ርዕሰ አንቀፅ

Rate this item
(6 votes)
 የተረት - አባት የሆነው ኤዞፕ እንዲህ ይለናል፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ተኩላዎች ተመካከሩና መልክተኞች ወደ በጎች ላኩ፡፡ የተኩላዎቹ ልዑካን እበጎች መንደር ደረሱ፡፡ በጎች ተኩሎች መጡብን ብለው ተሸሸጉ፡፡ አድፍጠው ጋጣቸው ውስጥ አድብተው ተቀመጡ፡፡ ተኩሎቹ ግን ረጋ ብለው፣ አደብ ገዝተው፣ “በጎች አትደንግጡ፤ እንደምን…
Rate this item
(8 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት መነኩሲት ጎኅ ሲቀድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሊሄዱ ይነሳሉ፡፡ አንድ ዛፍ አጠገብ ሲደርሱ ተንበረከኩና ሁለት እጃቸውን በልመና መልክ ዘርግተው፤ ጸለዩ፡፡“አምላኬ ሆይ! ድንገት ከወትሮው ፀሎቴ አሳንሼብህ ይሆናል፡፡ የከዋክብት ብዛቱን የውቂያኖስ ስፋቱን፣ የሙሴ በትሩን፣ የገብርኤል ተዓምሩን፣ የእመቤታችን አማላጅነቷን የምታውቅ፣…
Rate this item
(7 votes)
አንዳንድ ተረቶች በአንድ ወቅት አልደመጥ ሲሉ፣ በሌላ ወቅት ተደግመው መነገራቸው ግድ ይሆናል፡፡ የሚከተለውም እንደዚያው ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን ሦስት አህዮች በጠፍ ጨረቃ ሰፊ መስክ ላይ እየጋጡ ሳሉ፤ ሦስት ጅቦች የሚበላ ፍለጋ ሲዘዋወሩ ያገኙዋቸዋል፡፡ ጅቦቹ ገርሟቸዋል፡፡ አንደኛው ጅብ፤ “እነዚህ አህዮች እንዴት…
Rate this item
(6 votes)
ከዕለታት አንድ ቀን አያ ጅቦ አራት ልጆቹን ማለትም መዝሩጥን፣ ማንሾለላን፣ ድብልብልንና ጣፈጦን ይዞ በሌሊት መንገድ ይሄዳሉ፡፡ እየተጓዙ ሳለ ድንገት ከቤቷ የወጣች አህያ ያገኛሉ፡፡ይሄኔ አባት ጅብ፤“ልጆቼ ሆይ! እንግዲህ እኔ በጣም አርጅቻለሁና፣ ይቺን አህያ እኔ ነኝ የምበላት! እናንተ ራቅ ራቅ ብላችሁ ትጠብቁኛላችሁ”…
Rate this item
(3 votes)
አንድ የፈረንጆች ተረት አለ፡፡በማፍቀር ዕድሜ ላይ ያሉ ጐረምሶች፤ “የት ሄደን ነው ራት የምንገባበዘው?” ሲባባሉ፤ አንደኛው፤“ኦሽን-ቪው ሆቴል እንሂድ” አለ“ለምን?” ሲሉት፤“እዚያ ቆንጆ ቆንጆ፣ የሚታዩ ኮረዶች አሉ!” አለ፡፡ሁሉም ተስማሙና ሄደው በርቸስቸስ ሲሉና ሴት ሲያጫውቱ አመሹ፡፡ይህ በሆነ ከአሥር ዓመት በኋላ እንደዚሁ ተገናኙ፡፡ “የት እናምሽ?”…
Rate this item
(2 votes)
(የሚጬነ ከናስ አቻ ቦታ እሜስ ዴሬቄነ ኩቶስ አይፌ ዞኡዋ እሜስ) የወላይታ ተረት ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ደቃቃ ጥንቸል፤ እህል ውሃ ፍለጋ በጫካ ውስጥ ስትዘዋወር፤ አንድ ዝንጀሮ ታገኛታለች፡፡ ጥንቸሏ ግዙፍ ስላልሆነች በየቅጠላ ቅጠሉ ውስጥ እየተሹለከለከች መሄድ እንደምትችል ዝንጀሮ ያውቃል፡፡ ሆኖም አንድ…
Page 1 of 77