
Administrator
(አለ) መታደል እና ልብ
የግጥም ጥግ
(አለ) መታደል እና ልብ
ከሕይወት ሎተሪ
በቆረጥሽው እጣ
ያሸነፍሽው ንብረት
ልቤ ሆኖ ወጣ፡፡
… መታደልሽ፡፡
****
ነው ብለው ሰጡኝ ቁልፍ
የልቧ መክፈቻ
ብሞክረው እምቢ አለኝ
ዝጎ እንደሆነ እንጃ፡፡
… አለመታደሌ፡፡
****
የጅብ ችኩል ተረት
በእሷ ደረሰና
ደረት ኪሴ ገባች
ልቤን ተወችና፡፡
… አለመታደሏ፡፡
****
ሥጋዬን እንደጮማ
ከበር አስቀምጬ
ልቧን እንደ መቅደስ
በነፍሴ ረግጬ
በእድሏ ፀናፅል
በልቤ ከበሮ
በፍቅሯ በገና
ሀሴት ተደርድሮ
በገደል ሳይሆን
ያዜምኩላት ዜማ
በሰማይ ማሚቱ
ህዋ ላይ ተሰማ
… መታደላችን!
(ሳምሶን ጌታቸው)
የግጥም ጥግ
(አለ) መታደል እና ልብ
ከሕይወት ሎተሪ
በቆረጥሽው እጣ
ያሸነፍሽው ንብረት
ልቤ ሆኖ ወጣ፡፡
… መታደልሽ፡፡
****
ነው ብለው ሰጡኝ ቁልፍ
የልቧ መክፈቻ
ብሞክረው እምቢ አለኝ
ዝጎ እንደሆነ እንጃ፡፡
… አለመታደሌ፡፡
****
የጅብ ችኩል ተረት
በእሷ ደረሰና
ደረት ኪሴ ገባች
ልቤን ተወችና፡፡
… አለመታደሏ፡፡
****
ሥጋዬን እንደጮማ
ከበር አስቀምጬ
ልቧን እንደ መቅደስ
በነፍሴ ረግጬ
በእድሏ ፀናፅል
በልቤ ከበሮ
በፍቅሯ በገና
ሀሴት ተደርድሮ
በገደል ሳይሆን
ያዜምኩላት ዜማ
በሰማይ ማሚቱ
ህዋ ላይ ተሰማ
… መታደላችን!
(ሳምሶን ጌታቸው
“የአሬራ ጥጋብ የሚመጣውን ክረምት ያስረሳል”
አንድ የአይሁዶች አፈ-ታሪክ አለ፡፡
አንድ ኃይለኛ የመርሳት ችግር የነበረበት አይሁዳዊ ነበር፡፡ ከመርሳቱ ብዛት ማታ አውልቆት የተኛውን ልብስና ጫማ የት እንዳስቀመጠ እንኳ አያስታውስም፡፡ ልብስና ጫማውን ያስቀመጠበትን ቦታ ሲፈልግ ሁልጊዜ የጸሎት ሰዓቱ ይረፍድበታል፡፡ በፀሎት ቦታ የሚሰጠውን የቶራ ትምህርትም ጠዋት ተምሮ ማታ ይረሳዋል፡፡ እሱ ግን ከሌሎች ጓደኞቹ የተሻለ የተረዳው ይመስለዋል፡፡ “የእናንተን እውቀት ማነስ ምንም ላግዘው እንደማልችል ሁሉ፤ የእኔንም አዋቂነት ምንም ላደርገው አልችልም” እያለ ጉራውን ይነዛባቸዋል፡፡
አንድ ቀን ጠዋት ሲነሳ ልብሱን፣ ጫማዉንና ባርሜጣውን የት እንዳደረገው ጨርሶ ስለጠፋው ጠዋቱን በሙሉ እሱኑ ሲፈልግ ዋለ፡፡ ትምህርትም አመለጠው፡፡ በዚህ ምክንያት “ሁለተኛ እንዳልረሳ ዘዴ መፍጠር አለብኝ” ሲል አሰበ፡፡ ይህም ሁሌ ማታ ማታ ሲተኛ የትኛውን ልብሱን የት እንዳስቀመጠ፣ ባርኔጣውን፣ ጫማውን ወዘተ የት እንደሚያደርገው በወረቀት መዝግቦ ሊያስቀምጥ ወሰነ፡፡ በዚህ መሰረት “ኮቴ ከበሩ ጀርባ ነው፣ ሱሪዬ ወንበሩ ላይ ነው” እያለ ሁሉንም ዘርዝሮ መዘገበ፡፡
በመጨረሻም አልጋው ላይ ወጣና እንደቀልድ “እኔ ደሞ አልጋው ላይ ነኝ” ብሎ ፃፈና፣ ከትራሱ ስር አስቀምጦ ተኛ፡፡
ጠዋት ሲነሳ ወረቀቷን አውጥቶ በዝርዝሩ መሰረት ሁሉንም በየቦታው አገኘው፡፡ ከፃፈው ዝርዝር ውስጥ አንድ የመጨረሻ መስመር ግን አለ፤ “እኔ ደሞ አልጋው ላይ ነኝ” ይላል፡፡
አልጋው ላይ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ ሄዶ አየ፡፡ እሱ የለም፡፡ መኝታ ቤቱ ውስጥ በየስርቻ ሳይቀር ዞሮ አየ፡፡ ነገር ግን ራሱን ሊያገኝ አልቻለም፡፡
“እኔ ጠፍቻለሁ ማለት ነው” አለና ከቤቱ ወጥቶ ጮኸ፡፡ “ትላንት ማታ አልጋዬ ላይ መተኛቴንስ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ዛሬ ግን የለሁም!”
ይህን ሲናገር የሰሙ ጎረቤቶቹ፤ “ትክክል ነሃ፡፡ በእርግጥ አልጋህ ላይ የለህም፡፡ ምክንያቱም አንተ እዚህ ከእኛ ጋር ነው ያለኸው፡፡” አሉና ሳቁበት፡፡
“የምለው አልገባችሁም ማለት ነው፡፡ በዝርዝሬ ላይ’ኮ ተጽፌያለሁ” አለና ወረቀቷን አውጥቶ አሳያቸው፡፡
“ጅል አትሁን አንተ ሰው፡፡ አጉል ጭንቀት ውስጥም አትግባ፡፡ ይልቅ ወደ ቤትህ ግባ” አለው አንደኛው ጎረቤቱ፡፡
“ራሴን ሳላገኝማ ወደቤቴ ልገባ አልችልም”
“እያየንህ፣ እያዋራንህ እንዴት ጠፍቻለሁ ትላለህ? መኖርህን እያየን’ኮ ነው” አሉት ሁሉም፡፡ እሱ ግን ሊሰማቸው ፈቃደኛ አልሆነም፡፡
በመጨረሻም አንድ ሰውዬ በጣም ተቆጥቶ፤ “አንተ ደደብ ሰውዬ፤ እዚህ መሆንህንና አለመሆንህን አሁኑኑ አረጋግጥልሀለሁ፡፡” ብሎ በመጥረጊያ ይቆነድደው ጀመር፡፡
“ኧረ በጣም አሳመምከኝ ጎበዝ!” ሲል ጮኸ፡፡
“አሁን ይሰማሀል፤ አይደል?” ሲል ጠየቀው፡፡
“በጣም ይሰማኛል እንጂ”
“የሚያምህ እዚሁ በመሆንህ ነው፡፡ የመታሁትም አንተን በመሆኑ ነው፡፡ አንተኑ ራስህኑ፡፡ አንተ እንዳልከው ግን ጠፍተህ ቢሆን ኖሮ ህመሙ ሊሰማህ አይችልም ነበር፡፡ አይደለም እንዴ?”
