Administrator

Administrator

በፕርሽያ የህክምና ሙያና ጥናት ረዥምና የዳበረ ታሪካ ያለው ነው፡፡ የጥንት ኢራናውያን መድሀኒቶች ከሜሴፖታሚያ፤ ከግብጽ፤ ከቻይናና፤ ከግሪክ የህክምና ባህሎች የተወጣጣ ሲሆን ይሄ ከአራት ሺ አመታት በላይ ሲዳብር የነበረ እውቀትና የህክምና ሙያ ነው  በ13ኛው ክፍለ ዘመን ለአውሮፓ  የህክምና ሙያ መሰረት የሆነው።
ጁንዲሻፑር ዩኒቨርስቲን (3ኛው ክ/ዘመን ኤዲ) የመሳሰሉ የኢራን የትምህርት ማዕከሎች፣ ከተለያዩ ሥልጣኔዎች የወጡ ታላላቅ ሳይንቲስቶች መፈልፈያ ነበሩ፡፡
የኢራን የህክምና ባለሙያዎች፣በታላቁ የእስልምና ሥልጣኔ ወቅት፣ በህክምና ሳይንስ ለተመዘገበው ዕድገት ትልቅ ድርሻ ነበራቸው፡፡ በመካከለኛውና ቅርብ ምስራቅ የመድሃኒት ቅመማና ሥርጭትን ጨምሮ የህክምና ሳይንስ ወደ ጥንት የሜሶፖታሚያ ዘመን የሚዘልቅ ረዥም ታሪክ አለው ፡፡
 ኢራን ማናቸውንም ዓይነት የጤና ክብካቤ አገልግሎቶች በማቅረብ ከሚጠቀሱ የዓለማችን ምርጥ አገራት አንዷ ናት፡፡ ግሩም የጤና መሰረተ ልማቶችና አገልግሎቶች አሏት፤ ዓለማቀፍ መስፈርቶችን የሚያሟሉ፡፡ በላቀ ደረጃ የተማሩና የሠለጠኑ የህክምና ባለሙያዎች አፍርታለች፡፡ ከምዕራባውያንና ምስራቅ አገራት አንጻር የህክምና አገልግሎት ክፍያ በእጅጉ ተመጣጣኝ ነው፡፡ ለዚህም ነው የላቀ ጥራት ያለው የጤና ክብካቤ አገልግሎት ወይም የቀዶ ጥገና ሕክምና የሚፈለጉ ህመምተኞችና ቱሪስቶች የትኩረት ማዕከል የሆነችው፡፡
የህክምና ቱሪዝም በኢራን
የህክምና ቱሪዝም ወይም የህክምና ጉዞ (ሜድ ቱር)፤ የኢራን የህክምና ቱሪዝምን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና ከተጫወቱ ዘርፎች አንዱ ሲሆን  እያንዳንዱን የሰው ልጅ ህይወት ትናንሽ ክፍል ያካትታል፡፡ ይህን ዕድገት በተጨባጭ ለማየት ወደ ኢራን ተጓዙ፡፡ በርግጥ የህክምና ጉዞ (med tour) ሰፊ ጽንሰ ሃሳብ ነው፡፡ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው እያንዳንዱን የህብረተሰብ ክፍል የሚነካ ነው፡፡
የህክምና ቱሪዝም ባለው ዕምቅ አቅምና ተነፃፃሪ ብልጫ የተነሳ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል፡፡ የህክምና ቱሪዝም፤ ከነዳጅ ኢንዱስትሪው (oil industry) እና አውቶሞቢል ኢንዱስትሪው በመቀጠል በዓለም 3ኛው ትልቁ ኢንዱስትሪ ነው፡፡ በአገሪቱ  የውጭ ምንዛሬ ግኝት ላይ ትርጉም ያለው አዎንታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሲሆን በቅርቡ ያለ ጥርጥር የዓለማችን ቁጥር 1 ትልቁ ኢንዱስትሪ ይሆናል፡፡
ኢራንን እንደ ህክምና ቱሪዝም መዳረሻነት ለመምረጥም ሆነ ወደ ኢራን ለመጓዥ ብዙ ምክንያቶች አሉ፤ አስደማሚ ችሎታ ካላቸው የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች እስከ ግሩም የደንበኛ አገልግሎት እንዲሁም ከዝቅተኛ የህክምና ክፍያ እስከ የኢራን ከተሞች ውብ መስብህ ድረስ የሚዘልቅ፡፡
በአነስተኛ ወጪ ህክምና ለማግኘት ወደ ኢራን ተጓዙ፡፡ ዝቅተኛ የህክምና ክፍያ፣ ከኢራን የህክምና ቱሪዝም ጥቅሞች አንዱ ነው፡፡
የኢራን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ሰፊ ነው፡፡ በርካታ የህክምና ቱር ኩባንያዎች አሉ፡፡ አሊያም እንደ ታላቁ ዛንጃኒስ ያሉ ሆቴሎች አሉ፡፡ አንዱ የዛንጃን ሆቴል ለምሳሌ በህክምና ቱር ረገድ ሊረዳችሁ ዝግጁ ነው፡፡
ኢራን በህክምና ቱሪዝም ኢንዱስትሪው በእጅጉ አድርጋለች፡፡ የጤና ቱሪዝም በይፋ የተጀመረው እ.ኤ.አ ከ2003 አንስቶ ቢሆንም፤ ዘርፉ በዓይን ቀዶ ህክምና፣ በካንሰር፣ በውስጥ አካላት ቅድመ ተከላ፣በዓይን ህመም ፈውስ በፊትም ይታወቃል፡፡ በተዋጣላቸው የህክምና ባለሙያዎች፣ እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ጥራቱን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት ታገኛላችሁ፡፡ ከዚያም በምቹና አስደሳች ከባቢ ውስጥ በፍጥነት ጤናችሁን ትቀዳጃላችሁ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኩዌት፣ ኳታርና ኢራቅን ጨምሮ ከአረብ አገራት በርካታ ዜጎች ለህክምና ወደ ኢራን ይመጣሉ፡፡ በብቃት በተደራጁና ጥራታቸውን በጠበቁ ሆስፒታሎች ውስጥ ይታከማሉ፡፡ ከአውሮፓ አገራት ይልቅ ኢራንን ይመርጣሉ፡፡ አንድም የህክምና ዋጋ ከአውሮፓ በእጅጉ ዝቅተኛ በመሆኑ፤ አንድም ደግሞ ለቅርበቱ፡፡
የዛሬዋ ኢራንና  አቅሞቿ
ከአብዮቱ ድል  በፊት ኢራን  በጤናውና ህክምናው ዘርፍ  ጥገኛ ከሆኑ አገራት አንዷ ነበረች፡፡ ከእስላማዊ አብዮቱ ድል በኋላና አሁን ደግሞ (ከአራት አስርት ዓመታት በኋላ) በዓለም ከሚገኙ ዋነኛ የህክምና ማዕከላት አንዷ ለመሆን በቅታለች፡፡
ኢራን በአሁኑ ወቅት  ከሚያስፈልጓት መድሃኒቶች ውስጥ ከ97 በመቶ በላይ የሚሆነውን በአገር ውስጥ እያመረተች ሲሆን ከ14 በላይ recombination መድሃኒቶችም ታመርታለች፤አብዛኛውም ካንሰርን ለመሳሰሉ በሽታዋች ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ኢራን በደም መተካት ህክምና (blood transfusion medicine) ዘርፍ በእሰያ ካሉ 5 ቀዳሚ አገራት አንዷ ናት፡፡ በተጨማሪም በዓለም ሁለተኛዋ የፕላዝማ ቴራፒ ፕሮጀክት ተግባሪ ናት፡፡
የኢራን የጤና ቱሪዝም ኢንዱስትሪ፣ በውበትና ትሪትመንት ዘርፍ የተሟላ የህክምና አገልግሎቶችን  ይሸፍናል፡፡ የፊት እንዲሁም የእጅና እግር ውበት፣የጥርስ ማስተካከያ፣የመካንነት፣ የውፍረት ቅነሳ ቀዶ ጥገና፣የጀርባ ህመም፣የልብ ህመም፣የዓይን ቀዶ ጥገና፣የተለያዩ ካንሰሮች ሴል (ቲሹ) ምርመራና ህክምና፣ እንዲሁም የውስጥ አካል ቅድመ ተከላ፣የነርቭ ቀዶ ጥገና እና ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች በኢራን ይሰጣሉ፡፡
የፕላስቲክ ቀዶ ህክምናዎች በኢራን
ኢራን በዓመት ውስጥ በሚከናወኑ የፕላስቲክ ቀዶ ህክምናዎች ብዛት በዓለም  ቀዳሚዋ ናት፡፡ በኢራን በዘመናዊ የህክምና ተቋማት ውስጥ የፕላስቲክ ቀዶ ጥገና በሚያደርጉ ግለሰቦች ዘንድ ከተቀዳጀችው እምነት ባሻገር፣ በፕላስቲክ ቀዶ ህክምና ዋጋ አንጻር በኢራንና ሌሎች አገራት መካከል ያለው ከፍተኛ ልዩነት ህመምተኞች ኢራንን ተመራጭ  እንዲያደርጓት አበረታቷቸዋል፡፡
የህክምና አገልግሎት በኢራን ለምን?
