Administrator

Administrator

ከህወሓት ታጣቂ ኃይል ያፈነገጠውና ራሱን ‹ሀራ መሬት› ብሎ የሚጠራው ኃይል፣ በህወሓት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመክፈት መዘጋጀቱ ተሰማ፡፡ በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር እቅድ መንደፋቸውም ታውቋል፡፡
ጀነራል ታደሰ ወረደ በፌደራሉ መንግሥት ይደገፋል ያሉት ይህ ታጣቂ ኃይል፤ በህወሓት ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመክፈት መዘጋጀቱን የፈረንሳዩ አፍሪኬ XXI ዘግቧል፡፡
ከመቀሌ በስተምስራቅ 110 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ላኮራ አቅራቢያ ከሚገኙት ግንባሮች የአንዱ አዛዥ የሆኑት ሸዊት ቢተው፣ "በዓመቱ መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን" ሲሉ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል፡፡
ታጣቂ ኃይሉ በአፋር ሁለት “ግንባሮች” ያሉት ሲሆን፤ ሦስተኛው ግንባር በምዕራብ ትግራይ ወይም በወልቃይት አዋሳኝ በሆነው ሽሬ አቅራቢያ የጦር ሰፈር መስርቷል ብሏል ዘገባው። ከነዚህ ቦታዎች ታጋዮቹ የህወሓትን አመራር ለማፍረስ “ጸጥ ያለ አብዮት” ሲሉ የገለጹትን እቅድ እያዘጋጁ እንደሆነ ጠቅሷል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሆነው ከተሾሙ አንድ መቶ ቀናትን ያስቆጠሩት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ በሰጡት አስተያየት፤ "ይህ ታጣቂ ኃይል ጥቃት ከከፈተብን ትንኮሳው ከፌዴራሉ መንግሥት ወይም ከአፋር ክልላዊ መንግሥት እንደተደረገ እንቆጥረዋለን" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
የሀራ መሬት አመራሮች ከፌዴራሉ መንግሥት ምንም አይነት ድጋፍና እገዛ እንደማያገኙ በተደጋጋሚ የሚናገሩ ቢሆንም፤ አፍሪካን ኢንተለጀንስ ከወራት በፊት ባወጣው ዘገባ ቡድኑ በፌዴራል መንግሥት እንደሚደገፍ ጠቁሟል፤ ማረጋገጫ ባያቀርብም፡፡ ሕወሓትም መንግሥት በአፋር ታጣቂ ኃይል እያደራጀብኝ ነው ሲል ይከሳል፡፡
(Andafta)
ፎቶ፡- ብርጋዴር ጄነራል ገብረ እግዚአብሄር በየነ (ወዲ አንጥሩ)፤ የሀራ መሬት አዛዥ
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
 
 
 
 
 