“እውነትህን ነው፡፡ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ እንዴት እንዳደረግኸው ባላውቅም እራሴን እንዳገኝ አድርገኸኛል፡፡ ምናልባት እኔ የተሻልኩ ሰው አልሆን ይሆናል፡፡” ሲል ራሱን ዝቅ ማድረግ ጀመረ፡፡ ቀስ በቀስ የማስታወስ ችሎታውም እየተመለሰለት መጣ፡፡
***
ሁሉን ነገር የማውቅ እኔ ነኝ፤ ከማንም ሰው እኔ እሻላለሁ፤ የማለት አባዜ ክፉ እርግማን ነው፡፡ ክፉ መገበዝ ነው፡፡ የማታ ማታ ራስን ጭምር ወደ ማጣት ያመራል፡፡ ራስን ለመፈለግ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡ ጊዜ ከረፈደና ከመሸ በኋላ እራስን ማግኘት ዘበት ይሆናል፡፡ ይህንን መገንዘብ የጉዳዮች ሁሉ ቁልፍ ነው፡፡ ወረቀት በያዘው፣ አዋጅ በደነገገው፣ ፖሊሲ በቀረፀው፣ የትውስታ መዝገብ ቢደረደር፣ ቢገመገም ዋናው ራስ የጠፋ እስኪመስል ድረስ የግራ - መጋባትና የመወነባበድ ጣጣ ውስጥ መግባት አይቀሬ ይሆናል። ትላንት ያሉትን እንዳላሉ መሟገት፣ ትላንት ያመኑበትን በጭራሽ ዛሬ አላውቀውም ብሎ መሸምጠጥ ቀድሞውኑ ራስን ከመገበዝ የሚመነጩ ህፀፆች ናቸው፡፡ ራስን ዋርካ አሳክሎ ማየት መጨረሻው ጉቶ ማከልን መረዳት ይሆናል፡፡ ይህም የታደለና ልቡናውን የሰጠው ሰው ከተገኘ ነው፡፡ እንዲያመው እየተደረገ መኖሩን እንዲያውቅ የሚገደድ ራሱ የጠፋበት ኃላፊ፣ ባለሥልጣን ወይም መሪ ለሀገርና ለህዝብ ችግር እንጂ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ወደዚህ አሰቃቂ ሂደት መድረስም ባንድ ስር እንደተንጠለጠለ ዛፍ የሰቀቀን አፋፍ ላይ መንጠልጠል ይሆናል፡፡
“አድረህ እይ፣ አሳድረህም እይ” እንዲሉ አስቀድሞ ታላቅነትን ከመለፈፍ ይልቅ የራስን ሚዛን ለማወቅ የሚረዳው ለራስ ጊዜ መስጠት ነው፡፡ መብሰል አለመብሰልን በጥሞና መለካት ነው፡፡ የ”አሜን ባይ” መብዛት የትክክልነት ማረጋገጫ አለመሆኑን ማጤን ነው፡፡ እኔ ያወጣሁት መርህ ትክክል ነውና ተቀበል ከማለት በፊት አንተስ ምን ይመስልሃል? ብሎ ለሌላው ሀሳብ እድል መስጠት ብልህነት ነው፡፡ ምናልባት ንጋት ላይ የቀናን መስሎ የታየን ነገር ረፋዱ ላይ ወይ ማምሻው ላይ መለወጥ አለመለወጡን በሚገባ አስተውሎ “ለአንድ ወቅት የሰጠሁት መፍትሄ መልካም ነበር፡፡ አሁን ግን ያ ዘዴ ለዚህኛው ወቅት ላይሆን ይችላል” ብሎ መጠራጠር ያባት ነው፡፡ የትላንት ጣዕም ዛሬ ቃናው መለወጥ አለመለወጡን ማጣራት እጅግ ወሳኝነት አለው፡፡ “ነብር ሲያረጅ አነር ይወልዳል” ይሏልና ከሀሳብ ማርጀት፣ ከፖሊሲ ማርጀት፣ ከፕሮግራም መጣረስ ጋር የሚመጡትን ከሁኔታዎች ጋር የማይጣጣሙ እምነቶች አላየሁም አልሰማሁም ብሎ የዱሮውን ሃሳብ እኝኝ ብሎ መያዝ ተገቢ አይደለም፡፡ አገርና ዓለም ተቀበለውም አልተቀበለውም እኔ ያሰብኩት ጋ ካልደረስኩ ፍሬን አልይዝም - አንዳች የሚያቆመኝ ኃይልም ሊኖር አይችልም ብሎ ግትርነትን ማወጅ፣ ካፈርኩ አይመልሰኝ እንጂ ሌላ ፍሬ የምናፈራበት መላ አይደለም፡፡
የተመኘነው፤ ያለምነው ያቀድነውና የተለምነው ሁሉ ሙሉ በሙሉ ላይሳካ ይችላል ከሚለው እሳቤ ጀምሮ ከመሰረቱስ ሙሉ በሙሉ ስህተት ቢሆን እስከ ማለት ድረስ ለማሰላሰል ዝግጁና ደፋር መሆን ተገቢ ነው፡፡ ያማረውና የተሳካው ሁሉ የእኔ ድካም ፍሬ፣ የተሳሳተውና የተበላሸው ሁሉ የጠላቴ ሴራ ውጤት፤ ብሎ መፈረጅ የኋላ ኋላ ራሱ እንደጠፋበት ሰው መደነጋገርንና በአደባባይ “ራሴን አፋልጉኝ” ማለትን ያስከትላል፡፡
ከቶውንም የሌሎችን ድካም ለራስ ማድረግ ከአንድ ጀንበር በላይ ሊሸሸግ የሚችል ነገር አይደለም። “ያላረባ ልኳንዳ አራጅ ዐይን የሆነውን ብልት ይበላል” እንደሚባለው በሌሎች ጥናት መኩራራት፤ በሌሎች ሪፖርት ላይ ፈርሞ ብቻ መመስገን፤ በሌሎች ጫንቃ የተሰራን ስራ የእኔ ነው ማለት፤ ለሥራም፤ ለእድገትም፣ ለራስም ደግ አይደለም፡፡ አድሮ ያጋልጣልና!
