ዓመቱ ተጫዋች በ2021 ነበር ከፋይናንስ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች፣ ይህን ግዙፍ ስታዲየምና ክለቡን ለቆ ለመሄድ የተገደደው።
"ትላንት ምሽት በእጅጉ ወደ ናፈቅሁት ስፍራ ተመለስኩ" በማለት ካምፕ ኑን የገለፀው ሜሲ፤ ቦታው ብዙ ደስታዎችን ወደ ህይወቱ ያመጣበት ስፍራ መሆኑንም አንስቷል።
የስምንት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ተጫዋች ያኔ በ2021 የባርሴሎና ቆይታው የተቋጨው በእንባ ብቻ ነበርና፣ አሁን ወደዚህ የልጅነት ትዝታው ወደተኖረበት ስፍራ ተመልሶ "ከሚወዱኝና ከምወዳቸው" ጋር በወጉ "ደህና ሁኑ" መባባል እፈልጋለሁ ብሏል።
በእድሪስ አህመድ
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:38
"ያስለመድኳችሁን ፓስቲና ሻይ አላስቀርም"
የእኔ ነገር አላርፍም አይደል? እነሆ ስድስተኛ መጽሐፌን ላስመርቅ ነው። "ዥዋዥዌ" ብዬዋለሁ። አርባ ሰባት የዘመን ማስታወሻ ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡ የተስተካከለና የተመሰቃቀለው፤ የተሳካና የተሰናከለው፤ የሚያምርና የሚያስቀይመው፤ የሚያስደስትና የሚያማርረው፤ የሚያኮራና የሚያሳፍረው ዘመነኛ ኢትዮጵያዊ ሕይወታችንን እንደ ወረደ በእነዚህ ታሪኮች ልሰንድ ሞክሬያለሁ፡፡
የዥዋዥዌ ምርቃት እንደ ሌላው ጊዜ በተንጣለለ አዳራሽ የሚቀርብና በቅንጫቢ ንባብ፣ በሙዚቃ እና ሌላ ጨዋታ የተሞላ ዝግጅት አይደለም። ቀለል ያለ የሽያጭና የፊርማ ፕሮግራም ነው። ያስለመድኳችሁን ፓስቲና ሻይ ግን አላስቀርም።
የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 6 ቀን 2018 አዲሱና ሸላዩ የጃፋር መጽሐፍት መደብር
(ለገሃር) እስክትመጡ እናቱን እንደናፈቀ ጨቅላ በር በሩን እያየሁ እጠብቃችኋለሁ።
ከእናንተ የሚጠበቀው ከቀኑ 8 እስከ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ ያመቻችሁን መርጣችሁ ዘው ማለት ብቻ ነው።
ማስታወሻ!
የእኔን ዝግጅቶች ታድመው የሚያውቁ አንባቢዎቼ፣ ካልኩት ሰዓት ዝንፍ ብዬ እንደማላውቅ ምስክር ናቸውና፣ ታረፍዳለች ብላችሁ እንዳታረፍዱ።
በዚህ አጋጣሚ ምንግዜም ለማይለየኝ ድጋፍና ማበረታቻችሁ፣ ስልጡን ትችትና ወቀሳችሁ ምስጋናዬን ውሰዱ፡፡
ህይወት እምሻው-
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:38
“ጤንነቴ” የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ነው
ጤና ሚኒስቴር “ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያን” በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ይፋ አድርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ፤ ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ መሆኑን በመግለጽ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተዘጋጀዉን የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተዋል። ጤና ሚኒስቴር፣ የጤና ስርዓቱን ለማዘመን እያደረገ የሚገኘውን ጥረትም አድንቀዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸዉ፤ ጅምሩ የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት በቴክኖሎጂ ዘመናዊ ለማድረግና ለህብረተሰቡ ትክክለኛ የጤና መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እርምጃ መሆኑን በመግለጽ፣ የመድኃኒት አቅርቦትን ማሻሻልና በጤና ዲጂታይዜሽን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል።
አዲሱ የጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ ዜጎች ስለ መድሃኒት አቅርቦት፣ የጤና አገልግሎቶችና የጤና መረጃን በቀጥታ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ተገልጋዮች እንክብካቤን በፍጥነት እንዲያገኙና አላስፈላጊ ጉዞን እንዲቀንሱ ይረዳል።
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይም በመላ ኢትዮጵያ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጧል። አፕሊኬሽኑ የዲጂታል ጤና ስርዓትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን፤ ለታካሚዎች የታዘዙ መድሃኒቶች የት እንደሚገኙ በቀላሉ መረጃ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