ኢራን  የዓለም ጎብኚዎችን በሚያማልሉት ባህላዊ፣ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ትንግርቶቿ ትታወቃለች፡፡ ባለፉት አስርት ዓመታት ደግሞ የህክምና ቱሪዝም በሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች ወደ አገሪቱ እንዲጓዙ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡
ኢራን በዓለም ቀዳሚ ከሆኑት የጤና ቱሪዝም መዳረሻዎች አንዷ ናት፡፡ ከመላው ዓለም የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደዚህች አገር የሚጓዙ ህመምተኞች  በከፍተኛ መጠን እየጨመሩ መጥተዋል፡፡
መንግስት የጤና ቱሪዝሙን በንቃት እያስተዋወቀ ነው፡፡ ኢራን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከመላው ዓለም ለሚመጡ ጎብኚዎች አስተማማኝ የህክምና መዳረሻ ሆናለች፡፡
የህክምና ማዕከላትና ሆስፒታሎች የጤና ቱሪዝም ያለውን አቅም ተገንዝበዋል፤ እናም ግሩም የማረፊያ ስፍራ፣የላቀ ህክምና፣ ተመጣጣኝ ዋጋና ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶች የሚያቀርቡ ተቋማት ለጎብኚዎች (ተጓዦች) ግሩም አማራጭ ሆነዋል፡፡
በኢትዮጵያና በኢራን መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበትን 70ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም፣ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢራን የባህል ማዕከል የታዳጊዎች የስዕል ውድድር አዘጋጅቷል፡፡
የውድድሩ ጭብጥ ፡- የኢትዮ - ኢራን ወዳጅነት
ዕድሜ ፡- ከ 11 እስከ 16 ዓመት
የማስረከቢያ ቀነ-ገደብ፡-   ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ  መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም  ድረስ
የኢራን ባህል ማዕከል ለውድድሩ አሸናፊዎች  ሽልማት ይሰጣል፡፡
የውድድር ጭብጡን ወይም ደንቦችን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት በኢሜይል አድራሻችን፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.   ወይም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ይጻፉልን፡፡
ለበለጠ ዝርዝር መረጃ የፌስቡክ ገፃችንን ይጎብኙ፡፡
https://www.facebook.com/IranianculturalcenterInaddisababa

  ይህ ጽሁፍ በዓለማቀፍ የወዳጅነት ቀን ዋዜማ ላይ፣ በእህትማማች አገራቱ በኢራንና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ለማሳየትና ሁለቱ አገራት ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ዕምቅ እድሎችን ለመጠቆም ያለመ ነው፡፡
ጥንታዊ ፐርሺያና ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጮች ነበሩ፡፡ እነዚህ ታላላቅ ሥልጣኔዎች፤ በንግድና ባህላዊ እሴቶች አማካኝነት መደበኛ ግንኙነቶችንና ልውውጦችን ሲያደርጉ ኖረዋል፡፡ በርካታ የአኗኗር ልማዶችን፣ ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም የሥነምግባርና የሞራል መርሆችን ተጋርተዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በጥንታዊ ሥልጣኔ ፈር ቀዳጅነት ብቻ ሳይሆን መድብለ-ባህላዊነትንና  ብዝኃነትን በማስተናገድም ረገድ ተመሳሳይነትን ይጋራሉ፡፡ በታሪክ፣ የተለያዩ ብሔሮች አገር የሆነችው ኢራን፤ በርካታ የብሔረሰብ፣ ቋንቋና ሀይማኖት ቡድኖችን ያቀፈች መድብለ  ህብረተሰብ ሆና ቀጥላለች፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ኢትዮጵያም የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ሀይማኖቶችና ባህላዊ እሴቶች ያሏቸው ብሔር ብሔረሰቦች አገር ናት፡፡ ሁለቱም  መድብለ ባህላዊነትን እንደ አስተዳደር ዘይቤያቸው ሙሉ በሙሉ ተቀብለውታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት ብዝኃነትን በአግባቡ በመያዝና በሰላም በጋራ መኖርን በማረጋገጥ ረገድ አይነተኛ ምሳሌዎች ናቸው፤ያውም በዓለም አቀፍ ደረጃ የአገራዊ ብሔርተኝነት ተረክ እየጎላ በመጣበት ዘመን፡፡
ሁለቱ ታላላቅ ሀገራት በረዥም ዘመን ታሪካቸው በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል፡፡ አገራቱ የገጠሟቸውን የውጭ ወራሪዎች በፅናት ተዋግተዋል፡፡ ነፃነታቸውን ለመቀዳጀትም ህዝባቸውን መስዋዕት አድርገዋል፡፡ ነፃነትንና ሉአላዊነትን ማስጠበቅ ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለትውልድ ላስተማሩ የሁለቱ ሀገራት ሰማዕታት ምስጋና ይግባቸውና፤ በወራሪ የውጭ ሀይሎች ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል፡፡
በዘመናዊ ዲኘሎማሲ አግባብ፣ በኢራንና በኢትዮጵያ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት የተመሰረተው እ.ኤ.አ በ1960 ዓ.ም ነው፡፡ ኢራን፤ ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ግንኙነት የመሰረተችበት የመጀመሪያዋ አገር ኢትዮጵያ ስትሆን ሁለቱ አገራት በአለም አቀፍና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ እይታዎችን ሲጋሩ ኖረዋል። ኢራንና ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ከመሰረቱት አባል አገራት መካከል ተጠቃሽ ሲሆኑ የተባበሩት መንግስታት ቻርተር ፈራሚዎችም ናቸው፡፡ ከተባበሩት መንግስታትም አስቀድሞ ሁለቱ አገራት ሰላም የሰፈነባት ዓለም የመፍጠር፣ የእርስ በእርስ ዕውቅናና ክብር የመስጠት እንዲሁም ጣልቃ ያለመግባት መርሆችን ለማክበር ያላቸውን ቁርጠኝነት ሊግ ኦፍ ኔሽንን በመቀላቀል አረጋግጠዋል፤ ምንም እንኳን ተቋሙ የተጣለበትን አደራ ሙሉ በሙሉ መወጣት ቢሳነውም፡፡ ሁለቱ አገራት የNon-Aligned movement (NAM) ደጋፊና አባላትም ናቸው፡፡ ሁለቱም የNAM ንቁ ተሳታፊ ሲሆኑ በንቅናቄው አማካኝነትም፣ ጣልቃ ገብነትን፣ ቅልበሳን፤ በሀያላን አገራት የሚደረግ የሀይል እርምጃን እንዲሁም በሌሎች አገራት የፖሊሲ አቅጣጫ ላይ ማናቸውም አይነት ርዕዮተ አለም ለመጫን የሚያደርጉትን ጥረት አበክረው ይቃወማሉ፡፡ ኢራንና ኢትዮጵያ፣ በNAM አማካኝነት፣ አባል አገራት ነፃነትን ፣እኩልነትንና ብሔራዊ ማንነትን እንዲሁም ውጤታማ ትብብርን እንዲያረጋግጡ አበረታተዋል፡፡  
የእህትማማች አገራቱ ጠንካራ ትብብር በሌሎች አለማቀፋዊና ክልላዊ ጉዳዮችም ተስተውለዋል፡፡ ሁለቱም የ G-77 እና ሳውዝ-ሳውዝ ትብብርና ሌሎች መድረኮችም አባላት ናቸው፡፡ ኢራንና ኢትዮጵያ፣ በእነዚህ መድረኮች አማካኝነት፣ ለአለማቀፋዊና ክልላዊ ጉዳዮች በስምምነት ላይ የተመሰረተ ህግ ለመቅረጽ እንዲሁም አለማቀፋዊና ክልላዊ ተግዳሮቶችን በመፍታት ረገድ ሁሉም አሸናፊ የሚሆንበት ዲፕሎማሲያዊ ማዕቀፍ ለማጎልበት ተግተዋል፡፡
የኢራንና የኢትዮጵያ መሪዎች በ1971 ዓ.ም የኤሚቲ ትሪቲን በመፈረም አርቆ አሳቢነት የተመላበት ውሳኔን ወስነዋል፤ ይህም ሁለቱ ህዝቦች የመሰረቱትን ወዳጅነት የሚያጠናክር ወሳኝ ፖለቲካዊና ህጋዊ መሰረቶችን የጣለና ከረዥም ጊዜ አንፃርም፣ የሁለትዮሽ የወዳጅነት ትብብርን የሚያረጋግጥ ነው፡፡ የኤሚቲ ትሪቲ መፈረም ሁለቱ አገራት እንዲሁም የሁለቱ አገራት ህዝቦች የረዥም ጊዜ ልማትን ለማረጋገጥ ያላቸውን ፅኑ ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ውሉ ወይም ስምምነቱ የተፈረመው የጋራ ልማትና ብልፅግናን ለማሳካት ይቻል ዘንድ ሁለቱንም በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ ትብብርን ለማጠናከር ነበር፡፡
ለመጪዎቹ ረዥም ጊዜያት፣ ኢራንና ኢትዮጵያን በአንድነት የሚያስተሳስሩ እጅግ በርካታ ዕድሎች አሉ፡፡ ከአለም ነባራዊ ሁኔታ አንፃር፣ በአንድ ክፍለ ዘመን ያልታየ ጉልህ ለውጥ እየታዘብን ባለንበት ወቅት፣ ኢራን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር፣ በጋራ ለመስራትና ለሁለቱም ህዝቦች የበለጠ ተጠቃሚነትን ለማምጣት፣ የአገራቱን የወዳጅነት ትብብር ወደ አዲስ ደረጃ ለማሳደግ ዝግጁ ናት፡፡ ውስብስብና ተለዋዋጭ አለማቀፋዊ እውነታ በተደቀነበት ሁኔታ፣ ኢራንና ኢትዮጵያ በእጅጉ ማደጋቸውን መቀጠል ያለባቸው ሲሆን የሁለትዮሽ ግንኙነቶችንም ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ ይኖርባቸዋል፡፡
 አገራቱ ካላቸው የቴክኒክና ኢንጅነሪንግ አቅምና ችሎታ አንፃር፣ ኢራንና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ የኢኮኖሚና ንግድ ትስስራቸውን ሊያሳድጉት ይችላሉ፡፡ ሁለቱ አገራት ካላቸው የገበያ ስፋትና ቅርበት እንዲሁም የኢኮኖሚ አቅም አንፃር፣ የንግድ ግንኙነታቸው ሳይቋረጥ   እያደገ መቀጠል ይኖርበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በአግሮ-ፕሮሰሲንግና ኢነርጂ ዘርፍ ኢንቨስት ያደረጉ የኢራን ኩባንያዎች አሉ፤ ነገር ግን ኢራን ተጨማሪ ኩባንያዎችን በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሳታፊ ሆነው ማየት ትሻለች፡፡  
የአገሮቻችንን የቴክኖሎጂ እድገት አንዳንድ  አገራት ለመግታት በሚያደርጉት ማቆሚያ የለሽ የሆነ ሙከራ አውድ ውስጥ፣ በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍ መስተጋብር መፍጠር ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ነው፡፡ የሳይንስ፣ የቴክኒክና የፈጠራ ትብብርን ማጠናከር ያስፈልገናል፡፡ የሁለተኛና የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በኢራን ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚከታተሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ቢኖሩም፣ ያለውን አቅም አሟጥጦ ለመጠቀም የበለጠ መስራት ይገባናል፡፡
ሁለቱም አገራት ለብዝኃነት መርህ ተገዥ ሲሆኑ፤ የአንድ ወገን የበላይነትንና የሀይል ፖለቲካን ይቃወማሉ። በዚህ ረገድም በስፋት ይመሳሰላሉ፡፡ ፍላጎታቸውና አጀንዳቸው ብዙ ጊዜ ይጣጣማል፤ ሁለቱም በተባበሩት መንግስታት ላይ ለተመሰረተ አለም አቀፍ የህግ ማዕቀፍ ትኩረት ይሰጣሉ፤ በተለይም በሉአላዊ አገራት ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ ያለመግባት መርህን፡፡
 ሲጠቃለል፤ ኢራንና ኢትዮጵያ ያለፈው ዘመን ታላላቅ አገራት ብቻ አይደሉም፤ የመጪውም ዘመን ታላላቅ አገራት እንጂ፡፡ በመጨረሻም፤ ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት እንዲሁም ለሁሉም ሰላም ወዳድ ህዝቦች፤ እንኳን ለአለም አቀፍ የወዳጅነት ቀን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡
በኢትዮጵያና በኢራን መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረበትን 70ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግም፣ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢራን የባህል ማዕከል የታዳጊዎች የስዕል ውድድር አዘጋጅቷል፡፡
የውድድሩ ጭብጥ ፡- የኢትዮ - ኢራን ወዳጅነት
ዕድሜ ፡- ከ 11 እስከ 16 ዓመት
የማስረከቢያ ቀነ-ገደብ፡-   ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ  መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም  ድረስ