በሲቪል ሰርቪስ መርሆዎች መሻሻል ብቻ መልካም አስተዳደር አይመጣም፡፡ ሰው ይፈልጋል፡፡ መርሆዎችን ከልቡ ሊተገብር የቆመ ሰው ይፈልጋል፡፡ ፍትሕ ርትዕ የሰፈነባት አገርን የሚያመላክት በርካታ አቅጣጫ ሊነደፍ ይችላል፡፡ ግን የወረቀት ስራ ብቻ ነው፡፡ ሰው ይፈልጋል፡፡ በትላንቱ አባያ በሬ አዲስ መሬት ልረስብህ ቢሉት ትርፉ ጅራፍ ማጮህ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ ወደ ባህልነት ሊቀየር አንድ ሀሙስ የቀረው ሙሰኝነት ምንም ያህል የጠበቁ አናቅጽትና ህግጋት ቢጠቀሱለት፤ ተግባራዊ ትርጓሜ የሚሰጣቸው እጁን የታጠበና ልቡን ያፀዳ ሰው ብቻ ነው፡፡
አለበለዚያ “የወረት ውሻ ስሟ ትደነቂያለሽ ነው” ከሚባለው ፈሊጥ የዘለለ ነገር አይገኝም፡፡ በእርግጥም በተጎሰመው ነጋሪት፣ በተላለፈው አዋጅ፣ በብራና በተከተበው ህግና መመሪያ ጥናቱን ያስጠናውን ክፍል ለማስደሰት ይቻላል፡፡ ተግባሩ ግን ከፍተኛ የሰው ኃይልና ልባዊ ህዝባዊ ተሳትፎ እንዲኖር የማድረግን ብርቱ ጥረት የሚጠይቅ ተልዕኮ ነው፡፡ የሃገራችን የዘወትር ህመም፤ ያማረ እቅድና እንከን - አልባ የተባለ የወረቀት ስራ በተነደፈ ቁጥር፤ የተፃፈው ሊቀደድ እንደሚችል የታቀደው ሽባ ሆኖ ሊቀር እንደሚችል ዘንግቶ፣ ከአፍ አፍ እየተቀባበሉ በየመዋቅሩ አሸንዳ የድል ብስራት መለፈፍ፣ ነገ ያለአንዳች ተግባር በነባቤ - ቃልነት ብቻ ሊቀር እንደሚችልና ለከፋ ችግር ሊያጋልጥ እንደሚችል አለመገንዘብና ተዘናግቶ ማዘናጋት ነው፡፡ “የአሬራ ጥጋብ የሚመጣውን ክረምት ያስረሳል” እንደሚባለው መሆኑ ነው!
ኢሰመኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀውን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋዜጣዊ መግለጫ መስከረም 4 ቀን 2016ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፤ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን ሁኔታ የተመለከተ ዓመታዊ ባለ 29 ገጽ ሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው የዘርፍ ሪፖርት፣ ኢሰመኮ ሐምሌ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት ላይ በተጨማሪነት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ላይ በማተኮር የታዩ መልካም እመርታዎች፣ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ አሳሳቢ ጉዳዮችና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል።
ሪፖርቱ ከሰኔ ወር 2014 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን፤ ኮሚሽኑ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ካከናወናቸው የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራዎች፣ጥናቶች፣ የውትወታ ሥራዎች፣ በግለሰቦች ከቀረቡ አቤቱታዎች፣ ከልዩ ልዩ የምክክር መድረኮች ላይ የተገኙ ግብአቶችንና ሌሎች የመረጃ ምንጮችን በማጠናቀር የተዘጋጀ ነው።
በሪፖርት ዘመኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ፣ በባለሦስትና አራት እግር አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ላይ ያሳለፈውን የእገዳ ውሳኔ ተከትሎ፣ የኢሰመኮን ምክረ-ሐሳቦች በመቀበል ለጉዳዩ እልባት መሰጠቱ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ በተደረገው የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት፣ በኮሚሽኑ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አፈጻጸም ላይ በተለይም የዘላቂ መፍትሔ ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን በተመለከተ አበረታች ሥራዎች መከናወናቸውና የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞች መብቶች አተገባበር እየተሻሻለ መምጣቱ በመልካም እመርታነት በሪፖርቱ ተካተዋል።
በተጨማሪም በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ ጉዳት የደረሰባቸውን መሠረተ-ልማቶች መልሶ ለማቋቋም በፌዴራል መንግሥት ይፋ የተደረገው “የመልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፕሮግራም” እና እነዚህን ተቋማት ወደነበሩበት ለመመለስ እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎችም ተጠቃሽ ናቸው።
በሌላ በኩል፣ በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የጸጥታ ችግርና እየናረ የመጣው የኑሮ ውድነትና የዋጋ ግሽበት፣ ሊደረስበት የሚችል ከፍተኛ አካላዊና አእምሯዊ ጤና የማግኘት፣ ትምህርትና መጠለያ የማግኘት፣የመሥራት፣ከሚኖሩበት ቦታ ያላግባብ በኃይል ያለመፈናቀልና ንብረት የማፍራት መብቶችን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደራቸው በአሳሳቢነት ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ናቸው።
በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ከሚያዝያ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የተከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች፣ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ከማድረሳቸውም በላይ ወቅቱ የግብርና ሥራ ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት የነበረ በመሆኑ አርሶ አደሩ ተረጋግቶ የግብርና ሥራውን እንዳይሠራና መደበኛ ሕይወቱን እንዳይመራ አድርጎታል። ግጭቱ ይህ ሪፖርት ይፋ በተደረገበት ወቅትም የቀጠለና እልባት ያልተበጀለት በመሆኑ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሱ መባባሱ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
በኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ በታጣቂዎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች፤የቤት እንስሳትና የንብረት ዝርፊያዎች፣ ቤቶችን የማቃጠልና ነዋሪዎችን በኃይል ማፈናቀልና ቤተ-እምነቶችን ማቃጠል ምክንያት ኅብረተሰቡ በአካባቢው ተረጋግቶ የዕለት ተዕለት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሕይወቱን እንዳይመራ ማድረጉንና በርካታ ሰዎች ያለ መጠለያ እንዲኖሩ፤ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኙና ሕፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዲሆኑ ምክንያት እንደሆነ በሪፖርቱ ተብራርቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጸጥታና ደኅንነት ሥጋት በሚልና በሌሎች ምክንያቶች የንግድና የመኖሪያ ቤቶች በማፍረስ ሂደት ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አካል ጉዳተኞች ሳይቀር የንግድ ቤቶቻቸው ያላግባብ እንዲፈርሱ መደረጉና ንብረታቸው መወሰዱ በገቢያቸውና በኑሯቸው ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።
በኦሮሚያ፣ በሶማሊና በተለያዩ የደቡብና ደቡብ ምዕራብ ክልሎች አካባቢዎች ባለፉት ሦስት ዓመታት ከፍተኛ ድርቅ በመከሰቱ የሕብረተሰቡ መተዳደሪያ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው የቤት እንስሳት ሞተዋል፤ ነዋሪዎችም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።በመንግሥት በኩል ለችግሮቹ መፍትሔ ለማፈላለግ የተለያዩ ሙከራዎች ቢደረጉም የቅድመ መከላከል ሥራ በበቂ ሁኔታ ባለመተግበሩ ችግሩን የከፋ እንዲሆን እንዳደረገው በሪፖርቱ ተጠቁሟል።
የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል፣ በ2015 ዓ.ም. በኮሚሽኑ የቀረቡ ምክረ ሐሳቦችን ከመተግበር ረገድ አበረታች ተግባራት መስተዋላቸውን ገልጸው፤ የትምህርት፣ የጤና፣ ንብረት የማፍራት፣ በቂ በሆነ የኑሮ ደረጃ የመኖር፣ የሥራና ተያያዥ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች እንዲከበሩ የፖሊሲና የሕግ ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁምጠንካራ የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የአርታኢያን ማህበር በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ጉዳይ ላይ ተወያየ
የኢትዮጵያ አርታኢያን ማኀበር (Editors Guild of Ethiopia) 6ኛ ዙር የቁርስ ላይ የውይይት መርሐግብሩን ዛሬ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል አካኺዷል።
የዕለቱ የውይይት መርሐግብር ያተኮረው “ሰብዓዊ መብቶች እና መገናኛ ብዙሃን፤ በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጉዳይ የአርታኢው ሚና (Media and Human Rights: Role of Editors in Protection of Human Rights)” በሚል ርዕሰጉዳይ ላይ ነው። የውይይት መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት ጋዜጠኛ ፍሬው አበበ ናቸው፡፡
አቶ ፍሬው በፅሑፋቸው፣ የሰብዓዊ መብቶች የሰው ልጆች ሰው በመኾናቸው የተጎናጸፏቸው ስለመኾኑ፣ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ህገመንግሥት መሠረታዊ ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን ጭምር ተቀብሎ ማካተቱን በጠንካራ ጎኑ አንስተዋል።
ኾኖም በአፈፃፀም ሒደት የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በተደጋጋሚ የሚያጋጥም ቢኾንም፣ መገናኛ ብዙኃን በችግሩ ስፋት ልክ በቂ ሽፋን እየሰጡ አለመኾኑን በአሳሳቢነቱ አብነቶችን በመጥቀስ አስረድተዋል።
መገናኛ ብዙኃንና አርታኢያን፤ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለባቸው፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን በመደበቅ ለተጠርጣሪ ወንጀለኞች ሽፋን እንዳይሰጡ በብርቱ ሊጠነቀቁ እንደሚገባ፣ ዘገባዎች በሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት እንዳይጠለፉ አስፈላጊው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አመልክተዋል። በርዕሰ ጉዳዩ ላይም በማህበሩ አባላት ሰፋ ያለ ውይይት ተካኺዷል።
የመንግስት መገናኛ ብዙኃን፣ የሰብአዊ መብት ጉዳዮችን የሚያነሱት፣ ከዓለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ኢትዮጵያን የተመለከቱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርት ሲወጣ፣ ምላሽ ወይም ማስተባበያ ለመስጠት ብቻ እንደሆነም በውይይቱ ወቅት ተጠቁሟል፡፡
በመንግሥት ባጀት የሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ የተሻለ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም፣ የሚያወጣቸው ሪፖርቶች በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በቂ ሽፋን እንደማያገኙም በማህበሩ አባላት ተነስቷል፡፡
የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በበላይ አለቆች “የአገር ገጽታ ያበላሻሉ” በሚል ሽፋን እንደማያገኙም ተጠቅሷል - በውይይቱ ወቅት፡፡
ሪፖርተሮችም ሆኑ አርታኢያን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በቁርጠኝነት እንዲዘግቡ ከተፈለገ ከተቋማቸው ዋስትና ሊያገኙ እንደሚገባም ተነስቷል፡፡
በአዲሱ ዓመት ለአገሬ የምመኘው!
መመኘት አልተከለከለም አይደል?
ጊዜው በትክክል ትዝ አይለኝም። ግን የአዲስ ዓመት በዓል ላይ እንደነበር አስታውሳለሁ። አንድ የኢቲቪ ጋዜጠኛ ለአንድ በሥራ ላይ ለነበረ የትራፊክ ፖሊስ ጥያቄ ያቀርብለታል። “የአዲሱ ዓመት ዕቅድህ ምንድነው?” የሚል። ትራፊክ ፖሊሱም ሲመልስ፤ “እኔ እንኳን የግል ዕቅድ የለኝም፤ መ/ቤቴ ዕቅድ ካለው ግን እሱን ለመፈጸም ዝጁ ነኝ” አለ። የእኔም ነገር እንዲሁ ነው የሆነው ዛሬ። የመጀመሪያ ሃሳቤ በራሴ የአዲስ ዓመት ዕቅድ ወይም ምኞት ዙሪያ የሚያጠነጥን ፅሁፍ መከተብ ነበር፡፡ በኋላ ግን የራሴን ትቼ በአዲሱ ዓመት ለአገሬ የምመኘውን ብተነፍስ ወደድኩ። “በመጀመሪያ የመቀመጫየን” አለች - እንደተባለው መሆኑ ነው።
እነሆ አሮጌውን ዓመት አጠናቅቀን አዲሱን (2016) ዓመት ልንቀበል ከ72 ሰዓታት ያነሰ ጊዜ ብቻ ነው የቀረው። እንዳለመታደል ሆኖ 2015 ዓ.ም ከቀደሙት ሁለት ዓመታት የባሰና የከፋ እንጂ የተሻለ ሆኖ አላለፈም። የተሻለ ዓመት ልናደርገው አልቻልንም ቢባል ይሻላል (ለእውነት የቀረበ ነውና!) ለምን ቢሉ? ተጠያቂው ራሳችን ነንና!!