አፕሊኬሽኑ የዲጂታል ጤና ስርዓትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት፣ ለታካሚዎች የታዘዙ መድሃኒቶች የት እንደሚገኙ በቀላሉ መረጃ የሚሰጥበት ነው ተብሏል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:36
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን የያዘ መጽሐፍ ተመረቀ
ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላትን ይዟል
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የያዘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በመዝገበ ቃላቱ የመጀመሪያው ዕትም ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት አቻ ስያሜ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ተነግሯል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር በላይ ካሳ እንዲሁም ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዶ/ር በለጠ ሞላ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መጽሐፉ በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚሄድ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ነው።
ሳይንሳዊ እውቀትን በሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡
Published in
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:35
አፍሪካ ህብረት እየተባባሰ ለመጣው የማሊ ቀውስ ዓለማቀፍ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ
የአፍሪካ ህብረት በማሊ እየተባባሰ የመጣውን የፀጥታና የሰብአዊ ቀውስ ተከትሎ፣ አስቸኳይ አለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት እንዲደረግ ጠይቋል።
አሸባሪ ቡድኖች የነዳጅ አቅርቦቶችን በመዝጋታቸው ሰላማዊ ዜጎችን ለችግር መዳረጋቸው ተነግሯል።
የአፍሪካ ህብረት የንፁሀን ዜጎችን መገደልና የሶስት ግብፃውያንን አፈና አውግዞ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።
የአፍሪካ ህብረት በሳሄል አካባቢ ለሚታየው ሽብርተኝነት የተቀናጀ አለም አቀፍ ምላሽ እንዲሰጥ ግፊት እያደረገ ነው፡፡
የማሊ መንግስትና ህዝብ ለሰላም፣ መረጋጋትና ልማት በሚያደርጉት ትግል ህብረቱ ከጎናቸው ለመቆም ቃል በመግባት አጋርነቱን አረጋግጧል።
Published in
ከአለም ዙሪያ
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:34
የጉራጌ ጦርነት 1867-1881
#በዘመናዊ የጉራጌ ታሪክ የቀቤና ቸሀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በመጀመሪያ የሚጠቀስ ገድል ነው ። ቀቤና በ1850ዎቹ በወልቅጤና በቸሀ መካከል “ ዘናበነር ” በሚባል ቀበሌ ከሰፈረ በኋላ ለቀበሌው የራሱን ስም የሰጠው አንድ የሀዲያ ማኅበረሰብ ነው።
#በ1860ዎቹ የቀቤናው ኢማም ሀሰን ኢንጃሞና የቸሀው ኢማም ኡመር በቅሳ የቀቤና አካባቢያዊ መንግሥት መሠረቱ ከ1860 ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1881 ድረስ የቀቤና መንግሥት መሪዎችና ተከታዮች በጊቤና በአዋሽ ወንዞች መካከል የሚገኙ የሀዲያ የጉራጌና የኦሮሞ ሕዝቦችን በአንድነት ለማደራጀት በወሰዱት ብርቱ የፖሊሲ እርምጃ ከአጐራባቹ የሸዋ አካባቢ መንግሥት ጋር የአስራ አራት (1867-1881) ዓመታት ጦርነት ተዋጉ ።
#በዚህ ረገድ በ1867 መጨረሻ የምኒልክ ጦር በራስ ጐበና አዝማችነት በሶዶ ጉራጌ የመጀመሪያ ጦርነት ከፍቶ በድል ተመለሰ ። ነገር ግን በ1869 በቀቤና ፣ በወለኔ ፤ በገዳባኖ ፤ በአክሊል ፡ በምሁር ፤ በእዣ ፤ በቸ ሀ ፤ በእነሞር ፡ በኤነር ፤ በየጨሬት ፤ በጉመር ፤ በውሪሮ ፤ በስልጤ በመስቃን ፤ በዶቢና በዱላ ላይ በንጉሥ ምኒልክ አዝማችነት ጦርነት የከፈተው ታላቅ የሸዋ ሰራዊት በየአካባቢው በእነ አበጋዝ ደርሰሞ በተመራው የጉራጌ ጦር ተሸንፎ እንደ ተመለሰ በታሪክ ጸሐፊ አጥመ ጊዮር ጊስና በጉራጌ ትውፊት ተመዝግቦአል ። “