የኢራን ባህል ማዕከል ለውድድሩ አሸናፊዎች  ሽልማት ይሰጣል፡፡
የውድድር ጭብጡን ወይም ደንቦችን በተመለከተ ጥያቄ ካለዎት በኢሜይል አድራሻችን፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.   ይጻፉልን፡፡


 የአፍሪካ የአየር መንገዶች ተጓዦች ቁጥር በ66 በመቶ ቀንሷል


            የኳታሩ ሃማድ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ የ2021 የፈረንጆች አመት የአለማችን ምርጥ አውሮፕላን ማረፊያ ተብሎ መሸለሙን አረብ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በአለም ዙሪያ የሚገኙ የአውሮፕላን ጣቢያዎችን በተለያዩ መስፈርቶች እየገመገመ ደረጃ የሚሰጠው ስካይትራክስ የተባለው ተቋም፣ ከሰሞኑም የአመቱን ምርጦች ዝርዝር ይፋ ያደረገ ሲሆን ባለፈው አመት በ3ኛ ደረጃ ላይ የነበረውና በኳታር መዲና ዶሃ የሚገኘው ሃማድ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ዘንድሮ በአንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
በዘንድሮው የአለማችን ምርጥ የአውሮፕላን ማረፊያዎች ዝርዝር ውስጥ የሁለተኛነትን ደረጃ የያዘው የጃፓኑ ቶክዮ ሃኔዳ አውሮፕላን ማረፊያ ሲሆን፣ ሲንጋፖር ቻንጊ አውሮፕላን ማረፊያ ሶስተኛ ደረጃን ለመያዝ ችሏል፡፡
ከአራተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ የያዙትም እንደ ቅደም ተከተላቸው ኢንቼኦን አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ናሪታ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ሙኒክ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ዙሪክ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የለንደኑ ሄትሮው አውሮፕላን ማረፊያ፣ ካንሳኢ አውሮፕላን ማረፊያ እና ሆንግ ኮንግ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በአመቱ ከፍተኛ የደረጃ መሻሻል ያሳየው የአውሮፕላን ማረፊያ ኢስታንቡል ኤርፖርት መሆኑንና ባለፈው አመት ከነበረበት 102ኛ ደረጃ ዘንድሮ ወደ 17ኛ ደረጃ ከፍ ማለቱንም ዘገባው አመልክቷል፡፡
በተያያዘ ዜና ደግሞ፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አለማቀፉ የአየር ትራንስፖርት መንገደኞች ቁጥር በ70 አመታት ውስጥ ከፍተኛውን ቅናሽ ባሳየበት የፈረንጆች አመት 2020፣ የአፍሪካ አየር መንገዶች ያጓጓዟቸው መንገደኞች ቁጥር በ2019 ከነበረው  በ66 በመቶ ያህል ቅናሽ ማሳየቱን ዘ ኢስት አፍሪካን ድረገጽ ከሰሞኑ ባወጣው ዘገባ አስነብቧል፡፡
የአፍሪካ የአየር መንገዶች በ2019 ያጓጓዟቸው መንገደኞች ቁጥር 95 ሚሊዮን ያህል እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፣ በ2020 የፈረንጆች አመት ግን ይህ ቁጥር በ65.7 በመቶ ያህል በመቀነስ ወደ 34.3 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን አመልክቷል፡፡
የአፍሪካ አየር መንገዶች በአመቱ በድምሩ 10.21 ቢሊዮን ዶላር ያህል ገቢ ማጣታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፣ አለማቀፉ የአየር መንገደኞች ገቢም በ69 በመቶ ያህል ቅናሽ ማሳየቱንም አመልክቷል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝ በአለማቀፍ ጉዞዎች ላይ የፈጠረው ቀውስ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር ያስታወሰው ዘገባው፣ የአለማቀፍ የአየር መንገደኞች ቁጥር በአንጻሩ በ2019 ከነበረበት 4.5 ቢሊዮን በ60.2 በመቶ ያህል በመቀነስ ወደ 1.8 ቢሊዮን ዝቅ ማለቱንም አክሎ ገልጧል፡፡


 የሱዳን መንግስት በእስር ላይ የሚገኙትን የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርንና ሌሎች የቀድሞ ባለስልጣናትን ለአለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አሳልፎ እንደሚሰጥ ማስታወቁን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
የአገሪቱ መንግስት የቀድሞውን መሪ ኦማር አልበሽርን ጨምሮ በዳርፉር ግጭት ወቅት የጦር ወንጀሎችንና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ፈጽመዋል ተብለው በአለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን የቀድሞ ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናትን አሳልፎ እንደሚሰጥ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያም አል መሃዲ ባለፈው ረቡዕ ማስታወቃቸውን ገልጧል፡፡
አልበሽርና ባለስልጣናቱ ለአለማቀፉ ፍርድ ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ ውሳኔ የተላለፈው የሱዳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባደረገው ስብሰባ እንዲሁም የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ከሰሞኑ ሱዳንን በጎበኙት ተቀማጭነቱ በሄግ የሆነው አለማቀፉ ፍርድ ቤት ዋና አቃቤ ህግ መካከል በተደረገ ውይይት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መናገራቸውንም ዘገባው አብራርቷል፡፡
ከአልበሽር ጋር ለአለማቀፉ ፍርድ ቤት ተላልፈው ይሰጣሉ ከተባሉት የቀድሞ የሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከልም፣ የአገር ውስጥና የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት አብደል ራሂም ሙሃመድ ሁሴን እንደሚገኙበት የጠቆመው ዘገባው፣ የሱዳን አቃቤ ህግ በዳርፉር ግጭት አልበሽርና ሌሎች ባለስልጣናት ፈጽመውታል የተባለውን ወንጀል በተመለከተ ባለፈው አመት የራሱን ምርመራ ጀምሮ እንደነበርም አስታውሷል፡፡
እ.ኤ.አ በ2003 በተቀሰቀሰው የዳርፉር ግጭት ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውንና ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

   እንደ መግቢያ
ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ [በግርድፉ የጥራት ሲኒ እንበለው ይሆን] የቡና የጥራት ውድድር ነው። ባለፉት 20 ዓመታት የጥራት ውድድር በዋና ዋና የቡና አብቃይ አገራት ውስጥ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በኢትዮጵያ ውድድሩ የተጀመረው ባለፈው ዓመት ነው።
ዓላማው ከተመረቱት ቡናዎች መካከል የተሻለውን ቡና መርጦ፣ በዓለም አቀፍ ጨረታ ለታላላቅ ገዢዎች መሸጥ ነው። በተጨማሪም፣ ትልቁ ዓላማው፣ ገበሬዎችን ማስተዋወቅ እንዲሁም በአንድ አገር ያሉትን ልዩ ጣዕም ያላቸውን ቡናዎችና አምራቾች ማስተዋወቅ ነው።
“ሲዳማ ውስጥ ያደገ ማንም ሰው ስለ ቡና በደንብ ያውቃል”
ታምሩ ታደሠ ውልደቱና ዕድገቱ በሲዳማ ክልል በምትገኘው ቀጠና ቀበሌ ነው። ከቡና ጋር የተዛመደ ሥራ የጀመረው በቅርቡ ነው። ግን ቡናን ያውቃል። በደንብ ያውቃል። “ሲዳማ ውስጥ ያደገ ማንም ሰው ስለ ቡና በደንብ ያውቃል። ይሰማል። አብዛኛው የአካባቢው ነጋዴ ቡና ነው የሚነገደው” ይላል።
ትምህርቱን በኤሌክትሪካል ምህንድስና ካጠናቀቀ በኋላ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ማስተማር ጀመረ። ለሁለተኛ ዲግሪ ትምህርቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ‘5 ኪሎ’ ገባ። ከትምህርቱ ጎን ለጎን፣ ቡና ኤክስፖርት በሚያደርግ ድርጅት ውስጥ ተቀጠረ።
“ለማስተርስ  ዲግሪ 5 ኪሎ እየተማርኩ፣ ዱካለ ዋቀዮ የሚባል ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ለ6 ዓመት ሰርቻለሁ። ስለ ቡና ያወቅሁት ያኔ ነው” ብሏል፤ ለቢቢሲ።
ስለ ቡና ሥራ ዕውቀቱን ሲያገኝ ቀጣዩ ዕቅዱ ደግሞ የራሱን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ነበር። ከዓመት በፊት ዓላማው ተሳክቶም ድርጅቱን አቋቋመ።
“ሲዳማ መፈጠር ስለ ቡና እንድታስብ ያደርጋል። ቡናው በዕውቀት ሳይሆን በልምድ ስለነበር በፊት ቁጭት ነበረኝ። ቡና ላይ ብሠራ ስለምል ልምዱም ጠቀመኝ።”
የግድ ግን ወደ እርሻ መግባት አልነበረበትም። “የቡና እርሻ እኔ የለኝም። እርሻ ካላቸው ገበሬዎች ነው የምንሰበሰብው። የተለያየ መጠን ያለው የቡና እርሻ ካላቸው ወደ 400 ከሚጠጉ ገበሬዎች ነው ቡና የምንሰበስበው” ብሏል፤ታምሩ።
“ዓምና አንድ ኪሎ ቡና 407 ዶላር ተሸጧል”
ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ሲጀመር፣ የኮቪድ ወረርሽኝ ሂደቱን አስቸጋሪ አድርጎት የነበረ ቢሆንም ብዙ ገዢዎች ግን ተሳትፈውበታል። ውድድሩ በጣም ጥብቅና የምርጦች ምርጥ የሚወጣበት ነው። በዘንድሮው ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ፣ 1864 ቡናዎች ለውድድር ቀርበው ነበር።
“ከመላው ቡና አምራች አካባቢዎች የመጡት ሁሉ ተቀምሰው የተሻሉ የተባሉት 40ዎቹን ወደ ስምንት አገር ልከናል” ይላሉ፤ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ኢትዮጵያ አማካሪ ወ/ት ቅድስት ሙሉጌታ።
ቀጣዩ  እነዚህን 40 ቡናዎች በጨረታ መግዛት ነው።
“እነዚህ ልዩ ጣዕም ያላቸው ቡናዎች የኢትዮጵያ ቡና ናቸው። ገዢዎቹ ልዩነታቸውንና ጣዕማቸውን ስለሚፈልጉት ነው ተጫርተው የሚገዙት” ይላሉ፤ወ/ት ቅድስት፡፡
“ባለፈው ዓመት 407 ዶላር በኪሎ የተሸጠው ለኢትዮጵያ ቡና የተከፈለ ትልቁ ዋጋ ነው። ከሲዳማ ክልል ቡና አምራቹ አቶ ንጉሤ ገመዳ  ናቸው በዚህ ዋጋ የሸጡት።”
ባለፈው ዓመት አንደኛ የወጣው ሰባት ኬሻ ቡና ነው የተሸጠው። አንዱ ኬሻ 60 ኪሎ ነው። የዘንድሮ አሸናፊም ከሲዳማ ክልል አልወጣም። ተረኛው ታምሩ ታደሠ ነው።
“24 ኬሻ ነው ከፍተኛው ማቅረብ የሚቻለው”
ታምሩ ታደሠ ስለ ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በአጋጣሚ ሰምቶ ነው ለውድድሩ እንዲዘጋጅ የተገፋፋው፡፡ “ባለፈው ዓመት ያሸነፈው ጓደኛዬ ነው። የማውቀው ሰው ነው። ያም አስተዋጽኦ ነበረው። በዚያው ቡና ለማዘጋጀት ወሰንኩ። ለውድድር ብቻ ሳይሆን ኤክስፖርት የሚሆንም ነው ያዘጋጀሁት። ማስታወቂያ ሲወጣ አቀረብኩ” ብሏል።
ታምሩ ሁለት ዓይነት ቡና ይዞ ቀረበ። ሁለቱም ቡናዎች ተሳካላቸው። አንደኛው ቀዳሚውን ደረጃ ሲይዝ፣ ሁለተኛው ደግሞ አምስተኛ ደረጃን ያዘ፡፡  
“24 ኬሻ ነው ከፍተኛው ማቅረብ የሚቻለው። እኔም አንደኛ ከወጣው ቡና 24 ኬሻ ነው ያቀረብኩት። አንድ ኬሻ በ60 ኪሎ ነው። ስለዚህ አንደኛ የወጣው 1440 ኪሎ ነው። አምስተኛ የወጣውም ብዛቱ ተመሳሳይ ነው።”
ቡናዎቹ ደረጃቸው ብቻ ሳይሆን ዋጋቸውም ጭምር ነው እጅን በአፍ ላይ የሚያስጭነው።  አንደኛ የወጣው ቡና በኪሎ 330 ዶላር ነው የተሸጠው።
“ለጨረታ የቀረበው 1440 ኪሎው አይደለም። ለናሙናም ብዙ አገር ሲላክ፣ ዝግጅት ሲደረግም የሚወጣ ስላለ 1140 ኪሎ ብቻ ነው ለጨረታ የቀረበው። አንደኛ የወጣው ወደ 364 ሺህ ዶላር ነው የተሸጠው።”
አምስተኛ የወጣው ወደ 67 ሺህ ዶላር ተሸጧል።
“በአጠቃላይ ሁለቱም 431 ሺህ ዶላር ገደማ ነው የተሸጠው። አሁን ባለው የዶላር ምንዛሪ ወደ 19 ሚሊየን ብር ማለት ነው” ታምሩ እንደገለጸው።
“ገዢዎቹ በጣም የተለየ ቡና ለመግዛት ነው የሚወዳደሩት”
ለምን ይሆን ቡናዎቹ በዚህን ያህል ዋጋ የሚሸጡት?