ከሁለት ዓመቱ የህወሃትና የፌደራል መንግስቱ ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ፣ በስንት ፀሎትና በእነ አሜሪካ ተፅዕኖና ግፊት ሳቢያ እፎይ ያልን ቢመስለንም፤ ወዲያው ግን ወደ አዲስ ጦርነት መሸጋገራችን፣ ትልቁ የአገራችን - (የክፍለ ዘመኑ) ትራጄዲ ነው ማለት ይቻላል።
አሁንስ በአማራ ክልል እንደ ዘበት ከገባንበት ጦርነት እንዴት ነው የምንወጣው? እንዴት ነው በዘላቂነት በክልሉ ሰላምና መረጋጋት የምንፈጥረው? አሁንም ለሰላም ድርድር እነ አሜሪካና የአፍሪካ ህብረት መምጣት አለባቸው ማለት ነው? ምክንያቱም በራሳችን መንገድ በውይይትና በድርድር የመፍታት አዝማሚያ በፍፁም እየታየ አይደለም።
በሌላ በኩል አሜሪካ ደግሞ ስስ ብልታችንን ጠንቅቃ አውቃዋለች። (አንዴ ወደ ጦርነት ከገባን፣ በቀላሉ እንደማንወጣ ገብቶታል) ስለዚህም የፕሪቶሪያው የሰላም ድርድር ዓይነት የአጋፋሪነት ሚና ለመውሰድ የቋመጠች ትመስላለች። በእኛ በኩል በማንም አደራዳሪነት ይሁን ዜጎችን በከንቱ ከሚፈጀውና ለሰቆቃ ከሚዳርገው ዘግናኝ ጦርነት ብንወጣና ሰላምና መረጋጋት ቢሰፍን ባልጠላን ነበር። ክፋቱ ግን እነ አሜሪካ የገቡበት ነገር ጣጣው ማብቂያ የለውም፡፡ ሽምግልና ብለው የባሰ ቀውስና ብጥብጥ ፈጥረውም ሊወጡም ይችላሉ፡፡ እነ ኢራቅ… ሊቢያ… አፍጋኒስታን… ሶሪያ… ምን እንደሆኑ አይተናል፡፡
የፈረሱ አገራት ነው የሆኑት። እውነታው ይህን ቢመስልም ቅሉ፣ በራሳችን ጊዜና በራሳችን አቅም ከጦርነቱ ወጥተን ወደ ሰላም ድርድር መግባት እስካልቻልን ድረስ ሌላ አማራጭ አይኖረንም - የአሜሪካና አጋሮቿን የሰላም ድርድር ሃሳብ ከመቀበል ውጭ። (ወደን ሳይሆን ተገደን!) ያኔ ደግሞ አዲስ ወጥመድ ውስጥ ገባን ማለት ነው።
በነገራችን ላይ በአሜሪካ አጋፋሪነት የተካሄደው የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት፣ ጦርነቱን በማቆሙ እፎይ ብንልም፣ የምንከፍለውን ዋጋ (ዕዳችንን) ግን ገና በቅጡ አላወቅነውም። (Free Lunch የሚባል ነገር የለማ!) እናም በጦርነት መፍትሄ እንደማይመጣ እያወቅን፣ በማያዋጣ መንገድ ከመባከን የሰላምን አማራጭ መውሰድ ብልህነት ይመስለኛል። ወደድንም ጠላንም ከጦርነትና እርስ በርስ ከመጠፋፋት አዙሪት ወጥተን፤ ወደ ሰላማዊ ውይይትና ድርድር መግባት ይኖርብናል - በእነ አሜሪካ ሳይሆን በራሳችን መንገድ።
የፖለቲካ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት የመፍታት ባህል በአንድ ጀንበር እንደማይመጣ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ግን በሂደት ባህል ይሆን ዘንድ ዛሬ መጀመር አለበት፡፡ ጨክነንና ቆርጠን ዛሬ - አሁኑኑ ልንጀምረው ይገባናል። ከዛም የሁልጊዜ ልምምዳችን ማድረግ፡፡ በትጋትና በፅናት ከቀጠልንበት፤ ያለጥርጥር በሂደት ባህል እናደርገዋለን፡፡ ከዚህ ውጭ ደግሞ ሌላ መፍትሄ የለንም። በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚነሱ ችግሮችና አለመግባባቶች ሁሉ ጦር እየሰበቅን፤ የጦርት ነጋሪት እየጎሰምን መቀጠል አንችልም። እውነት ለመናገር አቅሙ የለንም። የአገሪቱ ወገብ ተሰብሯል። ህዘቡ በጦርነትና ተያያዥ መከራዎች ጫንቃው ጎብጧል። ተጨማሪ ጦርነትም ሆነ ግጭት የመቋቋም አቅሙም ሆነ ችሎታው ጨርሶ የለንም!! እንደ አገር መፍረስ ካልፈለግን በስተቀር እስቲ ከሁለት ቀናት በኋላ በምንቀበለው አዲስ ዓመት ለአገሬ የምመኘውን ልነቁጥ እነሆ፡-
በየትኛውም የአገሪቱ አካባቢ የጦርነትና ግጭት ወሬ የማንሰማበት፤
የዜጎች ግድያና መፈናቀል፤ እንግልትና ሰቆቃ በዘላቂነት የሚያከትምበት፤
ፖለቲከኞችም ይሁኑ አክቲቪስቶች ጦርነትና ብጥብጥ የሚያነሳሱ ተንኳሽ ቃላትን መወራወር በህግ የሚከለከሉበት፤
ዜጎች በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተዘዋውረውና ሰርተው የመኖር ህገመንግስታዊ መብታቸው የሚረጋገጥበት፤
የሰብአዊ መብቶች የሚከበሩበትና የህግ የበላይነት የሚረጋገጥበት፤
የፖለቲካ ልዩነቶችን በሃይል አማራጭ ሳይሆን በውይይትና በድርድር የመፍታት ልምምድ የሚጀመርበት፤
ለኢኮኖሚ ስብራቶቻችንንና ለማህበራዊ ቀውሶቻችን ልሂቃኖቻችን ተግባራዊ መፍትሄ የሚያፈልቁበት ዜጎች በሰላም ከቤታቸው ወጥተው በታጣቂዎች የማይታገቱበት፤ ዘመን እንዲሆን እሻለሁ።
2016 ዓ.ም የሰላምና መረጋጋት፤ የፍቅርና አንድነት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ!!
ቅድም እንደጠቀስኩት ለአዲሱ ዓመት የራሴ ዕቅድና ምኞት ስለሌለኝ ሳይሆን አገራችንና ህዝባችን ተራራ የሚያህል ችግርና መከራ ተጋፍጠው የግል ጉዳይን ማንሳት ቅንጦት መስሎ ስለታየኝ ነው። በእርግጥም በውዱ ጋዜጣ ቦታ ላይ ያለውም በዚህ ክፉ ጊዜ ስለግል የአዲስ ዓመት ዕቅድና ምኞት ቅንጦት ነው የሚሆነው። ስለዚህም ተዘርዝሮ ከማያልቀው የአገራን አያሌ ችግሮችና መከራዎች መካከል አንገብጋቢዎቹን እያነሳሁ፤ በአዲሱ ዓመት እንዴት እንዲለወጥልን እንደምሻ ወይም እንደምመኝ የበዓል ሃሳቤን ልገልፅ እወዳለሁ።
በመጪው ህዳር ወር “አጋርነት ለዘላቂ የፊልም ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የፊልም ፌስቲቫል ይካሄዳል
ሊንኬጅ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ማዕከልና የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች ድርጅት፣ በመጪው ህዳር ወር፣ የፊልም ፌስቲቫል በትብብር እንደሚያካሂዱ ተገለጸ።
“አጋርነት ለዘላቂ የፊልም ዕድገት” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የፊልም ፌስቲቫል፤ ከህዳር 23 እስከ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ለ8 ቀናት፣ በልዩ ልዩ ኹነቶች እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
የፊልም ፌስቲቫሉንና በመንግስት አካላትና በግል ድርጅት የተፈጠረውን አጋርነት አስመልክቶ አዘጋጆቹ ከትላንት በስቲያ ሃሙስ፣ በአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሊንኬጅ የኪነጥበብ ስራዎች ማዕከልና የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት፣ የፊልም ፌስቲቫል በትብብር ለማዘጋጀት የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸው የተጠቀሰ ሲሆን፤ የዚህ አጋርነት ዋነኛ ዓላማው የኢትዮጵያን የፊልም ዘርፍ ወደ ኢንዱስትሪ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ማገዝ መሆኑ ተብራርቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር የጋራ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥና ለአገራዊ የገፅ ግንባታ ወሳኝ ሚና እንዲኖረው ዓላማን ያደረገ ነው ተብሏል - አጋርነቱ፡፡
“ይህ አጋርነት ከሚኖሩት ዘርፈ ብዙ ክንውኖች አንዱ፣ በ2016 ዓ.ም ተግባራዊ የሚደረገውን 18ኛውን የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (ኧርዞፕያ)ንና የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቱን የፊልም ፊስቲቫልን በድምር ይመለከታል፡፡” ብለዋል - አዘጋጆቹ በመግለጫቸው፡፡