#በጉራጌ የትውፊት መረጃ መሠረት ፤ የ1869 የምኒልክ ሠራዊት በአጋዝ ደርሰሞ በተመራው የጉራጌ ጦር የተሸነፈው በጉመር አገር በዌራና በአረቅጥ በተካሄዱ ተከታታይ ጦርነቶች ነው።በታሪክ ጸሐፊ አለቃ አጥመ ጊዮርጊስ ዘገባ መሠረት ፣ በጥቅምት 1869 ንጉሥ ምኒልክ ብዙ ጦር አስከተለው ወደ ጉራጌ ዘመቱ ። በጥቅምት 21 ቀን የንጉሡ ሠራዊት አለቀ።
#አለቃ ዘነብ የሚባል አዋቂ መጽሐፈ ጨወታ የደ ረሰ የዚያኑ ዕለት ሞተ። ብዙ መኳንንት ሞቱ። የቸሀና የጉመር ሌሎችም ጉራጌዎች ብዙን ሠራዊት ማርከው ወደ ከምባታ ወደ ወላሞ ሸጡ። ከንጉሡ ጋራ ከዘመቻው የተመለሰው ከሶስት አንድ እጅ ብቻ ነው። በዚያን ጊዜ በሸዋ ያልተለቀሰበት ቤት አልተገኘም። ንጉሡም በኃዘን ተመልሰው ልቼ ገቡ፡፡
#ከ1867 እስከ 1881 በጉራጌና በሸዋ መካከል በተካሄደው ጦርነት ዋና ዋና የሸዋ ጦር መሪዎችና አዛዦች ንጉሥ ምኒልክ ፣ ራስ ወልዴ አሻግሬ ፤ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያት፤ባላምባራስ መኳንንት ወልደ ሚካኤል (በኋላ ራስ) ፤ ቀኛዝማች ውቤ ኤርገኖ ፤ ደጃዝማች በሻህ አቦዬ፡ ራስ ጐበና ዳጭ ፤ ፊታውራሪ ገረዶ ጐበና ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ነበሩ ።
#ከእነዚህ የጦር መሪዎችና አዛዦች ቀኛዝማች ውቤ ኤርገኖና ፊታ ውራሪ ገረዶ ጐበና በጦርነቱ ሞቱ። የራስ ጐበና ዳጭ ጦር አራት በተለያዩ ጊዜያት በኢማም ሀሰን ኤንጃሞ እጅ ተሸንፎ ተመለሰ ፤ አለቃ አጥመ ጊዮርጊስ እንደ መዘገቡት ፤ በ1877 ቀቤኖች ቀኛዝማች ውቤ ኤርገ ኖን ስለ ገደሉት በ1878 ደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ ፤ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያትና ባላባራስ መኳንን ወልደ ሚካኤል በሌላ የቅጣት ዘመቻ ወደ ቀቤና ተላኩ። በመስከረም 1879 የደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ ወንድም በጦርነቱ እንደ ተገደለና ደጃዝማቹ 3000 ከብቶች በም ርኮ ይዞ ወደ እንጦጦ እንደ ተመለሰ በወቅቱ ሸዋ የነበረው አንድ የውጭ አገር ጸሐፊ መዝግቦአል። የተባለው ጸሐፊ በሰኔ 1880 ጉራ ጌዎች በበኩላቸው ከሸዋ ጦር 400 ጠመንጃዎችን በምርኮ እንደ ወሰዱ ጨምሮ ጽፎአል።
#በ1880-1881 ኢጣሊያኖች ከሰሜን ጠረፍ፣ ሱዳኖች ደግሞ በምዕራብ ከወለጋና ከጐንደር ጠረፎች በአገሪቱ ላይ በአንድ ጊዜ በሶስት ግምባሮች ወረራ በከፈቱ ጊዜ ከጉራጌ ኢማም ሀሰን ኤንጃሞ አዋሽ ተሻግሮ “ ሸዋን ያቃጥላል በማለት ራስ ጐበና ዘምተው እንዲወጉት ተመ ከረ። ራስ ጐበናም ወደ ሀሰን ኢንጃሞ ዘመቱ ” ይህ የጐበና የ1880ው ዘመቻ በጉራጌዎች ላይ አምስተኛው ጦርነት ነበር።
#በመጨረሻ ራስ ጐበና የወሊሶን ተወላጅ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮር ጊስ ዲነግዴን በኢማም ሀሰን ኤንጃሞ ላይ በማዝመት ጦርነቱን በመ ጋቢት 1881 ወደ ፍጻሜው አድርሰው ራሳቸው በሰኔ 1881 በድንገት ታመው በእንጦጦ ሞቱ።
#ከታሪክ አኳያ በ1881 የጉራጌ ጦርነት በሸዋ ድል መፈጸሙ ለምኒልክ ወታደሮችና ሹማምንት በሚቀጥሉት አመታት በደቡብና በምዕራብ ኢሉባቦር ፣ ከፋ ፣ ጋሞጐፋ፣ ሲዳሞና ባሌ ጨምሮ ብዙ አካባቢዎችን በፍጥነት በማዕከላዊ መንግሥት ሥር ለማምጣት በር ከፈተ።
►የኢትዮጵያ የገባር ታሪክና ጅምር ካፒታሊዝም፤ላጲሶ ጌ.ዴሌቦ፤192-4
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Sunday, 09 November 2025 00:00
የጋዛ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ያተኮረ የ2 ቀን ጉባኤ በኢስታንቡል ይካሄዳል
የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታትና ዓለም አቀፍ ወዳጅነትን ለማጠናከር ያለመው ጉባኤ፤ በፈረንጆቹ ህዳር 11 እና 12 ቀን 2025 ይካሄዳል።
ከመላው ዓለም አራት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ይታደሙበታል በተባለው ጉባዔ ፣ የሰብዓዊ መብት ጠበቆች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችና ምሁራን ይገኙበታል።
የጋዛ የወደፊት ዕጣ ፈንታ (the future of Gaza) በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤው፤ በጋዛ አጠቃላይ ገፅታ፣ በተኩስ አቁም ስምምነቱን ቁመና፣ እንዲሁም እርዳታ በሚደርስበት ሁኔታ ላይ ጥልቅ ውይይት የሚደረግበት መሆኑ ተዘግቧል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under