ይህ የቡና ግብይት መድረክ የተለየ ገበያ መሆኑን የሚገልጹት ወ/ት ቅድስት፤ “ሁሉም ቡና ግን በዚህ ዋጋ አይሸጥም” ይላሉ።
“ስፔሻሊቲም (ባለ ልዩ ጣዕም ቡና) እንደዚህ አይሸጥም። ይህ ውድድር ነው። ገዢዎቹ በጣም የተለየ ቡና ለመግዛት ነው የሚወዳደሩት። በዚያ ላይ ቡናው በአራት ደረጃ፣ በስምንት አገራት ተቀምሶ ስለተሸጠ በአንድ አምራች ሊሸጥ ሲሞከር አንድ አይደለም።” ሲሉ ያስረዳሉ፤ወ/ት ቅድስት፡፡
“ሌላው ካፕ ኦፈ ኤክሰለንስ ብዙ አባላት አሉት። እነሱ በሚያምኑት መንገድ ምንም መጭበርበር ሳይኖር የሚቀርብ ቡና ስለሆነም ነው በዚያ ዋጋ የሚሸጠው፡፡” ብለዋል።
የታምሩ ቡናስ ምን ቢሆን ነው እንደዚህ ተወዳጅና ተመራጭ የሆነው? ዋጋስ ያወጣለት?
“ቡናው ከሌላው ቡና የሚለየው፣ ከሚበቅልበት ቦታ ነው። አየሩ፣ ከአፈሩ ቡናው የሚያገኘው ሚኒራል አካባቢው ሁሉ ተደምሮ ልዩ ያደርገዋል። ከበቀለበት ቦታ እንጂ እኛ ያደረግነው ልዩ ነገር የለም። የቡናው ዝርያ ችግኙ 74158 እና 74165 የሚባል ዝርያ እኛ ጋ ብቻ አይደለም ያለው፤ ሌላም ቦታ አለ። በጣም ከፍታ ቦታ ላይ የሚበቅል ነው። ቦታው ነው ልዩ የሚያደርገው።” ብሏል፤ታምሩ፡፡
"ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ በረከት ይዞ
እንደመጣ ቁጠረው"
ውድድሩ የአንድ ጊዜ ገንዘብ ማግኛ ብቻ አይደለም። ታምሩም ሁሌም ቡናውን በዚህ ዋጋ ይሸጣልም ማለት አይደለም።
“በውድድሩ መሳተፉ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ተቆጥሮም የሚያልቅ አይደለም። አንደኛውና ትልቁ ዕውቅናን ያቀዳጃል፡፡ ቡና ላይ ያለ ሰውና ገዢዎችን ለማወቅ ያግዛል። ለአገርም ለግለሰብም ትልቅ ጥቅም ነው የሚያመጣው። በዘርፉ ታዋቂ እንድትሆን ያደርጋል። ለዓለም ገበያ ኤክስፖርት እንዲኖርህ ያደርጋል። በገንዘብ ረገድም በጣም ይረዳል።”
“ጥሩ መነቃቃት ነው ለእኛ ካምፓኒ የፈጠረው። በኢትዮጵያ ደረጃም ካየነው ‘ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ’ ትልቅ ዕድል ነው ይዞ የመጣው። በረከት ይዞ እንደመጣ ቁጠረው። ለአገራችንም መነቃቃቱ ደስ የሚል ነው። ገበሬው ሁሉ ከፍ ያለ ዋጋ ነው የሚያገኘው። እንዲህ ነው ብለህ የምትጨርሰው አይደለም” ብሏል።
ጥቅሙ ታምሩ ከገለጸው ቢበልጥ እንጂ የሚያንስ አይደለም የሚሉት ወ/ት ቅድስት ናቸው።
“ሽልማቱም ለሁሉም ነው” ይላል፤ ታምሩ፡፡
“ውድደሩ ተጽዕኖ ይፈጥራል፡፡ ካለፈው ዓመት አሸናፊዎች እንዳየነው፣ አካባቢው በመተዋወቁ ከመደበኛው ዋጋ በላይ በሦስት እጥፍ እየሸጡ ነው። አንዱ አምራች ካሸነፈ በአካባቢው ሌሎችም ቡና አምራቾች ይጠቀማሉ።” ብለዋል፤ ወ/ት ቅድስት፡፡
ገንዘቡ ጠቀም ያለ ነውና ብሩን ምን ላይ ታውለዋለህ? ሲል ቢቢሲ ታምሩን ጠየቀ።
“ቡና ውስጥ ነው ያለሁት። 100 ፐርሰንት ኤክስፖርት አደርጋለሁ። የቡና ሥራዬን ሰፋ አድርጌ ለመሥራት ነው ዕቅዴ። በዚህ ብቻ ሳይሆን ከባንክም ጨምሬ ሰፋ አድርጌ ለመሥራት ነው የምፈልገው” ታምሩ መለሰ።
መቼም ውጤቱ የታምሩ ብቻ አይደለም። ብዙዎችም ተሳትፈዋል። “ሽልማቱም ለሁሉም ነው” የሚለውም ለዚህ ነው።
“ገበሬዎች አሉ፤ ቡና የሚያቀርቡ፡፡ እነሱ ላይ የተሻለ ነገር እንዲኖራቸው እንደ ሽልማትም ለመስጠት አስበናል። እነሱንም ማበረታታት ነው። ቀጣይነት እንዲኖረው ከግብርና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ችግኝ በማቅረብ ምርታማነትን በመጨመር፣ ህይወታቸውን የሚያሻሽል ነገር በገንዘቡ ለመሥራት አስበናል።”
ታምሩ የአሁኑ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈበት ነው። ለዚህም ነው “በቀጣይ እወዳደራለሁ፤ ብዙ ቡና ላልሰጥ እችላለሁ ግን እወዳደራለሁ፤ በየዓመቱ ቡና እያዘጋጀሁ” ያለው፡፡  
“የቡና ሱሰኛ አይደለሁም”
ለመሆኑ ዘንድሮ ምርጥ ቡና ከኢትዮጵያ ማቅረብ የቻለው ታምሩ ቡና ይጠጣል?
ቡና ይጠጣል። ግን ካገኘ ነው። ሱሰኛ አይደለም። ካገኘ አራትም አምስትም ሲኒ በቀን ሊጠጣ ይችላል። ካጣ ደግሞ አንድም ላይጠጣ ይችላል። የጀበና ቡና ብዙም አይመስጠውም። ምክንያቱም ታምሩ ቡና መቅመስ ተምሯል። “በጣም ልምድ ባይኖረኝም እቀምሳለሁ” ሲል ራሱን ይገልጻል።
ቡና መቅመስ መቻሉ ደግሞ “ቡና ለመለየትም ለማድነቅም ጥሩ ነው” ይላል።
“የጀበና ቡና ብዙ ጊዜ ስለሚያር አልወደውም፡፡ በትክከል የሚፈላውን እጠጣለሁ፡፡” ብሏል።
እንደ መውጫ
ብዙዎቹ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ተጫራቾችና ገዢዎች ቡናን ከመቁላት ጀምሮ በተለያዩ ደረጃ እሴት ጨምረው የሚሸጡ ናቸው። ሲሸጡም ‘ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ’ ብለው በከፍተኛ ዋጋ ነው የሚሸጡት። ሌሎች ደግሞ በጣም ትልልቅ የሆኑ ካፌዎች ውስጥ ይሸጣሉ።
“ባለፈው ዓመት አንደኛ [የሆነውን ቡና የገዛው] ለንደን ውስጥ በ65 ዶላር ነው አንድ ሲኒ የሸጠው። እሱም በማስታወቂያ ከዚህ እስከዚህ ቀን ተብሎ በግል ባሬስታ ነው የቀረበው” ብለዋል፤ ወ/ት ቅድስት።
“እነዚህ እንግዲህ ሃይ ኢንድ [ከፍተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ] ካፌዎች ናቸው። በጣም ውድ ውድድር ነው። ለብዙ ሰዎች የሚደርስ ሳይሆን የቅንጦት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህም ነው ታምሩ፣ በቡና ዘርፍ የተሰማራችሁ ወገኖች፣ በውድድሩ ተሳተፉ የሚለው።
“እየተወዳደርኩ እቀጥላለሁ፡፡ መወዳደሩ ጥሩ ነው፤ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው። ሁሉም ቡና ላይ የተሠማራ ሰው መወዳደር አለበት ብዬ ነው የምመክረው” ብሏል።
ውድድሩ ለማንም ክፍት ነው፤ ቡና ላይ ለተሠማራ አምራችም ሆነ ወደ ውጪ ላኪ ለሆነ ነጋዴ።
መስፈርት ግን አለ። “ቡናው ትሬሰብል (ከየት ተነስቶ የት እንደደረሰ የሚያሳይ ማስረጃ የሚቀርብበት) መሆን አለበት። በትክክል ቡናው የተመረተበትን ቦታ መረጃ እንፈልጋለን፤ የይዞታ ማረጋገጫ እንፈልጋለን። ይህን ማሟላት የሚችል መሳተፍ ይችላል” ብለዋል፤ ወ/ት ቅድስት።
እናም ለሚቀጥለው ዓመት ተዘጋጁ ተብላችኋል።
ምንጭ፡ (ቢቢሲ)
       ዶ/ር  ወርቁ መኮንን ኮመርስ (የንግድ ሥራ ኮሌጅ) ከቦታው መነሳቱን በመቃወም፣ በሪፖርተር ጋዜጣ ሐምሌ 25 ቀን 2013 ዓ.ም የተወሰኑ ውሀ የማይቋጥሩ ነጥቦችን አስቀምጠዋል።
መነሳታቸው አግባብነት ያለውና መንግስት ወደፊትም በሌሎችም በጥናት ላይ ተመስርቶ እንዲያድሱ፣ ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ እንዲገነቡና ቦታ እንዲቀይሩ ማድረግ ይጠበቅበታል። ይህም አዲስ አበባን፣ አዲስ አበባ የማድረግ ወሳኝ ተግባር ሲሆን እንደ ኮመርስ ያሉ ተቋማት ላይ ግን የተወሰደው እርምጃ ቢዘገይም ትክክለኛነቱን መጥቀስ ያስፈልጋል።
1.ተቋሙ እንደ ስሙ እድሜውና የያዘው ትልቅ ስፍራ የቆሻሻ መጣያ የመሰለ፣ ውስጡና ውጭው የቆሸሸ፣ ገፅታን የሚያበላሽ፣ ለተማሪው የማይመጥን አሳፋሪ ስፍራ የነበረ መሆኑ ያደባባይ ሚስጢር ነው።
2. አዲስ አበባ በጀመረችው የከተማ ለውጥ ጉዞ (አርባናይዜሽን) ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ፣ የከተማችንን ውበት እውን ማድረግ በሁለንተናዊ ቅንጅታዊ ስራ በመሆኑ፣ የረባ ያልረባ ምክንያት መፍጠር ሳይሆን የመፍትሄ አካል መሆን ይገባል።
3.  ለውጥ ሲኖር ነውጥ መኖሩ ግር ሳይለው በቀጣይም መንግስት ከተማዋን ለማዘመን የሚታደሱ፣ የሚፈርሱ ብሎም የሚሸጋሸጉ ተቋማት መኖራቸውን የቅድመ ግንዛቤ ስራ በመስራት፣ ኢትዮጵያን የአለም ቱሪስቶች ግንባር ቀደም መስህብ ማድረግ ያስፈልጋል።
ስዩም አበረ
( PhD in Urban Planning )


 ኢትዮጵያ እስከ 1966 ዓ.ም ማብቂያ ድረስ ባላባታዊ ስርዓት የምትከተል፣ በንጉሠ ነገሥት የምትመራ አገር ነበረች። በዘውዱ አገዛዝ ስር የምትገኘውን ኢትዮጵያ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረው ዋለልኝ መኮንን “የብሔረሰቦች ጥያቄ” በሚል ርዕስ ባቀረበው ጽሑፍ፤ “የብሔረሰቦች እስር ቤት” ሲል ፈረጃት። ከዚህ ፍረጃ በመነሳትም በብሔረሰባችን ላይ ጭቆና ደርሶበታል ያሉ አንዳንድ ወጣቶች፣ የየብሔረሰባቸውን የነጻነት ንቅናቄ ወይም ግንባር መሰረቱ። የሁሉም ንቅናቄዎች ወይም ግንባሮች አላማና ግብ፣ አለብን የሚሉትን ጭቆና ማስወገድና ኢትዮጵያን የእኩልነት አገር አድርጎ ማስቀጠል ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን በማፍረስ የየራሳቸውን ነፃ አገር መመሥረት እንዲሆን ተደርጎ ተቀረፀ።
ነፃነቱን የነፈጋቸው ፊውዳላዊውና ዘውዳዊው መንግሥት ነው ብለው በተቀበሉበት መጠን፣ ዘውዳዊውን መንግሥት፣ የአማራ መንግሥት አድርገው በመውሰዳቸው፣ አማራ ነፃነት ሰጪ እነሱ ነጻነት ተቀባይ ሆኑ። አማርኛ ቋንቋው ለአገር አቀፍ መግባቢያ በመሆን ከማገልገሉ በቀር የተለየ ልማትና እድገት ያላገኘው አማራ፣ በሌላው ሃብት እንደለማ ተደርጎ እስከ መታሰብም ተደረሰ።
የአጼ ኃይለስላሴ መንግስት ወድቆ የደርግ መንግስት ከተመሰረተ በኋላ የፊውዳላዊው መንግስት የኢኮኖሚ መሰረት የነበረው መሬት፣ በየካቲት 1967 ዓ.ም “የመሬት ላራሹ” አዋጁ ከታወጀና  መሬት የሕዝብ ከሆነ፣ ጭሰኝነት ከቀረ፣ ፊውዳሊዝም እንደ ሥርዓት ከፈረሰ በኋላ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በግልጽ መለወጡ የማይታይ ቢሆንም፣ የነጻነት ንቅናቄዎቹ ግን ከተለወጠው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጋር የተለወጠ የፖለቲካ አላማና ግብ መስራት አልቻሉም። የደርግ 17 ዓመት፣ የኢሕአዴግ 27 ዓመት፣ በድምሩ 44 ዓመት ያህል ጊዜ የነጎደ ቢሆንም፣ ነጻ አውጪ ነን ብለው እራሳቸውን የሰየሙ ወገኖች ዘንድ ግን ዛሬም በኢትዮጵያ መንግስታዊ ስልጣን ላይ ያለው “የንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት” ሆኖ ነው የሚታያቸው። ስለዚህም ነው ዛሬም ድረስ ከአርባ ዓመት በፊት ባነሱት ጥያቄ ላይ እንደቆሙ የቀሩት። ለዚህም ነው አማራ በኢትዮጵያ መንግስታዊ ሥልጣን ላይ ባይኖርም፣ በነገራቸው  ሁሉ ፀረ አማራ ሆነው የቀጠሉት። በዚህ በኩል ደግሞ አሸባሪውን ትህነግን የሚያህልና  የሚወዳደር ድርጅት የለም።
ትህሕነግ ለአማራ ነፍጠኛ የሚል ስም በመስጠት በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ብሔረሰቦች ጠላት አድርገው እንዲቆጥሩት አድርጎት እንደነበርም አይዘነጋም። ከክልሉ ወጪ ያለው አማራ ነፍጠኛ፣ በክልሉ ውስጥ የሚገኘው ደግሞ ትምክህተኛ እየተባለ በትሕነግ/ኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን፣ በአማራው ላይ የደረሰው በደል እጅግ ብዙ ነው። እሱን ከመዘርዘር ለታሪክ መተዉ የተሻለ ነው። ለዚያም ቢሆን ለማወቅ እንጂ ቂም ለመቋጠር እንዳይሆን አጥብቆ ማሳሰብ ያስፈልጋል። በቀል በበቀል አይሻርም፣ በይቅርታ እንጂ።
ከ2008 እስከ 2010 ዓ.ም መጋቢት ድረስ በዘለቀው የሕዝብ አመጻ ወንበሩ የተነቀነቀው ትህነግ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር  ዐቢይ አሕመድ መንግስት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ጓዙን ጠቅልሎ መቀሌ ለመግባት ተገድዷል። ወደ መቀሌ የሄደው ክልሉን ለማልማት ሳይሆን ለጦርነት ዝግጅት ለማድረግ ነበር፡፡
የአገሪቱ የመከላከያ ሰባ በመቶ የሚሆነውን ኃይል በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲሰፍር መደረጉ፣ የደህንነቱንና መገናኛውን ወዘተ ማዕከል ወደ መቀሌ መሻገሩ፣ ይኸና ይህን የመሰለው ተግባሩ ሁሉ ሲታይ፣ ትሕነግ ለአንድ ዓይት ፍልሚያ እራሱን ሲያዘጋጅ የነበረው ከአዲስ አበባ እግሩን ከመንቀሉ ብዙ ዓመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ለመረዳት አይከብድም።
ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ላይ ጥቃት የከፈተውና ጦርነቱን የጀመረውም ከእጄ የሚወጣ ወይም የሚያመልጥ ነገር የለም ከሚል እምነት ተነስቶ እንደሆነም እርግጥ ነው።
በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ያለ የሌለ ትጥቁ ወድሟል፤ ከሞትና ከምርኮ የተረፈው አመራሩም  በተምቤን በረሃ እንደ ዝንጀሮ ገደል ለገደል እየተንከራተተ ነው የተባለው ትሕነግ፤ ከስምንት ወር በኋላ እንዴትና እንደምን ወደ አጥቂነት ተሻጋገረ ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።
የአማራና አፋር ክልሎች የትግራይ ተጎራባች በመሆናቸው የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆነዋል፡፡ ትሕነግ ከትግራይ ድንበር ብዙ ርቀት ተጉዞ  አፋርና አማራ ክልል እስኪገባ ድረስ ምን እየተጠበቀ ነበር? ማለትም ግድ ይሆናል።  
ወደ ኋላ እንመለስ፡፡ ደርግ መቀሌን ለቆ ከወጣ በኋላ የትሕነግ ሰራዊት፣ “የትግራይ ድንበር አልውኃ ነው ብላችሁናል። ከዚህ በኋላ አንዋጋም። ሌላው ብሔር ብሔረሰብ ነፃነቱን ከፈለገው ራሱ ተዋግቶ ነፃነቱን በራሱ ያምጣ” በማለት አቋም ወስዶ እንደነበር ይታወቃል። ወደ አማራ ክልልና ወደ ሌላው አካባቢም የተንቀሳቀሰው ከብዙ ጊዜ  የፖለቲካ ሥራ በኋላ ነው። አማራ ክልል ከገባ በኋላ ደግሞ የተዋጋው ደርግን ይጠላ የነበረውንም ያልነበረውንም አማራ፣ በውድም በግድም  በፊት መስመር በማሰለፍ ነው።
ደርግ ትግራይን ለቆ ለትህነግ የመደራጃ ጊዜ መስጠቱና ትህነግ አማራ ክልል መግባቱ በአማራ ጉልበትና ህይወት ደርግን ለመውጋት ተጠቅሞበታል። ዛሬም ተመሳሳይ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ትህነግ በገባበት የአማራ ክልል የሚገኘውን ወጣትና  መሳሪያ ለመሸከም አቅም ያለውን የከበበውን ሰው እያስገደደ፣ ወደ ጦርነት የሚማግድበት ሁኔታ እየተፈጠረለት ነው።
የመጀመሪያው እርምጃ የትህነግን እንቅስቃሴ ወደ ኋላ መመለስ፣ እሱም ካልተቻለ ባለበት እንዲቆም ማድረግ ነው። ወደ ማሰልጠኛ እየገባ ያለውን የሰው ኃይል የእግረኛ ሰልፍ ማስተማሩ ቀርቶ ግዳጁን ለመፈጸም የሚያስችለው ስልጠና መስጠት ነው።
ሁለተኛው ልዩ ልዩ በራሪ ወረቀቶች በማዘጋጀት የትህነግ ጦር እጁን ለመከላከያ እንዲሰጥ ማግባባት ነው። በዚህ መንገድ የአንድ ሰው ልብ ማሸነፍ ከተቻለ እንደ ትልቅ ግብ መታየትም ይኖርበታል። ከሁሉ በላይ ግን የፌደራል መንግስትም ሆነ የክልል መንግሥታት እየተፋለሙት ያለውን ጠላት ማለትም፣ ትሕነግን አበጥረው አንጠርጥረው ማወቃቸው ወሳኝ ነው፡፡ ትሕነግን ድል ለመምታት አስፈላጊና ቀዳሚ ግብዓት ነውና።


 ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ንጉሥ ሶስት ጠቢባን አማካሪዎቻቸውን ይጠሩና ጥያቄ ይጠይቋቸዋል።
መሠረታዊ ጥያቄው፡-
አንድ ሰፊ እልፍኝ ዘንድ ወሰዷቸውና፤
“በጣም በርካሽ ዋጋ የሚገዛ፣ ሆኖም ይህንን እልፍኝ ከአዳራሽ የሚሞላ ነገር አምጡልኝ” አሏቸው።
የመጀመሪያው ጠቢብ፤
“ንጉሥ ሆይ! ይህን እልፍኝ የሚሞላ አምጥቻለሁ”
ንጉሡም፤
“መልካም፣ አሳየና?” አሉና ጠየቁት።
ጠቢቡም ያንን እልፍኝ የሚሞላ ጥጥ አቀረበና እልፍኙን ሞልቶ ለማሳየት ሞከረ። ንጉሡ ነጥብ ይዘው ተቀምጠዋል። ቀጥለው ንጉሡ ሁለተኛውን ጠቢብ ጠሩና፤
“ያንተን መወዳደሪያ አቅርብልና?” አሉት።
ተወዳዳሪው ጠቢብም፤
“ንጉሥ ሆይ፤ እነዚህን ጆንያዎች አምጥቻለሁ” አለና በብዙ ጆንያዎች የተሞላ አሸዋ ይዞ ቀረበ። አሸዋው ግን ከነጆንያው ሙሉ ሆኖ ቀረበ እንጂ ብቻውን እንዲወጣ ሲደረግ እልፍኙን ሊሞላ አልቻለም።
በመጨረሻው ንጉሡ ሦስተኛውን ጠቢብ ጠሩና፤
“አንተስ እልፍኙን የሚሞላ ምን ነገር ታቀርብልናለህ?” ሲሉ ጠየቁት።
ጠቢቡም የሚያስገርም ጥበብ ይዞ ቀረበ።
ይኸውም አንዲት ሻማና ክብሪት ነው።
ክብሪቱ ተጫረ። ተለኮሰና ሻማው በራ። እልፍኙ በብርሃን ሞላ።
ሶስተኛው ጠቢብ አሸናፊ ሆኖ ሽልማቱን ተቀበለ።
ንጉሡም እንዲህ ያለ ጠቢብ ስለሰጣቸው አምላካቸውን አመሰገኑ።
*   *   *
በጥበበኞች የታደለች አገር ከአገሮች ሁሉ ለብልፅግና የቀረበች ናት። መታደሏን ግን ህዝቧ ካላወቀ እርባና ላለው ሥልጣኔ አትመቻችም። ለዚህ ኃላፊነት ወጣቷን፣ ሴቶቿን፣ ምሁራኗን፣ ሊቃውንቷን ማበረታታት፣ የዕድገት መንገዶቿን ሁሉ መጥረግ ዋና ትኩረቷ ሊሆን ይገባዋል። ይህን ለማድረግ ግን አስቀድሞ ህዝቧን በአካልም በመንፈስም ማዘጋጀት ዋና ጉዳይዋ መሆን አለበት። የልጆቿ ያዋቂዎቿና የአዛውንቶቿ ጤና፣ ትምህርት፣ መልካም አስተዳደር ሊጤን ይገባዋል። ሥልጣኔ የሚታይ እንጂ የማይበላ ፍሬ ሆኖ ከቆየ  ሰነባብቷል። የማይበላውን ፍሬ አብስሎ የሚበላ ፍሬ ለማድረግ ታታሪነት፣ ልዩ ጥረት፣ ወቅታዊነትና ወቅት አልባነት (Timeliness and Timelessness) ሊኖር ይገባል።
አንድም ደግሞ በዕቅድ ላይ የተመሰረተ የሥራና የኑሮ ሂደትን ሳይታክቱ በማበረታታት ዕድገትን የማጎልበትን ክህሎት ማፍካት የህዝባችን በመላ ልዩ ኩራት እንዲሆን መታገል ልዩ ዒላማና ዓላማ ይሆን ዘንድ ዐይናችንን ሙሉ በሙሉ ከፍተን መንገዳችንን በንቃት ፀዳል እናብራ።
በፀጋዬ ገ/መድህን (ሎሬት) ትርጓሜ የሼክስፒርን ማክቤዝ የመጨረሻ ሰዓት እንዲህ ብሎ እንዳቀረበው እንይ። ሁለቱንም የሎሬት ፀጋዬን የትርጉም ብቃትም ለማሳየት ስንል አቅርበነዋል።
“--Tomorrow and tomorrow and tomorrow
 creeps in this Pety  Pace to the last syllables
Of the recorded times
And all our yesterdays have lighted fools the way to dusty death.
Out! Out! Brief Candle,
life is but a walking shadow
 a poor player, that struts and frets
His our upon the stage and is heard no more.
It is a tale told by an idiot
 full of sound and fury signifying nothing!”
“የነገ ውሎ፣ የነገ ውሎ፣ የነገ ውሎ”
ከቀን ወደ ቀን ይሳባል፣ በዕድሜ ንፉግ ጀርባ ታዝሎ
ትላንትናም ከትላንት በስቲያም፣ ለጅሎች ጥርጊያ አሳምሮ
ዛሬ ፈጥሮ ነገ ቀብሮ
እፍ አንቺ ብርሃን ጨልሚ አንቺ የህይወት ጭላንጭል
 የምትንቀሳቀሺው ጥላ የሰው ህይወት የሰው ዕድል
እንደ አልባሌ ተዋናይ
ተታትሮ ተፍጨርጭሮ ተውተርትሮ መድረኩ ላይ
 ለብልጭታ ብቻ እሚታይ
ጅል የሞኞች ተረት ነሽ
ቋሚ ትርጉም የሌለብሽ።”
ኑሯችን ለብልጭታ ብቻ የምንኖረው መሆን የለበትም። ቋሚና ዘላቂ ትርጉም ያለው እንጂ፡፡ ያ እንዲሆን ደግሞ ሥር-ነቀል አካሄድ፣ ደርዝ ያለው ለውጥ እና ያልተሸራረፈ ጉዞን መራመድ ያስፈልጋል።
ሀገራችን የመሪና የተመሪ ስብጥርና ልኬት እንዲኖራት አስፈላጊ ከሆኑት ግብዓቶች አንዱ የበሰለና አስተዋይ መሪ ለመሆን የሚጣጣሩ ልጆች ማፍራትዋ ነው። ለመሪነት በሚጣጣሩ ጊዜ ተመሪነትን ማወቅ አይቀሬ ነውና! ለዚህም ነው “መልካም  ተመሪ ከመሆን መልካም መሪ ለመሆን ተጣጣር” የሚባለው።

   ጥቅምት 24 ቀን 2013 በትግራይ በተቀሰቀሰውና ላለፉት 10 ወራት በዘለቀው ጦርነት፣ እስካሁን በተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት ጭምር በተረጋገጡ መረጃዎች፣ 2 ሺ ያህል ንጹኃን ዜጎች በህወኃት ሃይል ተገድለዋል፡፡
የአማራ ማንነት ጥያቄ ለዘመናት ሲነሳበት በነበረው ወልቃይት ጠገዴ በኩል በማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ሳምሪ በተባለው ቡድን ተፈጽሟል በተባለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ከ1 ሺህ 2 መቶ በላይ ሰዎች ስለመገደላቸው  የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን፤ በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ጥናት ያደረገው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በተፈፀመው ዘር ተኮር የጅምላ ጥቃት 1600 ያህል ንጹኃን መገደላቸውን ይፋ አድርጓል፡፡
የፌደራል መንግስት የክረምት ጊዜ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አርሶ አደሩ ወደ እርሻ ተግባሩ እንዲገባ በማሰብ የተናጥል ተኩስ አቁም እርምጃ መውሰዱን ተከትሎ ደግሞ ህወኃት መቀሌና ሌሎች የትግራይ አካባቢዎችን በተቆጣጠረበት አጋጣሚ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹኃንን “ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር አብራችኋል; በሚል እንደገደላቸው በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች ካወጧቸው መግለጫዎች መገንዘብ ይቻላል፡፡ ከሌሎች ገለልተኛ ወይም በሰብአዊ መብት ጥበቃና ክትትል ላይ ከሚሰሩ ተቋማት ማረጋገጫ ባይገኝም፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በመቀሌ ብቻ “ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ወግናችኋል” በሚል በህወኃት የተገደሉት ሰዎች 53 ያህል መሆናቸውን በወቅቱ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል፡፡
የፌደራል መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም እርምጃን ወደ ጎን በማለት ጦርነቱን የቀጠለው በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወኃት፤ በአፋር በኩል በከፈተው ጦርነት ደግሞ ጦርነቱን ሽሽት በአንድ ማዕከል በተጠለሉ 108 ያህል ህጻናትን ጨምሮ ከ240 በላይ ንፁሃን ላይ የጅምላ ግድያ መፈፀሙን አለማቀፍ ተቋማት ጭምር አረጋግጠዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫው፤ ግድያው እጅግ አሳዛኝና ሌሎች ተመሳሳይ ጥቃቶች ሊፈፀሙ እንደሚችሉም አመላካች መሆኑን አስገንዝቧል፡፡
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በአጠቃላይ ህወኃት በራሱ መንገድ በጀመረው ጦርነት ባለፉት 10 ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ2 ሺህ በላይ የንጹኃን ህይወት ጠፍቷል።
ከዚያ ቀደም  የፌደራል መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ ማጣሪያ መረጃ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት፤ በምዕራብ ወለጋና በሌሎች አካባቢዎች በህወኃት አቀነባባሪነት 1500 ያህል ዜጎች በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ መገደላቸውን ይፋ ማድረጉም አይዘነጋም፡፡
በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወኃት እነዚህን ሁሉ ድርጊቶች መፈጸሙን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና አለማቀፍ ተቋማት በየጊዜው ይፋ እያደረጉ ቢሆንም፣ አሁን ባለው ጦርነት የህወኃትን በደል አይቶ እንዳላየ በማለፍ ምዕራባውያን የጦርነቱን ሁሉ ሃጢያት በፌደራል መንግስቱ ላይ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። የፌደራል መንግስቱም እውነታውን በተደጋጋሚ እያስረዳ ቢሆንም፣ እስካሁን ምዕራባውያን ሃገራት ጆሮ የሰጡት አይመስሉም።
በህወኃት ተንኳሽነት በተቀሰቀሰውና 10 ወራት ባስቆጠረው የትግራይ ጦርነት፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ይፋ ባደረገው ወቅታዊ መረጃው፤ በትግራይ ብቻ 2 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ለእርዳታ ተዳርገዋል፤ ከ68 ሺህ የሚልቁት ደግሞ ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ተሰደዋል፡፡
በአጠቃላይ በህወኃት ቆስቋሽነት በተጀመረው ጦርነት፣ የትግራይ ህዝብ በእጅጉ ተጎሳቁላል። 5.2 ሚሊዮን ገደማ ህዝብ በቀጥታ የሰው እጅ ጠባቂ እንዲሆን ተፈርዶበታል፡፡ አሁንም አርሶ አደሮች ተረጋግተው የእርሻ ተግባራቸውን እንዳያከናውኑ ጦርነቱ እንቅፋት ሆኖባቸዋል፡፡ በርካቶቹ አርሶ አደሮችና የአርሶ አደር ልጆች ቀጥተኛ የጦርነቱ ተሳታፊ መሆናቸውን ምርኮኞች ከሚሰጡት ቃል መረዳት ይቻላል፡፡
በትግራይ በአሁኑ ወቅት ወደ ትምህርት ቤት የሚላክ ህፃን የለም፡፡ ት/ቤቶች ተዘግተዋል፣ ዩኒቨርሲቲዎች ተከርችመዋል። የትግራይ አዲስ ትውልድ እንደሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሱን በእውቀት እንዳያበቃ የተፈረደበት ይመስላል፡፡ በዚህ ትርጉም አልባ ጦርነት የትግራይ ህጻናትና ታዳጊዎች ተስፋ መክኗል፡፡ የትውልዱ ስነ ልቦና እንዲላሽቅ ተደርጓል።
የዚህ ጦርነት ዳፋ በትግራይ ብቻ አያበቃም፡፡ እንደ ሃገር በኢኮኖሚው ላይ  እያሳደረ ያለው ተጽዕኖም ቀላል አይደለም። መንግስት በ8 ወራት ጊዜ  ውስጥ የጦርነት ወጪውን ሳይጨምር በሰብአዊ ድጋፍና ትግራይን መልሶ ለመገንባት ብቻ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ፈሰስ ማድረጉን መግለፁ አይዘነጋም፡፡
መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም ባደረገበት ሁኔታ ጦርነቱን የቀጠለው ህወኃት፤ በአፋርና አማራ ክልል አካባቢዎች በፈጸመው ወረራም  በመቶ ሺዎች ተፈናቅለዋል፡፡ እንደ ክልል መንግስታቱ ሪፖርት ከሆነ፤ በአፋር ከ3 መቶ ሺህ በላይ ዜጎች የህወኃትን ጥቃት ሽሽት ሲፈናቀሉ፤ በአማራ ክልል በተመሳሳይ ከ250 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቅለዋል፡፡
ትግራይን ጨምሮ በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወኃት ተቆጣጥሯቸዋል በተባሉ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የመብራት፣ የስልክና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንደ ልብ እየተሟላላቸው አለመሆኑም የበርካቶችን ህይወት አናግቷል፤ የሚሊዮኖችን ተስፋ ነጥቋል፡፡
ህወኃት እንደ አዲስ ጦርነት ከፍቶ በተቆጣጠራቸው የራያና የሰሜን ወሎ አካባቢዎች ዜጎች ቀለብ አስፈጭተው እንዳይበሉ እንኳን የኤሌክትሪክ ሃይል አለመኖሩ እንቅፋት እንደሆነባቸውና በርካቶች ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን ከየአካባቢዎቹ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ህወኃት ሁሉንም ነገር ለጦርነት በሚል አባዜው፣ ከገበሬው ጎሮሮ እየነጠቀ ጦሩንም እያጠናከረበት እንደሆነ ይነገራል፡፡
መንግስት እንኳን ይፋ ባደረገው መረጃ፤ በ8 ወራት ውስጥ 100 ቢሊዮን ብር ወጪ ከማድረጉ ባለፈ፣ የተናጥል ተኩስ አቁሙን ከማድረጉ በፊት 4 መቶ ሺህ ኩንታል የእርዳታ እህል፣ 2.5 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ፣ 536 ሺህ 979 ኩንታል ማዳበሪያ፣ 37 ሺህ 599 ኩንታል ምርጥ ዘር ለህዝቡ ደህንነት ሲባል አስቀምጦ መውጣቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም 1079 ሜትሪክ ቶን ምግብ፣664 ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች፣ 47 ሺህ 740 ሊትር ነዳጅ በአለማቀፍ ተቋማት በኩል  ከተኩስ አቁሙ በኋላ እንዲገባ ተደርጓል፡፡
እነዚህ ሁሉ ለህዝቡ የቀረቡ የነፍስ ማቆያ ግብአቶች አሁን ላይ ለምን አላማ እየዋሉ ነው? የእርዳታ እህል በረሃብ አደጋ ላይ ላለው የትግራይ ህዝብ በትክክል እየደረሰ ነው? በክልሉ የሰብአዊ መብት አያያዝ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? ለዚህ ሁሉ ምላሽ የሚገኘው ጦርነቱ ሲቆም ብቻ ነው፡፡
ይህ ፈርጀ ብዙ የሰብአዊ ውድመት እያደረሰ የሚገኘው ጦርነት መቼ እንደሚቋጭ ደግሞ ለጊዜው ማንም የሚያውቅ አይመስልም፡፡                                             አድማስ ትውስታ

 ጥጋዊ፣ ጽንፋዊው፣ ዋልታዊ
በማህበራዊነትና በሉአላዊው ግለሰብ (Sovereign self) መካከል ሁልጊዜ ውጥረት አለ። “እኔ” ያለ “እኛ” ትንፋሽ ሲያጥረው፣ “እኛ”ም “እኔ” ከሌለ ህልውናም የለውም። ተፈላላጊም ናቸው፣ ተጠፋፊም ናቸው። “እኛ” “እኔ”ን ውጦ አይጠረቃም፣ “እኔ”ም የ “እኛ” ፍላጎቱ አያቆምም። ባጭሩ ማህበራዊነት ያለ ግለሰብ፣ ግለሰብም ያለ ማህበራዊነት ሊኖሩ አይችሉም። ይሁን እንጂ ማህበራዊነትን የጠላ ግለሰብም ሆነ ግለሰብነትን ያጠፋ ማሕበረሰብ፣ አንዱ የተናጠል፣ ሌላውም የስብስብ ስነ ልቡና ቀውስ ይገጥማቸዋል። ከእነዚህ የቀውስ ምልክቶች አንዱና ግጭት ፈጣሪ ወይም የተፈጠረን ግጭት አሻቃቢ የሆነው “የቡድን ኅሊና” ግሩፕ ቲንክ ነው።
ትርጓሜው፦ “የቡድን ኅሊና ማለት ግለሰቦች በቅጡ ድብልቅ ያለ ቡድን ውስጥ ጭልጥ ብለው ሲቀላቀሉ፣ አንድ ድምጽ ለመሆን ሲባል አዙሮ ማሰብንና እውነታን ወግድ የሚልና አማራጭን የማያይ፣ “ይሆንን?” ተብሎ ያልተጠየቀ ተግባር የሚመራው አስተሳሰብ ነው።” ድንገት ማሰብ ከቻለም የሚያስበው ከእኩይ ድርጊቱ በኋላ ነው።
ክፋቱ የአንድ ዘመን ወቅት ሆኖ አለማለፉ ነው። በእኩያን የግብ መምቻ የተመረጡ ትርክቶች (Selected victims’ narrative) እየተመራ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ የስብስብ ኅሊና (collective mindset) ባህል ይሆናል። በእውቀትና በኢኮኖሚ ድሆች በሆኑ አገሮች ለሰንሰለታማ ቍርቍስ ምክንያት ሆኖ የዘለቀ ቢሆንም በአጠቃላይ እውቀትና ብልጽግናም አይቸግራቸውም የምንላቸውን ምእራባውያንን የማይምር፣ የሰው ልጅ የተቻችሎ ኑሮ ጸር ነው።
አንድ ቡድን የሚከተሉት ስምንት ምልክቶች ካሉት የቡድን ኅሊና (Groupthink)   እያዳበረ ነው ማለት ይቻላል።
ስምንት ባሕሪያት አሉት፡-
ህልማዊ አይበገሬነት - Illusions of Invulnerability:
ሊደረግ አይችልም ተብሎ የሚታሰብን ተግባር ለማድረግ የሚያነሳሳ፣ ከልክ ያለፈ፣ የድላዊነት ስሜት የሚመራው ህልማዊ አይበገሬነት አለው።
ለማስጠንቀቂያዎች ምክንያት መስጠት Rationalization of Warnings:
ቡድኑ አለኝ የሚለውን ምግባር ልክነት የማይጠይቅ ስለሆነ የቡድኑ ውሳኔ በተግባር ለሚያስከትለው የሞራል እኩይ ውጤት ደንታ የለውም። “ከዚህም በፊት እንዲህ ተብሏል፣ ያኔም አሁንም ልክ” ብሎ ያልፋል።
ቸልተኛነት Complacency:
እንደ ቡድን ማስጠንቀቂያዎችን ዋጋ ያሳጣቸዋል። ቡድኑ የውሳኔውን አሉታዊ ውጤቶች ችላ ይላል።….
ባላጋራን የክፉ ተመሳስሎት ገጽታ መስጠት Stereotyping:
የጠላት ተብዬ መሪዎችን የክፉ ተመሳስሎት ገጽታ (Stereotype) እያበጁለት፣ እያሰየጠኑ (Demoniz) ወይም እያናናቁና እንደ ጅል እየቆጠሩ፣ የቡድኑ ሐሳብ አደናቃፊ እንደሆኑ እንዲታዩ ያደርጋሉ፤ እንዲህም በማድረግ ለሶስተኛ ወገን መካከለኛነት አስቸጋሪ ይሆናሉ።
የታማኝነት ተጽእኖ - Loyalty Pressure:
ውልፊት የሚል የቡድን አባልም ካለ ቀጥተኛ ተጽእኖ ይገጥመዋል፣ እያደርም ቡድኑ ይህንን ዓይነቱን አባል እንደ ከሀዲ እንዲቆጥረው ይደረጋል።
ራስን መገደብ/መቆጣጠር Self-Censorship:
ግለሰቦች ከቡድኑ የጋራ ስምምነት እንዳይወጡ ራሳቸውን ይቆጣጠራሉ። … ከቡድኑ የተለየ ማስተዋል እንዳላቸው ቢያውቁም ግለሰቦች ይህንን በመግለጥ መሳለቂያ ላለመሆን ራሳቸውን ያግታሉ።
ቡድኑ አንድ ድምጽ ያለው እንደሆነ የሚያስብ ቅዠት አለው Illusion of Unanimity:
የቡድን ኅሊና፣ ቡድኑ አንድ ድምጽ ያለው እንደሆነ የሚያስብ ቅዠት አለው። ይኽም በከፊል ግለሰቦች ለቡድኑ ያላቸውን ታማኝነት የሚያሳዩበት ሲሆን ከራስ ቍጥጥርም የሚመነጭ ስለሆነ ተቃውሞ የሌለበት ዝምታ ሁሉ ስምምነት እንደሆነ ያስባሉ።
የቡድን ኅሊና ጠባቂዎች Mind-guards:
ራሳቸውን የሾሙ የቡድኑን ኅሊና ጠባቂዎችም አሏቸው። እነዚህ ጠባቂዎችም ቡድኑ ከያዘው አቋም ከውጪም ሆነ ከውስጥ የሚመነጭን ይከላከላሉ።
ቡድኑ ተከታይ ነው እንጂ ሀሳብ አፍላቂ አይደለም፣ የተጫነ ነው። አንድ ወይንም ጥቂት መሪ እንዳዘዘው ይጓዛል፣ መነሻቸው አንድ ዓይነት ማህበራዊ ወይም ርእዮተ ዓለማዊ መነሻ መሆኑ ብቻ በቂ ነው፣ ጎሳም፣ ሃይማኖትም፣ የፖለቲካ ርእዮትም ሊሆን ይችላል። አንድ ቡድን አጋጥሞኛል ለሚለው ቀውስ ፈጣን ምላሽ መስጠት አለብኝ ብሎ ሲያምን፣ በዚህ እምነት ጥላ ሥር የሚሰባሰቡ ሁሉ መጀመሪያ የሚያጡት በእርጋታ የሚገኘውን ትክክለኛ የአስተሳሰብ ደረጃ ነው።
እንዴት ይፈጠራል? እንዴትስ ለግጭት ሽቅበት ምክንያት ይሆናል?
ተጠቅተናል ብሎ በቡድን የሚያስብ አንድ ጎራ ፍርሃት፣ ጭንቀትና ቁጣ ስላለበት ፈጣኑ ተግባር አጥቂ ተብዬውን መጉዳት ነው። ለዚህ ምክንያት በመሆን ወይም ከዚህ ተግባር በኋላ ደግሞ ሃፍረትና ውርደት የተባሉ የዝቅታ ስሜቶች ስለሚኖሩ በቀል የሚል ተግባር ይከተላል፣ ይህ ደግሞ አዳዲስ ማሕበራዊ ግጭቶችን ይፈጥራል፣ ወይም የተፈጠረ ግጭትን እንዲያሻቅብ ያደርጋል። ትንንሽ ቡድኖች፣ ተቋሞች፣ ወይም አገሮች፣ በጣም ተፎካካሪ የሆነ ግጭት ውስጥ ሲገቡ ከግጭቱ በፊት ከነበራቸው ሁኔታ በእጅጉ በብዙ ነገር በፍጥነት ይቀየራሉ፣ ይኽም ቅያሬአቸው ለግጭት ማሻቀብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
ጥጋዊ፣ ጽንፋዊው፣ ዋልታዊ ይሆናል፦ ውይይቶቻቸውና የቡድኑ አባላት በግንዛቤአቸውም ሆነ በባህሪያቸው ያከረሩና ጠላት ተኮር ይሆናሉ፦ አንድ ርእሰ ጉዳይ በቡድኑ መካከል ሲወሳ አባላት ቀድሞ ከነበራቸው ግንዛቤ የበለጠ የጠነከሩ ይሆናሉ፤ ከቡድናቸው ያልተቃረነ ተጨማሪ ማጠናከሪያ ያገኛሉ፤ እያንዳንዱም የሚያደርገው አስተዋጽኦ ቡድኑን የበለጠ የሚያከር እንዲሆን በማድረግ የቡድኑ አጠናካሪ በመሆን ተቀባይነት ማግኘት ይፈልጋል። ጥላቻና አለመተማመንም ወደዚያኛው ጎራ ይወረወራል።
ደንብ ይፈጥራል፦ ውዝግቡን በሚመለከት የቡድኑ ግንዛቤ በአብዛኛው አባላት አንድ ዓይነትነት ያለው ልማዳዊ ይሆናል። ወደ ሌላው ያለው አመለካከት አሉታዊ ግንዛቤ ያለው፣ የሌሎችን ጉዳት እንደ ትርፍ የሚቆጥርና (ዜሮ ሰም) እነዚህም ነገሮች በተፈጸሙ መጠን የጥንካሬና የድለኝነት መረጋጋት ስሜት የሚኖረው አስተሳሰብ ነው፣ እንዲህ ዓይነቱም ልማድ (ኖርም) የተፈጠረን ግጭት አሻቃቢ ይሆናል።
የማጥፊያ ግቦችን ያዳብራል፦ በግጭት ጊዜ ሌሎችን ማሸነፍ ወይንም ማጥፋት ቡድናዊ ተግባር ይሆናል። ይህ ተግባር ዑደታዊ ስለሆነ ያለፈ የቡድኑ ልምድ ይኸው ከሆነ፣ አሁንም ግጭት ሲፈጠር እዚያው ማሸነፍና ወይም ማጥፋት ዑደት ውስጥ ይገባል። ይህ የቡድን ኅሊና የሚመራው ተግባር ቢያስፈልግ ከራሱ ውስጥ ንኡስ ቡድን በመፍጠር በግድ አሸናፊ ቡድን ይፈጥራል። የተፈጠረውን ግጭት ማሻቀብም በራሱ እንደ ድል ይቆጠራል።
የተመሳስሎት ግንባር ይፈጥራል፦ ይህ ግንባር ነክ ገጽታ አባል ማራኪ ነው። የተመሳሰለ ቡድን ከተሰባጠረ ቡድን የሚለየው ሌላውን ቡድን እንደ ተፎካካሪ ሳይሆን፣ እንደ ተቃዋሚ ስለሚቆጥር ትግሉ “ሁሉ” ዐመጻዊና አድማዊ ነው።
መለዮ ባይለብስም ይህ የቡድን ኅሊና ራሱን በወታደራዊ ገጽታ ያደራጃል መደበኛ የሆኑና ተቀባይነት ያላቸው ግጭቶች ልዩ ልዩ ረብሻ አልባ ወደ ግብ መድረሻ መንገዶች ሲጠቀሙ የቡድን ኅሊና ያሰባሰበው ቡድን ያመነው ትራኬ፣ ከሃይማኖት ስለሚጠነክር ተአማኒ መሪ ተብሎ የሚሰየመው ከዲፕሎማሲ ክህሎትና ዝንባሌ ይልቅ ወታደራዊ ተክለ ማንነት ያለው ነው። 
ዓላማው መግባባት ያልሆነ ተቋማዊ አደረጃጀት ይደራጃል አንደኛ፣ የእንቅስቃሴው ተነሳስቶት ማሸነፍና ማሸነፍ ብቻ ነው። ሁለተኛ፣ ብዙ መሪዎቹ “ረጅም ጊዜ” ባላጋራ ተብየውን ተገዳድሮ ለመጣል ሲጠባበቁ የነበሩ ናቸው። 
የቡድን ኅሊና ስህተት ብቻ ሳይሆን ክፉም ነው የቡድን ኅሊና የማያጠፋው የለም፣ የተፈጠረው ሊያጠፉኝ ነው ከሚል ስጋት በመሆኑ ቀድሞ ማጥፋት ግቡ ነው። ጓደኝነት ትዳር ቤተሰብ፣ ቤተ እምነትንና አገርን የሚፈታ ነው። የራሳችን ኅሊና አብሮን ተፈጥሮ፣ ሳንኖርበት ዳኝነት ሳንሰጥበት፣ በጭፍልቅ ኖረን እንድንሞት የሚያደርገን፣ ያለ ዐዋጅ የተለቀቀብን ኮሚኒስት ነው፣ ይሆንን ብለን እንዳንጠይቅ፣ ነው የተባልነውን ሁሉ ይዘን እንድንንጋጋ የሚያደርገን፣ እኛው የሰጠነው እልፍ እግሮች ያለው የመዋጮ አንድ ጭንቅላት ነው። የቡድን ኅሊና ተንኮለኞች የሚፈጥሩት፣ ያልተፈጠረ ዓለም ወይም የተጋነነ ዓለም ውስጥ ገብተን፣ በህገ አራዊት እንድንኖር የሚያደርገን፣ የሕልም ዓለም ነው። ድንገት ስንባንን ያጠፋነው ጥፋት ሲታወሰን ቀጥሎ ያለውን የነቃውን ኑሯችንን ሲበጠብጠው ይኖራል።
እንዲህ ዓይነት ቡድኖች፣ የተግባሮቻቸው ገጽታ በራሱ እና በራሱ ብቻ ሲታይ ቅን ስለሚመስል ለወቀሳም ለሙገሳም አስቸጋሪ ነው፣ ከዚህም በተጨማሪ በየክስተቱ የሚሰለፉት ሰዎች በትምህርት ዘለቅነት፣ በነባርነት ወይም እንደ ገንዘብና ሥልጣን ባሉ በተመሳሳይ ማሕበራዊ እሴቶች የሚታወቁ ግለሰቦች በመሆናቸው በየአካባቢው በሚፈጠረው ችግር የፈጥኖ ደራሽ ጣልቃ ገብነታቸው ወዲያው ተቀባይነት ማግኘት ይችላል፣ የተጽእኖ አቅማቸው ግን እንደ የአካባቢው ይለያያል። አንዳንድ አካባቢዎች ትሥሥራቸው ጠንካራ ስለሆነ በቀላሉ አይደፈሩም። በግራም ሆነ በቀኝ ወደውም ሆነ ሳይወዱ፣ አስበውበትም ሆነ ሳያስቡ ግን በውጤቱ ተግባራቸው በአብዛኛው አፍራሽ ነው፣  አሰራራቸው ጀምስቦንዳዊ ነው  በድንገት ከፓራሹት እንደሚወርድ ይወርዳሉ፣ ባጭር ጊዜ ተደራጅተው የሚፈጽሙትን ፈጽመው ወደ ቀዬአቸው ይመለሳሉ፤ እንዲህ ዓይነት ኃይል ለመሆን የሚያስፈልጉ አብይ መስፈሪያዎች የሚከተሉት ናቸው፦
የተጨቋኝ/ተገፋሁ ባይ ትራኬ (Appealing narrative of the “oppressed”) እውነቱና ውሸቱ፣ የተደባለቀ ነው የጨቋኝ ተብየው ስሱ ጎን (Vulnerability of the so called “oppressor”) ይህ የድል ተስፋ ማርኬቲንግ ማግኛ ነው።
የዘመቻ ፊት አውራሪዎች (Vanguards for a campaign) በምግባራቸው ግብ እንጂ መርህ ጠያቂ ያልሆኑ አስተባባሪዎች (Pragmatic and goal oriented individual coordinators) ኃይል፣ ሥልጣን፣ ታዋቂነት፣ ተጽእኖ ፈጣሪነትን የተጠሙ አንደበተ ርቱአንና ደፋር ተግታጊዎች (Power mongers, cheap popularity seekers,…) እነዚህ ራሳቸውን ሰውረው ሊቀላቀሉ ይችላሉ።
ጥቂት የዋሃን አጃቢዎች “መናጆዎች” (Few innocent crowed) ሌሎች ፍጆታዎችና የግለሰብ ዓይነቶች እንደ አስፈላጊነቱና በየደረጃው ጥቅም ላይ ይውላሉ፣ ዘመቻው ይዘመታል፤ የተፈለገው ግብ ዘንድ ይደረሳል:: ከዚያ በኋላ በሚኖሩ እንቅስቃሴዎች “ተመልካች አለ”፣ “ተሳስተን ሊሆን ይችላል”፣ “የምንሰራው ስራ የረጅም ጊዜ ችግር ይፈጥራል”፣ “ተዉ የሚሉንን ሰዎች እንስማ” እና የመሳሰሉት አስተሳሰቦች የሌሉበት “ቡልዶዘራዊ” አካሔድ መሔድ ነው።
በውጤቱም ዚሮ ሰም (Zero-sum)  ድምዳሜ ላይ ይደረሳል። ዋናው ቁም ነገር የግጭት ባለ ድርሻዎች በማንኛውም የድርድር መንገዶች አለመስማማት ላይ ሲደርሱ “አልቦ ግብ ድርድር”  ላይ ለመቆም ይወስናሉ (አልቦ ማለት ዜሮ ማለት ነው)። በዚህም ቡድኖች በሙሉ ይከስራሉ፣ ይሁን  እንጂ አንደኛው ወገን የሚጠቀመው፣ ከሌላው ወገን በሚቀነሰው ነገር ነው፣ ባጭሩ “ጥቅሜ ያለው ጉዳትህ ውስጥ ነው” ማለት ነው፣ ወይም “ጉዳትህ ጥቅሜ  ነው” እና “ኪሳራህ ትርፌ ነው” የሚል የግጭቱ ባለድርሻዎች አይቀሬ ጉዳት ላይ ያተኮረ የግጭት መፍትሄ ነው። እንዲህ በመሆኑ የግጭት ባለድርሻ አረጋግጦ መሔድ የሚፈልገው ጥቅሙ የሚመሰረተው በሌላኛው ወገን ጉዳት ላይ መሆኑን ነው። በፖለቲካውና በንግዱ ዓለም ይህንን ምርጫ ለመምረጥ የሚገደዱበት ጊዜ አለ። ማህበራዊ ኑሮን ግን ያንኮታኩታል።
ጥቂት እንደ መፍትሄ
የ“ባላጋራን” አመለካከት ለመረዳት መመርመር። ትክክልም ሆኖ የተገኘ ያልተመለሰ ጥያቄ ካለ መመለስ። በዚህም ሒደት ውስጥ እውቅና ሊሰጣቸው የሚገባቸው በደሎች ካሉ እውቅና መስጠት
ገንቢና የተሻለ የግጭት መንገዶችን መፍጠር - ሶስተኛ ወገን መካከለኛነትን በባህላዊና በዘመናዊ መንገድም መፈጸም
የቡድን ኅሊናን የሚመሩ ሰዎችን ተጽእኖ ከመጀመሪያው መቅጨት - የቡድን ኅሊና ውጤት የሆኑ ተግባራትን በፍጥነትና በግልጽ ዋጋ እንደሚያስከፍሉ ማሳየት
ትክክለኛና ሊረጋገጡ የሚችሉ መረጃዎችን መስጠት። የማሕበራዊ ድረ-ገጾችንና የመገናኛ ብዙኃን አውታሮችን በመጠቀም ግለሰቦች ከቡድን ኅሊና ወደ ነጻ ራስ ገዝ ወይም በስምምነትና በውይይት በዳበረ የጋራ ሀሳብ እንዲያምኑ ማድረግ፣ ሆን ብሎ ሰው በመመደብ የተሳሳቱ ትራኬዎችን በጭብጦች እንዲፈተኑ በመጋበዝ የቡድን አባላት ወደ አስተውሎት የሚመጡበትን መንገድ ማመቻቸት።
የቡድን ኅሊና ወደ መዋቅራዊ ረብሻ/አመጽ/ (Structural violence) እንዳይሸጋገር የአገር ሰራዊትን፣ ፖለቲካውንና የኢኮኖሚውን መዋቅር የተሰባጠረ ቡድንን የሚያስተናግድ የሚሆንበትን ፖሊሲዎች መቅረጽ።
መካከለኛ የሆነን ቡድን ማብዛት፣ እንዲኖርም ጥረት ማድረግ፣ “ወይ ከኛ ጋር ነህ አለዚያ ተቃዋሚያችን ነህ” ከሚል አሰልቺ ሰንሰለት ተፈትቶ ሌሎችን መፍታት።


Page 8 of 546