በመጪው አዲስ ዓመት በኢትዮጵያ ፊልም መታየት ከጀመረ 100ኛ ዓመት መሙላቱ ደግሞ ለፊልም ፌስቲቫሉ እራሱን የቻለ ድምቀትና አስተዋፅኦ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ የፊልም ፌስቲቫሉን በትብብር ለማዘጋጀት የመንግስት አካላትና የግል ድርጅት የፈጠሩት ይህ አጋርነት በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን እንደማይቀር የገለጹ አስተያየት ሰጪዎች፤ መሰል አጋርነቶች መቀጠላቸው ለኪነጥበቡ እድገት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ተናግረዋል፡፡
የአውዳመት ምሣ - በሙዳይ በጎ አድራጎት
• ድርጅቱ ለቤት ኪራይ ብቻ በወር 250ሺ ብር እያወጣ ነው ተባለ
• ከአስተዳደሩ ቦታ ቢሰጠውም በፋይናንስ እጥረት ግንባታ አልጀመረም
ሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት እንደወትሮው ቢሆን ኖሮ፣ ለሚደግፋቸው ከ1ሺ100 በላይ ችግረኛ ወገኖች ለዓመት በዓል ዱቄትና ዘይት እንዲሁም የበሬ ቅርጫ የመሳሰሉ የአውዳመት ፍጆታዎችን በያሉበት ያከፋፍላቸው ነበር፡፡ ዘንድሮ ግን በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ የተለመደውን ችሮታ ማድረግ አለመቻላቸውን የበጎ አድራጎት ድርጅቱ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ ይናገራሉ፡፡
ይህን ችግራቸውን ያማከሩት ጋዜጠኛ ተሻለ ጣሰው፣ በመጨረሻ ሰዓት፣ በሬ ገዝቶና ሙሉ ወጪውን ችሎ፣ አዲስ ዓመትን ከ100 በላይ ከሚሆኑ ተረጂ ወገኖች ጋር ምሳ እየበላን በደስታ እንድናሳልፍ አድርጎናል ሲሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የድርጅቱ መሥራች ይህን የተናገሩት፣ በዛሬው ዕለት፣ ኮተቤ በሚገኘው የሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት ግቢ ውስጥ ተረጂ ወገኖችን ምሣ የማብላት ሥነስርዓት ከተከናወነ በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው፡፡
የበጎ አድራጎት ሥራ ከጀመረ 23 ዓመታትን ያስቆጠረው ሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት፤ በአሁኑ ወቅት ከ1ሺ100 በላይ ለሚሆኑ ችግረኛ ወገኖች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 650 ያህሉ ህጻናት መሆናቸው ታውቋል፡፡
ድርጅቱ የራሱ የሆነ ማዕከል ስለሌለው ለሚደግፋቸው ወገኖች የቤት ኪራይ ብቻ በወር 250ሺ ብር እንደሚያወጣ መሥራቿ ይናገራሉ፡፡ ይህን ችግራቸውን የተረዳው የአዲስ አበባ አስተዳደር ታዲያ ዝም አላላቸውም፡፡ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማና በሃያት አካባቢ በአጠቃላይ 4ሺ ካሬ ቦታ እንደሰጣቸው ገልጸዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር ቦታውን መስጠት ብቻ ሳይሆን ግንባታውንም ለማከናወን በወቅቱ ቃል መግባቱን ነው ወ/ሮ ሙዳይ የሚናገሩት፡፡ ሆኖም አስካሁን ግንባታው ባለመጀመሩ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገናል ብለዋል፡፡
የራሳችንን ማዕከል በፍጥነት መገንባት ብንችል ቢያንስ የቤት ኪራይ ወጪያችንን በመቀነስ ለተጨማሪ ችግረኛ ወገኖች መድረስ እንችል ነበር ያሉት ወ/ሮ ሙዳይ፤ ኢትዮጵያውያን ከአንድ ምስማር ጀምሮ የአቅማቸውን በማዋጣት ግንባታውን እውን ያደርጉላቸው ዘንድ ተማጽነዋል፡፡
“ሙዳይ በጎ አድራጎት ከ1ሺ100 በላይ ተረጂ ወገኖችን ቤት ተከራይቶና ቀለብ ቆርጦ እንዴት ነው የሚያኖረው?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ወ/ሮ ሙዳይ ሲመልሱ፤ የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን ለአገር ውስጥና ለውጭ በማቅረብ እንዲሁም በከብት እርባታ ላይ በመሰማራት ከሚያገኙት ገቢ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በተለይ “ሙዳይ እንጀራ” በከተማዋ እንደሚታወቅ የጠቆሙት ወ/ሮ ሙዳይ፤ ይሄ ሥራ ከ1ሺ በላይ ለሚሆኑ እናቶችም የሥራ ዕድል መፍጠሩን አክለው ገልጸዋል፡፡
አቅሙ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በወር 500 ብር ስፖንሰር በማድረግ አንድ ልጅ ማሳደግ እንደሚችሉ የጠቆሙት የበጎ አድራጎት መሥራቿ፤ በ9923 አጭር መልዕክት ሙዳይን እንዲደግፉም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ያለምንም ተጨማሪ ክፍያ በ9923 አጭር መልዕክት ድርጅቱ ድጋፍ እንዲያገኝ በማድረጉም ምስጋቸውን ያቀረቡት ወ/ሮ ሙዳይ ምትኩ፤አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ያሰራውን የህጻናት ማቆያ ማዕከል አስመረቀ
2015 እንዴት አለፈ? ግጭት፣ ጦርነት፣ ቀውስ፣ ሞትና መፈናቀል የነገሰበት ዓመት
ሊጠናቀቅ ቀናት የቀሩት 2015 ዓ.ም ለኢትዮጵያውያን እጅግ የከፋ ዓመት ነበር። ዓመቱ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ግጭት፣ ጦርነት፣ ሞትና መፈናቀል ተባብሶ የቀጠለበት፣ በርካቶች ለብዙ መከራና ሰቆቃ የተዳረጉበት፤ ፈታኝ ዘመን ነበር፡፡
በዚህ ዘገባ በ2015 ዓ.ም በአገራችን በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊና ሃይማኖታዊ እንዲሁም በኪነጥበቡ ዘርፍ የተከናወኑ አንኳር ጉዳዮች እንዳስሳለን፡፡
በፖለቲካው ዘርፍ
የህውሃት ታጣቂ ሃይሎች በመከላከያ ሃይሉ ላይ ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም በፈፀሙት ጥቃት ሳቢያ በመንግስት የመከላከያ ሰራዊትና በህውሃት ሃይሎች መካከል የተጀመረው ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲያበቃና የህውሃት ሃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ሁለቱ አካላት በደቡብ አፍሪካው ፕሪቶሪያ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከስምምነት ላይ ደረሱ፡፡ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው ስምምነት ለ2ዓመት የዘለቀውን ጦርነት ለማስቆም ቢችልም ስምምነቱ በአግባቡ ተግባራዊ የተለያዩ የተቃውሞ ድምፆች ሲሰሙ ሰንብተዋል። የስምምነቱ ዋንኛ አካል የሆነው የህውሃት ታጣቂ ሃይሎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ተግባር ሲያወዛግብ ቆይቶ ከወራት በኋላ ታጣቂ ሃይሉ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ለመንግስት ማስረከቡ ተገለፀ፡፡ ከዚሁ በማስቀጠልም ክልሉን በጊዜያዊነት ሲያስተዳድር ከነበረው የፌደራል መንግስት ስልጣኑን የሚረከብ አካል ለመምረጥ የህውሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ አርብ መጋቢት
