Administrator
አሜሪካዊው ራፐርና አስቴር አወቀ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ በሸራተን ያቀነቅናሉ
ቴክሳስ ቁጭ ብዬ መርካቶን አያለሁ
በአመት 9.1 ቢ. ዶላር ገቢ ባስገኘው አየር መንገዳችን እንኮራለን
የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ የኡጋንዳ አየር መንገድ ስራ አስፈጻሚ ሆነዋል።
.
አቶ ግርማ ዋቄ ሊፈርስ የደረሰውን አየር መንገድ እንዲያቀኑ ነው ከፍተኛ ሀላፊነት የተጣለባቸው።
????????
ታዲያ ከሰሞኑ ለኡጋንዳ ፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ ነበር: ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳ ሪፖርት ነው ያቀረቡት። አቶ ግርማ አየር መንገዱ በሙስና የተነሳ መበስበሱን ገልፀዋል። ኡጋንዳ አየር መንገድ ካሉት 8 አውሮፕላኖች ውስጥ 2ቱ ብቻ እንደሚሰሩ አሳውቀው፤ አየር መንገዱ አደጋ ላይ መሆኑን አቀረቡ።
የኡጋንዳ ፓርላማ "መቼ ነው ከክስረት ወጥተን ማትረፍ የምንጀምረው?" ብሎ በጉጉት ሲጠይቅ አቶ ግርማ "እስከ 2033 ትርፍ የሚባል ነገር አይታሰብም፤ እቅጩን እወቁት" አሉ።
????????
ይህንን ስንሰማ በአመት 9.1 ቢሊየን ዶላር ገቢ ባስገኘው Ethiopian Airlines /የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንኮራለን ስሙንም ከፍ በኩራት እናደርጋለን።
በአመታቶች ውስጥ የስራ አስፈጻሚዎቹ ስልታዊ አመራር፤ የሰፋተኞቹ ታታሪነት እና የመንግስታት ድጋፍ ባበረከቱት አስተዋጽኦ አየር መንገዳችን ከአለም አቀፍ ስመጥር አየር መንገዶች አንዱ ሆኗል።
ዌል እንግዲህ
ባለበት የሚፀና በርትቶ የቆየ ነውና አየር መንገዱ በብርታቱ እንዲቀጥል የሚስተዋሉ የመንገደኞች መጎሳቆል፤ የሻንጣ መጥፋት፤ የሰራተኞች በሙስና መጠመድ፤ የሚታወቅበት hospitality መቀነስ ሊሰራባቸው ይገባል።
Zemelak Endrias-
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
አዲሱ የዓለም ሥርዓት፡ ደራሲው ዓለም በአንድ ንጉሥ እንድትመራ ጥሪ አቀረቡ
በደራሲ ንጉሥ ታደለ ድሪባ የተዘጋጀው እና 340 ገጾችን የያዘው “አዲሱ የዓለም ሥርዓት” (New World Order) የተሰኘ መጽሐፍ በቡራዩ ኩሪፍቱ ሪዞርት በይፋ ተመረቀ። መጽሐፉ ዓለም በአንድ የገንዘብ ሥርዓት፣ በአንድ ንጉሥ እና በአንድ የአመራር እዝ ስር ስትመራ የበለጠ ፍትሃዊነትና እኩልነት ይሰፍናል የሚል አከራካሪ እናለየት ያለ ሃሳብ ያነሳ ሲሆን፣ ደራሲው ለዚህ አዲስ ሥርዓት ራሳቸውን እንደ ዋነኛ እጩ አቅርበዋል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የሀገራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰርፀፍሬ ስብሀት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጡት ዶክተር ገዛኸኝ ፀጋው፣ መጽሐፉ የምርምር አስተሳሰብን ለማሳደግ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ሊወያዩበት የሚችሉ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍራት ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ይህ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ ተዘጋጅቶ ከሀገር አልፎ ለዓለም አቀፍ አንባቢያን እንዲደርስ ወደ 13 ተጨማሪ ቋንቋዎች የተተረጎመው መጽሐፍ የምረቃ መርሐ-ግብር ታዋቂ አርቲስቶች፣ ምሁራን እና የፈጠራ ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
የኦርቶዶክስ መንፈሳዊ ትውፊት እና የዘመናዊ አስተዳደር
ቢል ጌትስ ሮቦቶችና ኤአይ ላይ ግብር እንዲጣል ጥሪ አቀረቡ
የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትስ ሮቦቶች እና አርቲፊሻል ኢንቴሊጀንስ (AI) የሰዎችን ስራ በከፍተኛ ፍጥነት እየተኩ በመሆናቸው፣ መንግስታት በነዚህ ቴክኖሎጂዎች ላይ ግብር የመጣል ውሳኔ እንዲያስቡበት ጥሪ አቀረቡ። ጌትስ ባወጡት አዲስ ጽሁፍ እንደገለፁት፣ እንደ ደንበኞች አገልግሎት፣ የህግ ረዳትነት እና ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ያሉ ስራዎች በኤአይ እየተተኩ ነው፤ በቀጣይም በኮንስትራክሽን እና በሆቴል ዘርፍ ያሉ አካላዊ ስራዎች በሮቦቶች ሊወሰዱ ይችላሉ። አሁን ያለው የግብር አሰራር ኩባንያዎች ሰራተኞችን በሮቦቶች እንዲተኩ ያበረታታል፤ ምክንያቱም ሰራተኛ ሲቀጠር የሚከፈለው የደመወዝ ግብር ሮቦት ሲገዛ ስለማይከፈል ነው።
በመሆኑም በሮቦቶች እና ኤአይ አጠቃቀም ላይ ግብር እንዲጣልና የሚሰበሰበው ገንዘብ በቴክኖሎጂው ምክንያት ስራቸውን ላጡ ሰዎች መልሶ ማሰልጠኛና ድጋፍ እንዲውል ሀሳብ አቅርበዋል። ቢል ጌትስ በሮቦቶች ላይ ግብር እንዲጣል ጥሪ ሲያቀርቡ የመጀመሪያቸው አይደለም፤ እ.ኤ.አ በ2017 ሰራተኞችን በሮቦት የሚተኩ ኩባንያዎች ሰውየው ይከፍል የነበረውን ያህል ግብር ሊከፍሉ ይገባል ሲሉ ተከራክረው ነበር። አሁንም መንግስታት ከፍተኛ የስራ ማጣት ችግር ከመከሰቱ በፊት አስቀድመው ተዘጋጅተው አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
ከጎርፍ አደጋው 10 ደቂቃዎች በፊት የተሰጠ ውሳኔ
*ርዕሰ መምህሩ የ900 ተማሪዎችን ህይወት ታድገዋል
በኔፓል ኑዋኮት ወረዳ በሚገኘው ትሪቡቫን ትሪሹሊ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት ራጄንድራ ዳዋዲ፣ አሰቃቂው ጎርፍ ትምህርት ቤቱን ከመደምሰሱ ከ10 ደቂቃ በፊት ባደረጉት ፈጣን ውሳኔ የ900 ተማሪዎችን ህይወት ታድገዋል። በዕለቱ ከጧቱ 3፡10 ላይ ጎርፍ እየመጣ መሆኑን የሚገልጹ ጥሪዎች እንደደረሷቸው፣ ለሰከንድ ሳይወላውሉ ተማሪዎቹ በፍጥነት ወደ ተራራ እንዲሸሹና ወደ ትምህርት ቤት እየመጡ ያሉ ባሶች እንዲመለሱ አዘዋል። መምህሩ “ውሳኔያችን በ10 ደቂቃ ቢዘገይ ኖሮ፣ ተማሪዎቼን ጨምሮ ሁላችንንም ዛሬ በሕይወት አታዩንም ነበር” ሲሉ አስደናቂውን አጋጣሚ ተናግረዋል።
የ16 ዓመቷ ተማሪ ዩኒሻ አማትያ እና ጓደኞቿ አደጋው ከመድረሱ ከጥቂት ሰከንዶች በፊት አምልጥዋል። ተማሪዎቹ በትምህርት ቤቱ ጀርባ ባለው ጠባብ መወጣጫ በኩል ወደ ተራራው ሲወጡ፣ ከኋላቸው የነበረው ገበያ በደቂቃዎች ውስጥ በጎርፍ ተጠራርጎ ሲወሰድ በዓይናቸው ተመልክተዋል። በተራራው ላይ ከፍ ብለው በመሸሸጋቸው ምክንያት ለሁለት ቀናት ያህል ከውጭው ዓለም ተቆራርጠው የቆዩ ቢሆንም፣ የልጅቷ አባት በስልክ ሲያገኛት በደስታ አልቅሷል። በኋላም በሄሊኮፕተር ተነስተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ከ2,400 በላይ ሰዎች በጠፉበት በዚህ አሰቃቂ የጎርፍ አደጋ ትምህርት ቤቱ ሙሉ በሙሉ በጭቃና በፍርስራሽ ተሸፍኗል። ተማሪዋ ዩኒሻ በሕይወት በመትረፏ ብትደሰትም የትምህርቷ ነገርና የጓደኞቿ መለያየት አሳስቧታል። ርዕሰ መምህር ዳዋዲ በበኩላቸው፣ ያንን አጣዳፊ ውሳኔ ባይወስዱ ኖሮ የትምህርት ቤቱ ደወል ብቻውን እንደሚቀርና ትልቅ እልቂት ይከሰት እንደነበር ገልጸዋል።
የደባርቅ ከተማ የኮሪደር ልማት ከ450 ሚ. ብር በላይ ድጋፍ አገኘ
የደባርቅ ከተማን የቱሪዝም መስህብነት ለማሳደግና ጽዱ፣ ውብ እንዲሁም ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የበርካታ ወገኖችን ድጋፍና ትብብር በማግኘት ላይ ይገኛል። ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች ተገኝተዋል። በዚህ ታላቅ መድረክ በጥሬ ገንዘብና በአይነት ከ450 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን፣ የሃብት ማሰባሰብ ሂደቱ አሁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
በዚሁ መድረክ ታዋቂ ባለሀብቶችና ድርጅቶች ከፍተኛ አጋርነታቸውን ያሳዩ ሲሆን፣ የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ፍቅሬ 20 ሚሊዮን ብር፣ አቶ በላይነህ ክንዴ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢአይካ (BIKA) 15 ሚሊዮን ብር በመለገስ ግንባር ቀደም ተሳትፎ አድርገዋል። ይህ የልማት እንቅስቃሴ ደባርቅን በቱሪዝም፣ በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የበለጠ ተወዳዳሪ የሚያደርጋት ሲሆን፣ በቀጣይም ነዋሪዎችንና የከተማዋን ወዳጆች ያካተተ ሰፊ የልማት ምዕራፍ እንደሚቀጥል የከተማዋ ልማት ኮሚቴ አስታውቋል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
ከ300 ሚ. ዶላር በላይ የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች በጂቡቲ ወደብ መታገዳቸው ተገለጸ
*አስመጪዎች ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገናል አለ
በጂቡቲ ወደብ ከ8 ወራት በላይ ቆመው በሚገኙና ግምታቸው ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሚሆኑ ከ4,500 በላይ የከባድ ጭነትና የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ምክንያት፣ አስመጪዎች ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ተሽከርካሪዎቹ ወደ አገር እንዳይገቡ የታገዱት አገሪቱ በተፈጥሮ ጋዝ አጠቃቀም መመሪያ ምክንያት በቤንዚንና ናፍጣ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ በወጣው አዲስ መመሪያ ነው። በመሆኑም ከ100 በላይ አስመጪዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ደብዳቤ በማስገባት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ተማፅነዋል።
እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ፣ የጉምሩክ ኮሚሽንም ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን በተደጋጋሚ ጠይቋል። መመሪያው ከመውጣቱ በፊት ተሽከርካሪዎቹን ያዘዙት አስመጪዎች በየቀኑ ለተጨማሪ የኪራይና የወደብ ወጪ እየተዳረጉ ይገኛሉ። በተጨማሪም እገዳው በመቀጠሉ ምክንያት መንግሥት ማግኘት የሚገባውን ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ገቢ ያጣል ተብሏል።
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
https://t.me/AdissAdmas
የኢትዮጵያ ወጣት አትሌቶች በኬንያው የዞን 5 ኦሎምፒክ ደምቀዋል
በኬንያ ሲካሄድ የቆየው የሁለተኛው አፍሪካ ዞን 5 ወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ትናንት ምሽት ተጠናቋል። ኢትዮጵያ በውድድሩ ካስመዘገበቻቸው አጠቃላይ 12 ሜዳሊያዎች ውስጥ 6ቱን (4 ወርቅ እና 2 ብር) በአትሌቲክስ አግኝታለች።
የወርቅ ሜዳሊያዎቹን በሴቶች 800፣ 1500፣ 3000 እና 5000 ሜትር የእርምጃ ውድድር ስናገኝ፤ የብር ሜዳሊያዎቹ ደግሞ በወንዶች 1500 እና 3000 ሜትር ተመዝግበዋል።