 
• በዓለም የባለጸጎች ዝርዝር ከ74ኛ ወደ 73ኛ ደረጃ ተሸጋግሯል
በአፍሪካ ቀዳሚ ቢሊየነር የሆነው ናይጄሪያዊው አሊኮ ዳንጎቴ፣ ባለፈው ሐሙስ ሃምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም የተጣራ ሃብቱ በ24 ሰዓት ውስጥ በ414 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ተዘግቧል፡፡
የዳንጎቴ ሃብት በአንድ ቀን ውስጥ ይህን ያህል ጭማሪ ያሳየው፣ የስኳርና ሲሚንቶ አክስዮን ዋጋው በመጨመሩና ኢንቨስተሮችን በመሳቡ ነው ተብሏል፡፡
የብሉምበርግ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ግዙፉ ኩባንያው ዳንጎቴ ሲሚንቶ ትልቁን ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን፤ የአክስዮን ሽያጩ የ9.99 በመቶ ጭማሪ በማሳየት በአንድ ቀን ውስጥ የተጣራ ሀብቱን ከ27.8 ቢሊዮን ዶላር ወደ 28.2 ቢሊዮን ዶላር እንዲያድግ አድርጎታል፡፡
በዚህም ዳንጎቴ በዓለም የባለጸጎች ዝርዝር ውስጥ ቀድሞ ከነበረበት የ74ኛ ደረጃ ወደ 73ኛ ደረጃ እንደተሸጋገረ መረጃው ይጠቁማል፡፡
የሲሚንቶ ድርሻው ብቻ 410 ሚሊዮን ዶላር መጨመሩ ታውቋል፡፡ የስኳርና የምግብ አክስዮን ድርሻውም የጨመረ ሲሆን፤ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ድርሻው ግን አልተለወጠም ተብሏል።
በኢትዮጵያ በ3 ቢሊዮን ዶላር የማዳበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም ከስምምነት ላይ የደረሰው ናይጄሪያዊው ቢሊየነር ዳንጎቴ፤ በናይጄሪያ አዲስ የባህር ወደብ ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደሆነ የቢዝነስ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
"ፍትሃዊ ጥያቄ በጦርነት ዛቻ ሊታፈን አይችልም"
ሕወሓት፣ የትግራይ ሕዝብ ፍትሃዊ ጥያቄ በጦርነት ዛቻ ሊታፈን አይችልም ሲል ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አቋሙን ገልጧል።
ከመሃል አገር ከሄደ የኃይማኖት ልዑካን ቡድን ጋር ሰሞኑን መወያየቱን የገለጠው ሕወሓት፣ የልዑካኑ አባላት በትግራይ ያለው "የሰላም ፍላጎት" እና "ዝግጁነት" ቀደም ሲል ከሠሙት የተለየ መኾኑን ተናግረዋል ብሏል።
ሕወሓት፣ በትግራይ በኩል ለግጭት የሚጋብዝ እንቅስቃሴ በሌለበት ኹኔታ ፌደራል መንግሥቱ የማስፈራራት ዘመቻ እያካሄደ፣ የታጠቁ ሃይሎችን እያደራጀና እያስታጠቀ ይገኛል በማለትም መክሰሱን ዋዜማ ዘግባለች፡፡
መንግሥት በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት ግዴታውን እስካልተወጣ ድረስ፣ የትግራይ ሕዝብ ከመሪ ድርጅቱ ጋር ለኅልውናውና ሉዓላዊነቱ ሠላማዊ የፖለቲካ ትግሉን ይቀጥላል ሲል ሕወሓት አቋሙን ገልጧል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የሩሲያ ጦር በዩክሬን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ የምሽት ጥቃት መሰንዘሩን ስፑትኒክ የመከላከያ ሚኒስቴርን መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት የሚሳኤሎችና ድሮኖች ክፍሎችን የሚያመርቱ ናቸው ሲል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በዩክሬን ወታደራዊ ኦፕሬሽን ዙሪያ ባወጣው መግለጫ፤ የሩሲያ የአየር መከላከያ ስርዓት ስድስት የአየር ቦምቦችንና 349 ድሮኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
የሩሲያ ጦር በዩክሬን ወታደራዊ አየር ማረፊያና የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል ላይ ጥቃት መሰንዘሩን የጠቆመው መግለጫው፤ የዩክሬን ጦር በግምት 1 ሺህ 195 ወታደሮቹን አጥቷል ብሏል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
May be an image of 1 person
 
 
 