8 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ምርጫ፣ አቶ ጌታችው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጣቸው። ሆኖም ክልሉን የመምራት ሃላፊነቱ ለአቶ ጌታቸው ረዳ አልጋ ባልጋ አልሆነላቸውም። ርእሰ መስተዳደሩ ከሰሞኑ በሰጡ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ክልሉን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳይችሉ የሚያደርጉ በርካታ ፈተናዎች እንደገጠሟቸው ጠቁመው፤ ከህውሃት አመራሮች መካከል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ የሚታትሩ መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ በወረዳዎችና በታችኛው እርከን ያሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮች የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል እንዳይሆኑ የተደራጀ ንቅናቄ እንዳለም ተናግረዋል ይህ በእንዲህ እንዳለም በትግይ ክልል የተንሰራፋውን ጭቆናና የአንድ ፓርቲ ስርዓትን እታገላለሁ የሚል “ትንሳኤ 70 እንዳርታ (ትስአፓ)” የተባለ ክልላዊ ፓርቲ መስራች ጉባኤውን በአዲስ አበባ ከተማ አካይዷል፡፡ ፓርቲው በክልሉ “ህብረ ብሔራዊ ስርዓት” እንዲፈጠር እንደሚታገልና ይህ ካልሆነ ግን የራሱን ክልላዊ መንግስትም እንደሚመሰርት አስታውቋል፡፡
ከትግራይ ክልል ሳንወጣ በክልሉ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም የተደረገውና በክልሉ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ 3 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተጠርቶ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ተበትኗል፡፡
“የትግይ ህዝብ ስቃይ አላበቃም” በማለት ሰልፍ ወጥተው የነበሩ የትግራይ ክልል ወጣቶች፤ በክልሉ የፀጥታ ሃይሎች እንዲበተኑ መደረጋቸውን ከቀናት በፊት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ሰሜን ሁሉ ደቡባዊው የአገሪቱ ክፍልም በፖለቲካ ውዝግብ በተቃውሞና በግጭት ነበር አመቱን ያሳለፋው፡፡ 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ህገመንግስት ከተጠቀሱት ዘጠኝ ክልሎች መካከል የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ህልውናው በይፋ ያከተመበት አመት ነው፡፡
ለሁለት አስርት አመታት በዚህ ስም ሲጠራ የኖረው ክልል፣ በአራት ክልሎች እንዲዋቀርም ጸደርጓል፡፡ ከክልሉ ቀድሞ የወጣው የሲዳማ ክልል ነበር፡፡ በመቀጠልም የደቡብ ምእራብ ህዝቦች ክልል በተመሳሳይ አዲስ ክልል ሆኖ ተቋቁሟል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ደግሞ ሶስተኛው ደቡቡ ኢትዮጵያ ክልል የተመሰረተ ሲሆን፤ አራተኛው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆኖ ተዋቅሯል፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ የተመሰረቱት ክልሎች በውስጣቸው የየራሳቸውን ክልል ለማቋቋም ጥያቄ ያቀረቡ የተለያዩ ብሄሮችን የያዙ በመሆናቸው ጉዳዩ ማቆሚያ እንደሌለው የፖለቲካ ምሁራን ይናገራሉ፡፡
አገሪቱ ብሄር ተኮር ፌደራሊዝም እስከተከተለች ድረስ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ከግምት ውስጥ በማስገባት የክልልነት ጥያቄው አይቀሬ እንደሆነም ይገልጻሉ፡፡
2015 ዓ.ም በአማራ ክልልም በተከሰተው ግጭትና ጦርነት ሳቢያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህይወት የጠፋበትና ዓመት ሆኗል። አመቱ በተለይ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ግጭትና ጦርነት ተቀስቅሶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንፁሃንን ለሞት የዳረገ ሆኗል፡፡
በክልሎች ስር ተዋቅረው የሚገኙት ልዩ ሃይሎች እንዲፈርሱና በፌደራል የፀጥታ መዋቅር ውስጥ እንዲካተቱ የተወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገውን ሙከራ ባልተቀበሉ ወገኖችና በመንግስት መካከል ላለፉት 5 ወራት ከባድ ጦርነት ሲደረግ ቆይቷል፡፡
ግጭቱ የተባባሰው ሚያዝያ 19 ቀን 2015 ዓ.ም የገዥው ብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በታጣቂዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነበር፡፡ በሰሜን ሸዋ መሃል ሜዳ የተጀመረው ግጭት ተቀጣጥሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመድረሱ በሰሜን ጎንደር በደብረማርቆስ፣ በፍኖተሰላም በሰሜን ወሎና በሰሜን ሸዋ ዞኖች አንዳንድ አካባቢዎች በመከላከያ ሰራዊትና በታጣቂዎች መካከል ግጭት ተካሂዷል በዚህም በርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ ነው ያለው ግጭትና ጦርነት በሲቪል ሰዎች ላይ የሞት የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሷል ብሏል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል ተባብሶ በቀጠለው ጦርነት ሳቢያም የትራንስፖርት አገልግሎት ተቋርጦ የቆየ ሲሆን የመንግስት ቢሮዎችም ለአገልግሎት ዝግ ሆነው ሰንብተው ነበር። ክልሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር እንደሆነ ከተወሰነበት ሐምሌ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ አንፃራዊ መረጋጋት ቢኖርም ዛሬም ድረስ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ውጥረት መንገሱንና ዛሬም ድረስ ግጭቶች መኖራቸውን ምንጮች ይገልፃሉ፡፡ ክልሉን እጅግ ለበዛ ችግርና መከራ የዳረገው የሰላም እጦት በቀጣይም አመት እንዳይከተለው ይሰጋል።
አሮጌውን ዓመት በግጭትና በሰላም እጦት ያሳለፉት የአዲስ አበባና ዙሪያዋ አካባቢ ከተሞችም ከግጭትና አለመረጋጋት አላመለጡም። በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳቱ አቶ ሺመልስ አብዲሳ “በኦሮሚያ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ” ነው በተባለለት የሸገር ከተማ ምስረታ ሳቢያ በተቀሰቀሱ ግጭቶች በርካታ ንፁሃን ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ አምስት ከተሞችን በመያዝ በ12 ክፍለ ከተሞች በኦሮሚያ ክልል ስር የካቲት 19 ቀን 2015 የተመሰረተችው የሸገር ከተማ ለአመታት ጎጆ ቀልሰው ልጆች ወልደው ኑሮአቸውን የመሰረቱ በርካቶችን አፈናቅላለች። የከተማ አስተዳደሩ “ያለ ፕላንና ህጋዊነት ተሰርተዋል” ያላቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችንና የእምነት ተቋማትን አፍርሷል። ከዚህ ከከተማው ቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ 100 ሺ አቤቱታዎችን መቀበሉን የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ገልጿል፡፡
