Administrator
Monday, 10 November 2025 17:40
"ወደ ካምፕ ኑ ስቴዲየም መመለስ እፈልጋለሁ"
አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ እድሳት የተደረገለትን ካምፕ ኑ ስቴዲየምን ጎብኝቷል።
የወቅቱ የኢንተር ማያሚ አማካይ፣ ብዙ ታሪክ የሰራበትን ስቴዲየም በጎበኘበት ሰዓት ወደ ካምፕ ኑ መመለስ እንደሚፈልግ ተናግሯል።
የ38 ዓመቱ ተጫዋች በ2021 ነበር ከፋይናንስ ጋር በተያያዙ ምክንያቶች፣ ይህን ግዙፍ ስታዲየምና ክለቡን ለቆ ለመሄድ የተገደደው።
"ትላንት ምሽት በእጅጉ ወደ ናፈቅሁት ስፍራ ተመለስኩ" በማለት ካምፕ ኑን የገለፀው ሜሲ፤ ቦታው ብዙ ደስታዎችን ወደ ህይወቱ ያመጣበት ስፍራ መሆኑንም አንስቷል።
የስምንት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ተጫዋች ያኔ በ2021 የባርሴሎና ቆይታው የተቋጨው በእንባ ብቻ ነበርና፣ አሁን ወደዚህ የልጅነት ትዝታው ወደተኖረበት ስፍራ ተመልሶ "ከሚወዱኝና ከምወዳቸው" ጋር በወጉ "ደህና ሁኑ" መባባል እፈልጋለሁ ብሏል።
በእድሪስ አህመድ
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:38
"ያስለመድኳችሁን ፓስቲና ሻይ አላስቀርም"
የእኔ ነገር አላርፍም አይደል? እነሆ ስድስተኛ መጽሐፌን ላስመርቅ ነው። "ዥዋዥዌ" ብዬዋለሁ። አርባ ሰባት የዘመን ማስታወሻ ታሪኮችን የያዘ ነው፡፡ የተስተካከለና የተመሰቃቀለው፤ የተሳካና የተሰናከለው፤ የሚያምርና የሚያስቀይመው፤ የሚያስደስትና የሚያማርረው፤ የሚያኮራና የሚያሳፍረው ዘመነኛ ኢትዮጵያዊ ሕይወታችንን እንደ ወረደ በእነዚህ ታሪኮች ልሰንድ ሞክሬያለሁ፡፡
የዥዋዥዌ ምርቃት እንደ ሌላው ጊዜ በተንጣለለ አዳራሽ የሚቀርብና በቅንጫቢ ንባብ፣ በሙዚቃ እና ሌላ ጨዋታ የተሞላ ዝግጅት አይደለም። ቀለል ያለ የሽያጭና የፊርማ ፕሮግራም ነው። ያስለመድኳችሁን ፓስቲና ሻይ ግን አላስቀርም።
የፊታችን ቅዳሜ ሕዳር 6 ቀን 2018 አዲሱና ሸላዩ የጃፋር መጽሐፍት መደብር
(ለገሃር) እስክትመጡ እናቱን እንደናፈቀ ጨቅላ በር በሩን እያየሁ እጠብቃችኋለሁ።
ከእናንተ የሚጠበቀው ከቀኑ 8 እስከ 10 ሰዓት ባለው ጊዜ ያመቻችሁን መርጣችሁ ዘው ማለት ብቻ ነው።
ማስታወሻ!
የእኔን ዝግጅቶች ታድመው የሚያውቁ አንባቢዎቼ፣ ካልኩት ሰዓት ዝንፍ ብዬ እንደማላውቅ ምስክር ናቸውና፣ ታረፍዳለች ብላችሁ እንዳታረፍዱ።
በዚህ አጋጣሚ ምንግዜም ለማይለየኝ ድጋፍና ማበረታቻችሁ፣ ስልጡን ትችትና ወቀሳችሁ ምስጋናዬን ውሰዱ፡፡
ህይወት እምሻው-
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:38
“ጤንነቴ” የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ
የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን እየተካሄደ ነው
ጤና ሚኒስቴር “ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያን” በአዲስ አበባ የሳይንስ ሙዚየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን የመክፈቻ መርሃግብር ላይ ይፋ አድርጓል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት ፕሬዝዳንት ታዬ አስቀስላሴ፤ ጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ መሆኑን በመግለጽ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተዘጋጀዉን የዲጂታል ጤና ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተዋል። ጤና ሚኒስቴር፣ የጤና ስርዓቱን ለማዘመን እያደረገ የሚገኘውን ጥረትም አድንቀዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸዉ፤ ጅምሩ የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት በቴክኖሎጂ ዘመናዊ ለማድረግና ለህብረተሰቡ ትክክለኛ የጤና መረጃን ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እርምጃ መሆኑን በመግለጽ፣ የመድኃኒት አቅርቦትን ማሻሻልና በጤና ዲጂታይዜሽን እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አብራርተዋል።
አዲሱ የጤንነቴ የሞባይል መተግበሪያ ዜጎች ስለ መድሃኒት አቅርቦት፣ የጤና አገልግሎቶችና የጤና መረጃን በቀጥታ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። ተገልጋዮች እንክብካቤን በፍጥነት እንዲያገኙና አላስፈላጊ ጉዞን እንዲቀንሱ ይረዳል።
አገልግሎቱ በአዲስ አበባ በይፋ መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጣይም በመላ ኢትዮጵያ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጧል። አፕሊኬሽኑ የዲጂታል ጤና ስርዓትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ሲሆን፤ ለታካሚዎች የታዘዙ መድሃኒቶች የት እንደሚገኙ በቀላሉ መረጃ የሚሰጥ ነው ተብሏል፡፡
አፕሊኬሽኑ የዲጂታል ጤና ስርዓትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት፣ ለታካሚዎች የታዘዙ መድሃኒቶች የት እንደሚገኙ በቀላሉ መረጃ የሚሰጥበት ነው ተብሏል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:36
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን የያዘ መጽሐፍ ተመረቀ
ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላትን ይዟል
የሳይንስና ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላትን በአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች የያዘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።
በመዝገበ ቃላቱ የመጀመሪያው ዕትም ከ11 ሺህ በላይ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ቃላት አቻ ስያሜ ለመስጠት ጥረት መደረጉ ተነግሯል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዚዳንት ፕ/ር በላይ ካሳ እንዲሁም ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዶ/ር በለጠ ሞላ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ መጽሐፉ በየጊዜው እያደገና እየተሻሻለ የሚሄድ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ነው።
ሳይንሳዊ እውቀትን በሀገር ውስጥ ቋንቋ በመተርጎም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል፡፡
Published in
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:35
አፍሪካ ህብረት እየተባባሰ ለመጣው የማሊ ቀውስ ዓለማቀፍ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ
የአፍሪካ ህብረት በማሊ እየተባባሰ የመጣውን የፀጥታና የሰብአዊ ቀውስ ተከትሎ፣ አስቸኳይ አለም አቀፍ ጣልቃ ገብነት እንዲደረግ ጠይቋል።
አሸባሪ ቡድኖች የነዳጅ አቅርቦቶችን በመዝጋታቸው ሰላማዊ ዜጎችን ለችግር መዳረጋቸው ተነግሯል።
የአፍሪካ ህብረት የንፁሀን ዜጎችን መገደልና የሶስት ግብፃውያንን አፈና አውግዞ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።
የአፍሪካ ህብረት በሳሄል አካባቢ ለሚታየው ሽብርተኝነት የተቀናጀ አለም አቀፍ ምላሽ እንዲሰጥ ግፊት እያደረገ ነው፡፡
የማሊ መንግስትና ህዝብ ለሰላም፣ መረጋጋትና ልማት በሚያደርጉት ትግል ህብረቱ ከጎናቸው ለመቆም ቃል በመግባት አጋርነቱን አረጋግጧል።
Published in
ከአለም ዙሪያ
Tagged under
Monday, 10 November 2025 17:34
የጉራጌ ጦርነት 1867-1881
#በዘመናዊ የጉራጌ ታሪክ የቀቤና ቸሀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በመጀመሪያ የሚጠቀስ ገድል ነው ። ቀቤና በ1850ዎቹ በወልቅጤና በቸሀ መካከል “ ዘናበነር ” በሚባል ቀበሌ ከሰፈረ በኋላ ለቀበሌው የራሱን ስም የሰጠው አንድ የሀዲያ ማኅበረሰብ ነው።
#በ1860ዎቹ የቀቤናው ኢማም ሀሰን ኢንጃሞና የቸሀው ኢማም ኡመር በቅሳ የቀቤና አካባቢያዊ መንግሥት መሠረቱ ከ1860 ዎቹ መጀመሪያ እስከ 1881 ድረስ የቀቤና መንግሥት መሪዎችና ተከታዮች በጊቤና በአዋሽ ወንዞች መካከል የሚገኙ የሀዲያ የጉራጌና የኦሮሞ ሕዝቦችን በአንድነት ለማደራጀት በወሰዱት ብርቱ የፖሊሲ እርምጃ ከአጐራባቹ የሸዋ አካባቢ መንግሥት ጋር የአስራ አራት (1867-1881) ዓመታት ጦርነት ተዋጉ ።
#በዚህ ረገድ በ1867 መጨረሻ የምኒልክ ጦር በራስ ጐበና አዝማችነት በሶዶ ጉራጌ የመጀመሪያ ጦርነት ከፍቶ በድል ተመለሰ ። ነገር ግን በ1869 በቀቤና ፣ በወለኔ ፤ በገዳባኖ ፤ በአክሊል ፡ በምሁር ፤ በእዣ ፤ በቸ ሀ ፤ በእነሞር ፡ በኤነር ፤ በየጨሬት ፤ በጉመር ፤ በውሪሮ ፤ በስልጤ በመስቃን ፤ በዶቢና በዱላ ላይ በንጉሥ ምኒልክ አዝማችነት ጦርነት የከፈተው ታላቅ የሸዋ ሰራዊት በየአካባቢው በእነ አበጋዝ ደርሰሞ በተመራው የጉራጌ ጦር ተሸንፎ እንደ ተመለሰ በታሪክ ጸሐፊ አጥመ ጊዮር ጊስና በጉራጌ ትውፊት ተመዝግቦአል ። “
#በጉራጌ የትውፊት መረጃ መሠረት ፤ የ1869 የምኒልክ ሠራዊት በአጋዝ ደርሰሞ በተመራው የጉራጌ ጦር የተሸነፈው በጉመር አገር በዌራና በአረቅጥ በተካሄዱ ተከታታይ ጦርነቶች ነው።በታሪክ ጸሐፊ አለቃ አጥመ ጊዮርጊስ ዘገባ መሠረት ፣ በጥቅምት 1869 ንጉሥ ምኒልክ ብዙ ጦር አስከተለው ወደ ጉራጌ ዘመቱ ። በጥቅምት 21 ቀን የንጉሡ ሠራዊት አለቀ።
#አለቃ ዘነብ የሚባል አዋቂ መጽሐፈ ጨወታ የደ ረሰ የዚያኑ ዕለት ሞተ። ብዙ መኳንንት ሞቱ። የቸሀና የጉመር ሌሎችም ጉራጌዎች ብዙን ሠራዊት ማርከው ወደ ከምባታ ወደ ወላሞ ሸጡ። ከንጉሡ ጋራ ከዘመቻው የተመለሰው ከሶስት አንድ እጅ ብቻ ነው። በዚያን ጊዜ በሸዋ ያልተለቀሰበት ቤት አልተገኘም። ንጉሡም በኃዘን ተመልሰው ልቼ ገቡ፡፡
#ከ1867 እስከ 1881 በጉራጌና በሸዋ መካከል በተካሄደው ጦርነት ዋና ዋና የሸዋ ጦር መሪዎችና አዛዦች ንጉሥ ምኒልክ ፣ ራስ ወልዴ አሻግሬ ፤ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያት፤ባላምባራስ መኳንንት ወልደ ሚካኤል (በኋላ ራስ) ፤ ቀኛዝማች ውቤ ኤርገኖ ፤ ደጃዝማች በሻህ አቦዬ፡ ራስ ጐበና ዳጭ ፤ ፊታውራሪ ገረዶ ጐበና ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ነበሩ ።
#ከእነዚህ የጦር መሪዎችና አዛዦች ቀኛዝማች ውቤ ኤርገኖና ፊታ ውራሪ ገረዶ ጐበና በጦርነቱ ሞቱ። የራስ ጐበና ዳጭ ጦር አራት በተለያዩ ጊዜያት በኢማም ሀሰን ኤንጃሞ እጅ ተሸንፎ ተመለሰ ፤ አለቃ አጥመ ጊዮርጊስ እንደ መዘገቡት ፤ በ1877 ቀቤኖች ቀኛዝማች ውቤ ኤርገ ኖን ስለ ገደሉት በ1878 ደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ ፤ ደጃዝማች ገርማሜ ወልደ ሐዋርያትና ባላባራስ መኳንን ወልደ ሚካኤል በሌላ የቅጣት ዘመቻ ወደ ቀቤና ተላኩ። በመስከረም 1879 የደጃዝማች ወልዴ አሻግሬ ወንድም በጦርነቱ እንደ ተገደለና ደጃዝማቹ 3000 ከብቶች በም ርኮ ይዞ ወደ እንጦጦ እንደ ተመለሰ በወቅቱ ሸዋ የነበረው አንድ የውጭ አገር ጸሐፊ መዝግቦአል። የተባለው ጸሐፊ በሰኔ 1880 ጉራ ጌዎች በበኩላቸው ከሸዋ ጦር 400 ጠመንጃዎችን በምርኮ እንደ ወሰዱ ጨምሮ ጽፎአል።
#በ1880-1881 ኢጣሊያኖች ከሰሜን ጠረፍ፣ ሱዳኖች ደግሞ በምዕራብ ከወለጋና ከጐንደር ጠረፎች በአገሪቱ ላይ በአንድ ጊዜ በሶስት ግምባሮች ወረራ በከፈቱ ጊዜ ከጉራጌ ኢማም ሀሰን ኤንጃሞ አዋሽ ተሻግሮ “ ሸዋን ያቃጥላል በማለት ራስ ጐበና ዘምተው እንዲወጉት ተመ ከረ። ራስ ጐበናም ወደ ሀሰን ኢንጃሞ ዘመቱ ” ይህ የጐበና የ1880ው ዘመቻ በጉራጌዎች ላይ አምስተኛው ጦርነት ነበር።
#በመጨረሻ ራስ ጐበና የወሊሶን ተወላጅ ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮር ጊስ ዲነግዴን በኢማም ሀሰን ኤንጃሞ ላይ በማዝመት ጦርነቱን በመ ጋቢት 1881 ወደ ፍጻሜው አድርሰው ራሳቸው በሰኔ 1881 በድንገት ታመው በእንጦጦ ሞቱ።
#ከታሪክ አኳያ በ1881 የጉራጌ ጦርነት በሸዋ ድል መፈጸሙ ለምኒልክ ወታደሮችና ሹማምንት በሚቀጥሉት አመታት በደቡብና በምዕራብ ኢሉባቦር ፣ ከፋ ፣ ጋሞጐፋ፣ ሲዳሞና ባሌ ጨምሮ ብዙ አካባቢዎችን በፍጥነት በማዕከላዊ መንግሥት ሥር ለማምጣት በር ከፈተ።
►የኢትዮጵያ የገባር ታሪክና ጅምር ካፒታሊዝም፤ላጲሶ ጌ.ዴሌቦ፤192-4
Published in
ህብረተሰብ
Tagged under
Sunday, 09 November 2025 00:00
የጋዛ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ያተኮረ የ2 ቀን ጉባኤ በኢስታንቡል ይካሄዳል
የጋዛን ሰብዓዊ ቀውስ ለመፍታትና ዓለም አቀፍ ወዳጅነትን ለማጠናከር ያለመው ጉባኤ፤ በፈረንጆቹ ህዳር 11 እና 12 ቀን 2025 ይካሄዳል።
ከመላው ዓለም አራት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ይታደሙበታል በተባለው ጉባዔ ፣ የሰብዓዊ መብት ጠበቆች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮችና ምሁራን ይገኙበታል።
የጋዛ የወደፊት ዕጣ ፈንታ (the future of Gaza) በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ጉባኤው፤ በጋዛ አጠቃላይ ገፅታ፣ በተኩስ አቁም ስምምነቱን ቁመና፣ እንዲሁም እርዳታ በሚደርስበት ሁኔታ ላይ ጥልቅ ውይይት የሚደረግበት መሆኑ ተዘግቧል፡፡
Published in
ዜና
Tagged under
Monday, 03 November 2025 16:24
የቀድሞው የእግር ኳስ ኮከብ ዴቪድ ቤካም የግብርና ሥራ ጀመረ
ለዓመታት በዘመናዊቷ ለንደን ከተማ ሕይወቱን የመራው ዝነኛው እንግሊዛዊ ዴቪድ ቤካም አሁን ላይ በገጠራማዋ የኮትስዎልድስ መንደር በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ዙሪያ የግብርና ሥራን እያስፋፋ ነው።
ዛፎችን በመትከል፣ የአትክልት ስፍራዎን በመንከባከብ፣ ዶሮዎችን በማርባት እና ንብ በማነብ ሥራ ላይም ተሰማርቷል።
የግብርና ሥራው ላይ ቤተሰቡም እየተሳተፈ መሆኑን ሜትሮ የተሰኘው ሚዲያ ዘግቧል።
Published in
ስፖርት አድማስ
Tagged under
Sunday, 02 November 2025 06:26
ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን ሥነ ጥበባዊ ወግ
የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት 10ኛውን የወር ወንበር በድምቀት አከናወነ።
በአስረኛው የወር ወንበር
"ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን ሥነ ጥበባዊ ወግ"
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት (ወመዘክር) ማህበራዊ፣ፍልስፍናዊ፣ታሪካዊ፣ጥበባ
ዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት ጥልቅ ውይይት እና የሀሳብ ልውውጥ የሚደረግበት የወር ወንበር አስረኛ መርሐግብሩን ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በተቋሙ ብላታ መርስዔ ኃዘን ወልደ ቂርቆስ አዳራሽ አከናውኗል።
የወሩ ወንበር "ስለ አደባባይ ሐውልቶቻችን ሥነ ጥበብ ወግ" በሚል ርዕስ ሲሆን የውውይት መነሻ ሀሳብ
ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአለ ፈለገ ሰላም የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ዲን ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ ናቸው።
የአደባባይ ሐውልቶቻችን አሠራራቸው፣በታሪክ ውስጥ ያለፉበት መንገድ፣የታለመላቸውን ሀሳብ ዓላማ
የማስተላለፍ አቅማቸው፣ የተሰሩበት ዓላማ፣የፈረሱ ሐውልቶች፣በአደባባይ በቆሙ ሐውልቶቻችን ላይ የተነሱ ጉዳዮች እና ስለሐውልቶቹ ምን ተባለ የሚሉትን ሰዓሊ አገኘሁ አዳነ በገለጻቸው ከዳሰሷቸው ነጥቦች የሚጠቀሱ ናቸው።
የዕለቱ ታዳሚያን ንቁ ተሳትፎ ጎልቶ በወጣበት የወር ወንበር፤የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት መርሐግብሩን ከዚህ በላቀ መልኩም ለማስቀጠል ተቋሙ እንደሚሰራ እና የወር ወንበር ሁሌም በወሩ የመጨረሻ ሳምንት ቅዳሜ ላይ የሚዘጋጅ በመሆኑ ታዳሚያን ይገኙ ዘንድ የክብር ጥሪን አስተላልፈዋል።

Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና
Tagged under
Tuesday, 28 October 2025 00:00
ሎሚ
፩) ሎሚ የጉሮሮን ኢንፌክሽን ከሚከላከሉ ፍራፍሬዎች አንዱ ሲሆን የፀረ ባክቴሪያ ሀይል ስላለው በሻይ መልክ መጠጣት ከፍተኛ ጥቅም ይሠጣል።
፪) የሎሚ ጭማቂ የምግብ አለመፈጨትንና የሆድ ድርቀትን ይከላከላል።
፫) በምግብ ውስጥ ትንሽ ጠብታ ሎሚ ጨምሮ መጠቀም ደምን ያጣራል።
፬) ጥሩ የዕቃ ማፅጃ በመሆንም ያገለግላል።
፭) የሎሚ ጭማቂ በብርድ፣ በሳልና በትኩሳት ለሚሰቃዩ ሰዎች መድሀኒት ነው። እንዲሁም ትኩሳት በሚኖር ወቅት ቶሎ ቶሎ እንዲያልበን በማድረግ ያስታግስልናል።
፮) የጥርስ ህመም በሚያጋጥምበት ጊዜ የሎሚ ጭማቂ በህመሙ ቦታ ላይ በማድረግ እንደ ማስታገሻነት መጠቀም ይቻላል።
፯) በሎሚ ጭማቂ ድድን ማሸት ከድድ መድማት ችግርና ከመጥፎ የአፍ ጠረን ይታደጋል።
፰) ከውሀ ጋር የተቀላቀለ የሎሚ ጭማቂ መጠጣት ለኩላሊት ጠጠር እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
፱) የሎሚ ጭማቂ በተቃጠለው የሰውነታችን ቁስል ላይ በማድረግ ጠባሳ እንዳይኖር ለማድረግ ያስችላል።
፲) የሎሚ ጭማቂ ውስጣዊ መድማትን ይከላከላል። ምክንያቱ ሎሚ ፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው ነው። ስለሆነም የአፍንጫ መድማትን ለመከላከል በሎሚ ጭማቂ የተነከረ ጥጥ በአፍንጫ ቀዳዳ ውስጥ ከተው ለትንሽ ደቂቃዎች ማቆየት ይመከራል።
፲፩) ሎሚ ደምን የማጣራት አቅም ስላለው እንደ ወባና አተት ያሉ በሽታዎችን ይከላከላል።
፲፪) ሎሚ የፀረ ጀርምና ፀረ ባክቴሪያ ባህሪ ስላለው እርጅናን፣ የቆዳ መሸብሸብና ቆዳ ላይ ያሉ ትንንሽ ጥቁር ነጠብጣቦችን ያስወግዳል።
፲፫) የፀሀይ ጨረርን ለመከላከል የሎሚ ጭማቂ ፊትን መቀባት ጠቃሚ ነው።
፲፬) የሎሚ ጭማቂ ከማርና ውሀ ጋር በመቀላቀል መጠጣት ጥርት ያለ የፊት ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል።
፲፭) የሎሚ ጭማቂ የሰውነት ክብደትን ለመቀነስ ይረዳል።
፲፮) ሎሚ በቫይታሚን ሲ የበለፀገ ስለሆነ የአስምና የመተንፈሻ አካላት ችግር ላለባቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው።
፲፯) ሎሚ በውስጡ ፖታሲየም ስላለው ጭማቂውን መጠጣት የልብ ህመምን ለማስታገስ ይጠቅማል።
፲፰) ከፍተኛ የደም ግፊትን፣ ማዞርና ማቅለሽለሽን በመቆጣጠር አእምሮና ሰውነታችን ዘና እንዲል ያደርጋል።
፲፱) የራስ ቆዳ አናትን የሎሚ ጭማቂ መቀባት እንደ ፎረፎር፣ የፀጉር መነቃቀልና ከራስ ቅል ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመከላከል ይጠቅማል። እንዲሁም ፀጉራችን አንጸባራቂ እንዲሆን ያደርጋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
.
Published in
ዋናው ጤና
Tagged under