 
ከቤተሰብ ፣ ከዘመድ ብሎም ከጎረቤት አንድ ሰው ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፍ፣ ሽኝቱና የቀብር ስነ-ስርዓቱ ምን መምሰል አለበት? የሚለው በየአካባቢው የተለያየ አይነት መልክ አለው።
በመዲናዋ እየተዘወተረ የመጣው የቀብር ስነ-ስርዓት ግን ኪስን የሚያራቁት ከመሆኑም በላይ “ሰርግ እና ሞት አንድ ነው” የሚለውን ብሂል ያስመሰከረ ሆኗል።
የቀብር መኪና እና የመኪና ዲኮር፣ የቀብሩ ስርዓት ወጪ፣ ምግብና ውሃ ለማቅረብ የሚወጣው ገንዘብ የትየለሌ ሆኗል።
በተለይም ቤተሰብ ተቀምጦ የሚያሳልፍባቸው የለቅሶ ቀናት ዘለግ ያሉ ከመሆናቸው አኳያ፣ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚወጣባቸው የለቅሶ ስነ-ስርዓቶችን ማየትም የተለመደ ሆኗል።
ይህ አካሄድ ግን ተገቢ ነው ወይ? የሚለው አጠያያቂ ነው።
እንደ ደረጃው ከ15 ሺህ ብር ጀምሮ እስከ 150 ሺህ በደረሰ ክፍያ የሬሳ ሳጥን ማቅረብ፣ ስነ-ስርዓቱን ማስፈፀምና ዲኮርን የያዘ የጥቅል አገልግሎት መኖሩን የቀብር አስፈፃሚው መርዕድ ያስረዳል።
ይህ ስነ-ስርዓት ሲጠናቀቅ ሀዘኑን የተጋራና ሽኝት ያደረገ ታዳሚ ወደ መኖሪያ ቤት በማቅናት የተዘጋጀውን ምግብና ውሃ በመጠቀም ‘የሟችን ነብስ ይማርልን’ ሲል ሀዘኔታ የተላበሰ ምኞቱን ያደርሳል።
ይሁንና ለቀስተኛው ወደ ቤት ሲመጣ የሚዘጋጀው ምግብ በቤተሰብና በጎረቤት ህብረት፣ በዕድሩ ትብብር ታግዞ አሊያም በምግብ ዝግጅትና አቅርቦት ድርጅቶች በኩልም ሊከናወን ይችላል።
በምግብ ዝግጅትና አቅርቦት ድርጅቶች በኩል ባለው አሰራር፣ ለለቅሶ ከ150 ሰው ጀምሮ የሚገኙባቸው የሐዘን ቤቶች ላይ እንገኛለን የሚሉት የአገልግሎቱ አቅራቢ አህመድ ናቸው። ይህም ለምግብ በ1 ሳህን 495 ብር ሲያስከፍል፣ ከፍ ሲል እስከ 1 ሺህ 200 ብር የሚያስከፍል እንደሆነ ለኢቲቪ ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የድንኳን፣ የወንበርና የተለያዩ ወጪዎችን ሐዘንተኞች ከሐዘኑ ባሻገር የሚጋፈጧቸው የወጪ ዝርዝሮች ናቸው ይላሉ።
ይህ ወጪ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መሆኑንና አንዱ አንዱን እያየ እየተለመደ የመጣ ጎጂ ባህል መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ያስረዳሉ።
ይሁንና በርካታ እድሮች ይህን አጉል ልማድ ለማስቀረት በሐዘን ወቅት የቧንቧ ውሃና ለሐዘንተኛ ቤተሰብ ብቻ የሚሆን መጠነኛ ምግብ ማዘጋጀት እንደሚገባ መመሪያ አውጥተው ያላከበሩትን በመቅጣት ላይም ይገኛሉ።
(በአፎሚያ ክበበው #EBC)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
"መንግሥት የቡና ዘርፉን የሚጎዳ የትኛውንም ዓይነት እርምጃ አይቀበልም"
ኢትዮጵያ የትራምፕን ቀረጥ ተከትሎ አማራጭ የቡና ገበያዎችን እየቃኘች መሆኑ ተገለጸ፡፡
የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሻፊ ዑመር፣ የአሜሪካ አስተዳደር ፖሊሲ ከሀገሪቱ የወጪ ንግድ ገቢ 35 በመቶ የሚሆነውን የሚነካ በመሆኑ አማራጭ ገበያዎችን መመልከት ግድ ሆኗል ብለዋል፡፡
ለዚህም ባለሥልጣኑ ከነደፋቸው ዕቅዶች መካከል ወደ ሩቅ ምስራቅና መካከለኛው ምስራቅ የቡና ገበያን ማስፋት፣ በተያዘው በጀት ዓመት 20 አዳዲስ የቡና ወጪ ንግድ መዳረሻዎችን መክፈት፣ እንዲሁም ከቻይና፣ ጃፓን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጀርመንና ጣሊያን ጋር ግንኙነትን ማጠናከር ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የቡና ዘርፉን የሚጎዳ የትኛውንም ዓይነት እርምጃ አይቀበልም ሲሉ የቡናና ሻይ ባለሥልጣን ምክትል ዳይሬክተር ለሺንዋ ተናግረዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
በለንደን ዳይመንድ ሊግ የአንድ ማይል ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አሸነፈች።
ጉዳፍ ጸጋዬ የኢትዮጵያን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
• ከ39 ዓመታት በኋላ የሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ ነው ተብሏል
"ኪን ኢትዮጵያ - የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት" በሚል መሪ ሀሳብ፣ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቀው የኪነ ጥበብ ቡድን የፊታችን እሁድ ወደ ቻይና ያቀናል፡፡
መርሐ ግብሩን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) እና አርቲስት ካሙዙ ካሳ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ÷ መንግስት የኪነ ጥበብ ዘርፉ በሀገር ግንባታ ሥራ ላይ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ትክክለኛ ገጽታዋን ለማስገንዘብ የምታደርገው ጥረት በኪነ ጥበብ መታገዝ እንዳለበት ገልጸው÷ የዚሁ አካል የሆነው የኪነ ጥበብ ቡድን የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ ቻይና እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ቡድኑ በቻይና ቤጂንግና ናንጅንግ ከተሞች የኢትዮጵያን ባህል እንደሚያስተዋውቅ ጠቅሰው፤ መርሐ ግብሩ በመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት ጭምር የተደገፈ መሆኑን መግለጻቸውን ፋና ዘግቧል፡፡
ለቱሪዝም መስፋፋትና ለኢንቨስትመንት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ይህ የኪነ ጥበብ ጉዞ፤ በተለያዩ ዘርፎች ጥሩ ግንኙነት ያላቸውን የኢትዮጵያና ቻይና ትስስርን የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው÷ ከ70 በላይ የሚሆኑ ከያኒያን የሚሳተፉበት የኪነ ጥበብ ጉዞ፤ ከ39 ዓመታት በኋላ የሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ ሲሆን፤ ከ50 በላይ የሚሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎችና ጥበባት እንደሚቀርቡበት አመላክተዋል፡፡
በተጨማሪም በጉዞው ከትርኢቶች ባሻገር ኢትዮጵያ የአልባሳት ዲዛይን፣ የቡና ቅምሻ እና የአመጋገብ ባህሏን ታስተዋውቅበታለች ብለዋል።
አርቲስት ካሙዙ ካሳ በበኩሉ÷ የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ አራት ወር የፈጀ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ገልፆ፤ በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን ቱባ ባህሎች የሚያስተዋውቁ አዳዲስ ስራዎች ተካተውበታል ማለቱን ዘገባው አመላክቷል፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
የዉሀ የመጥለቅለቅ አደጋን 40 በመቶ መቀነስ ችሏል
በደቡባዊ እንግሊዝ የሚገኘዉ ሳዉዘርን ዋተር የተባለ በውሃና ፍሳሽ ዙሪያ የሚሰራ ድርጅት ኤ.አይ ቴክኖሎጂን ለተለያዩ አገልግሎቶች በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ አስታዉቋል።
ድርጅቱ ቴክኖሎጂዉን በመጠቀም በመሬት ስር የሚቀበሩ የዉሀ መስመሮችን ደህንነትን ይከታተላል። ኤስ.ኤ.ኤም 4 የሚሰኘዉ ሥርዓት፣ የዉሀ መስመሮቹ ላይ የብልሽት አደጋ ከመከሰቱ በፊት የጥገና ስራዎችን ለመከወን ያስችላል።
ሳዉዘርን ዋተር በድርጅቱ ድረ ገጽ ባወጣዉ መረጃ፤ በፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦዎች ላይ ከ32 ሺህ በላይ ሴንሰሮች መግጠሙን ገልጿል። ሴንሰሮቹን ከኤ.አይ ቴክኖሎጂ ጋር በማጣመር የቱቦዎቹን ወቅታዊ ሁኔታ መከታተል ይቻላል። በዚህም የፍሳሽ ማስወገጃዎች የመደፈን አደጋ ካጋጠማቸዉ ወዲያዉኑ ማሳወቂያ ይሰጣል። ችግሮች የመፈጠር አዝማሚያ ካላቸዉም አስቀድሞ በማስጠንቀቂያ መልዕክት ያሳዉቃል።
ድርጅቱ የኤ.አይ ሥርዓትን መጠቀም ከጀመረ ወዲህ የዉሀ የመጥለቅለቅ አደጋ 40 በመቶ መቀነሱን አስታዉቋል። ቴክኖሎጂዉ የፍሳሽ አወጋገድን ከማዘመን ባሻገር የዉሀ አጠቃቀምን ለማሻሻል እንዲሁም የሀብት ብክነትን ለመቀነስ አጋዥ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
(Ethiopian Artificial Intelligience Institute)
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
May be an image of water heater
 
 
 
 
Page 1 of 765