አስተዳደሩ ህገወጥ ናቸው እያለ ለሚያፈርሳቸው የመኖሪያ ቤቶች ምትክ ቦታ አለመስጠቱንና ለተፈናቃዮችም ጊዜያዊ መጠለያ አለማዘጋጀቱንም ተቋሙ ገልፆ ነበር፡፡ ያለፕላንና ህጋዊነት ተሰርተዋል ተብለው በከተማ አስተዳደሩ 22 መስጊዶችም መፍረሳቸውንም የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ላይ ገልጿል።
ሌላው የአመቱ አስገራሚ ክስተት በአገሪቱ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ዋንኛ የሚባለው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የአመራሮችና አባላቱ ከፓርቲው መልቀቅና የፓርቲው መዳከም ነው፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ የሺዋስ አሰፋንና ለኢዜማ መሪነት ከፕሮፊሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ተወዳድረው የነበሩትን አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በርካታ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ኢዜማን ለቀው መውጣታቸውን ይፋ ያደረጉት በዚህ አመት ሚያዝያ ወር ላይ ነበር ይሁን እንጂ የእነዚህ ጎምቱ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ከፓርቲው መልቀቅ ፓርቲውን ለመሰንጠቅ እንደማይዳርገው በቀሪዎቹ የፓርቲው አመራሮች መግለጻቸው ይታወሳል።
በማህበራዊ ጉዳዮች
አብዛኛው በአመቱ ያሳለፍናቸው ማህበራዊ ችግሮች የፖለቲካ ቀውሱን ተከትለው የመጡ ችግሮች ናቸው የሚሉት የፖለቲካ ምሁራን ህዝቡን ለተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች የዳረጉት የመልካም አስተዳደር ችግር፣ ግጭትና መፈናቀሎች እንደሆነ ይገልጻሉ። ችግሮቹም ፖለቲካዊ መፍትሄዎች የሚሹ መሆናቸውንም ምሁራኑ ይገልጻሉ። ለዜጎች መፈናቀል፣ ስደትና ሞት መነሻ የሚሆኑ ችግሮች በጊዜው መፍትሄ ካላገኙ ማህበራዊ ቀውሶችን ማስከተላቸው አይቀሬ መሆኑን የሚገልፁት የፖለቲካ ምሁሩ አቶ ታረቀኝ ደጀኔ በአገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረጉ ህጋዊነትን የማስጠበቅ ህገወጥ ድርጊቶች ዜጎችን ለከፋ ችግር የዳረጉ ናቸው ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ስር በተመሰረተው አዲሱ የሸገር ከተማ አስተዳደር የተፈፀመው ቤቶችን የማፍረስና ዜጎችን በግዳጅ የማንሳት እርምጃ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነውም ብለዋል፡፡ የቤት ማፍረሱ ተግባር ተገቢ እይታ ያልተደረገበት ህጋዊነትን ያልተከተለ ያለበቂ ማስጠንቀቂያ የተከናወነ አድሏዊ እርምጃ መሆኑንና ይህም ከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ ያስከተለ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
እገታ
ባሳለፍነው አመት በተለይ በማህበራዊ ሚዲያው መነጋገሪያ አጀንዳ ሆነው ከዘለቁ ጉዳዮች መካከል አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ የእገታ ተግባራት ይገኙበታል፡፡
ይኸው ከቤት ሰራተኞች ጀምሮ እስከ ታጣቂዎች ድረስ ለገንዘብ ሲባል የሚፈፀመው ሰዎችን ማገት በርካቶችን ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምስቅልቅል ዳርጓል፡፡ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከጥቂት ሺ ብሮች ጀምሮ እስከ ሚሊዮኖች ድረስ መክፈል የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከገጠር አካባቢዎች ወደ ከተሞች አድማሱን ያሰፋው የእገታ ተግባር የሁሉም አካባቢ ህዝብ ዋንኛ የስጋት ምንጭ ሆኖ ከርሟል፡፡ ይሁን እንጂ ስለዚህ አሳሳቢ ጉዳይ የፌደራል መንግስቱም ሆነ ድርጊቱ በተደጋጋሚ የሚፈፀምባቸው ክልል አስተዳዳሪዎች ምንም ያሉት ነገር የለም፡፡
በሃይማኖት ተቋማት ዘርፍ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዕውቅናና ከቤተክርስቲያኒቱ ስርዓትና ቀኖና ውጪ ጥር 14/2015 በተደረገ ህገ-ወጥ የጵጵስና ሹመት የተሾሙ 26 ጳጳሳትን ሹመት በመቃወም ቤተክርስቲያኒቱ ባወጣችው መግለጫና ለምህመናኑ ባቀረበችው ጥሪ መሰረት በአገሪቱ ከፍተኛ ተቋውሞ ተቀስቅሶ ነበር፡፡ በዚህ ተቃውሞም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ንፁሃን ዜጎች ተገድለዋል ይህንኑ የቤተክርስቲያኒቱን ጥሩ የተቀበሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች የካቲት 5/2015 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ሊያደርጉ የነበረውን ታላቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በመንግስት ጣልቃገብነት እንዲሰረዝ የተደረገ ሲሆን ህገ-ወጡ የጳጳሳት ሹመትና የሲኖዶስ ምስረታ እንዲታገድም ተደርጓል፡፡
ይህ ችግር በቅጡ ባልተቋጨበት ሁኔታ በቅርቡ ደግሞ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ፣ የትግራይ ቤተክህነት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ጋር ያለውን ግኑኝነት በማቋረጥ በመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ቤተክህነትን መመስረቱን አስታውቆ፤ ዘጠኝ ጳጳሳትን ሾሟል፡፡ ይህንን ሹመት ተከትሎም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “ህገ-ወጥ ነው” ያለውን የጳጳሳት ሹመት ተቃውሞ አውግዟል፡፡ በእነዚህ ተደጋጋሚ የቤተክርስቲያኒቷን ስርዓትና ቀኖና የሚጥሱ ተግባራት ሳቢያ ያሳለፈፍነው አመት የውጥረትና የግጭት ዓመት ሆኖ አልፏል፡፡
ከሸገር ከተማ ምስረታ ጋር በተያያዙ የፈረሱት 22 መስጊዶች ባሳለፍነው አመት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎችና በእምነቱ ተከታዮች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት ከሆኑ ጉዳዮች መካከል ዋንኛው ሆኖ ይገለፃል፡፡ ባለፈው ግንቦት ወር በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ውስጥ ከተከናወነው የመስጊድ ፈረሳ ጋር በተያያዘ ድርጊቱን የተቃወሙ የእስልምና እምነት ተከታዮች በታላቁ አንዋር መስጊድ ተቃውሞአቸውን ባሰሙበት ወቅት ከመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ጋር በተቀሰቀሰ ግጭት ንፁሃን መገደላቸው ይታወሳል፡፡ ተቃውሞው በየሳምንቱ ቀጥሎ በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ለሞት ለእስርና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸውም ተዘግቧል።
ከሁለት ቀናት በኋላ የሚጠናቀቀውን 2015 ዓ.ም ከጦርነትና ግጭት፣ ከሞትና ሰቆቃ ውጭ እንዲታወስ የሚያደርጉ ብቸኛ ምክንያቶች ጀግኖቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ናቸው። አገር በጦርነትና መከራ እየታመሰችም ሰንደቃችን በዓለም አደባባይ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርገውልናል።