Thursday, 18 April 2024 20:48

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የክብር ሽልማት ምርጥ 5 ዕጩዎች ታወቁ !

Written by 
Rate this item
(3 votes)

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የክብር ሽልማት ምርጥ 5 ዕጩዎች ታወቁ !


በቃል መልቲሚዲያ አማካይነት ‹‹ክብር ሽልማት›› በሚል ሀሳብ ለደራሲዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች ዕውቅና ለመስጠት ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት የክብር ሽልማት አዘጋጆች ካለፈው ዓመት አንስቶ ባለሙያዎች፣ በድረገጽ እና በሌሎች የመገናኛ አውታሮች እንዲጠቁሙ ሲያደርግ ነበር፡፡

በዚህም መሰረት በሚዲያና በድርሰት ዘርፍ የተጠቆሙ ሰዎችን በድረገጽ ላይ በማውጣት ባለፉት 30 ቀናት ዳኞችና ህዝብ እንዲመርጡ ማድረጋችን ይታወሳል፡፡

አጠቃላይ በ16 ዘርፎች በባለሙያዎችና በሕዝብ ድምጽ ሲሰጥባቸው የቆየ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ስርዓቱም ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5 ቀን  2016 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡

ከእያንዳንዱ ዘርፍ ከተጠቆሙ ሥራዎችና  ሠራተኞች ውስጥ ምርጥ 5ቱን ለመምረጥ ከህዝብ የተገኘን 40 ከመቶ ድምጽ እንዲሁም በዳኞች የተሰጠን 60 ከመቶ አንድ ላይ በማድረግ፣ ክብር ሽልማት በ16 ዘርፎች ምርጥ አምስት ያላቸውን  ባለሙያዎች ዛሬ ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ያደርጋል፡፡  

ክብር ሽልማት የዳኝነት ስርዓቱን ሙያዊ ለማድረግ፣ ትክክለኛ የመዳኘት አካሄድን ተከትሏል፡፡ በተለይ  መስፈርቶችን ጊዜ ወስዶ በጥንቃቄ  በማዘጋጀትና መስፈርቶቹንም ደግሞ ደጋግሞ በመከለስ የተጣራ ማወዳደሪያ በመቅረጽ የዕውቅና ሥነ ስርዓቱ በጥብቅ የዳኝነት መስፈርት እንዲከናወን አድርጓል፡፡

ሁሉም ተወዳዳሪዎች በ2015 ባለው የሥራ ውጤታቸው እንዲዳኙ ተደርጓል፡፡ ይህንንም ዕውን ለማድረግ በክብር ሽልማት ስር የተዋቀረው የጥናትና ምርምር ማዕከል፣ የባለሙያዎችን የህይወት ታሪክ እንዲሁም ናሙና ስራዎችን በቋት ውስጥ በማጠራቀም ለዳኝነቱ ስራ ተገቢ መላ ዘይዶ የማወዳደሩን ስራ በተገቢው መልኩ አከናውኗል፡፡

የዳኝነት ሥራውም ፍጹም ምስጢራዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ባለሙያዎችን ከሥራቸው አንጻር ብቻ በማየት ወደ ውድድሩ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ዋናው የክብር ሽልማት ግብ የሰራ የልፋቱን ያህል እንዲመሰገን፣ እንዲታወቅና እንዲከበር ማድረግ ሲሆን ይህንንም ባህል በመላ አገሪቱ እንዲስፋፋ እንሻለን፡፡ ስለሆነም ትናንት በልዩ ልዩ መንገድ  ሥራቸውን በትጋትና በችሎታ የተወጡ ሰዎችን ዛሬ ደግሞ ዕውቅና አግኝተው ሊሸለሙ ይችላሉ፡፡

ዛሬ የዕውቅና ካባ የሚደርቡ ደግሞ ነገ ታሪካቸው እየተሰነደ ለትውልዱ ተምሳሌት ይሆናሉ፡፡ ክብር ሽልማት በቂ ልምድ ባካበቱ ባለሙያዎችና የቦርድ አባላት የሚመራ ሲሆን ለሥራችን መቃናት የረዱንን ሁሉ ከልብ ማመስገን እንወዳለን፡፡ በስተመጨረሻም ከዚህ በሁሉም ዘርፍ የተመረጡትን ባለሙያዎች ድምጽ እንድትሰጡ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ፡፡  

በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ ምርጥ 5 የሚከተሉት ናቸው።
የዓመቱ ምርጥ ልብ ወለድ
፩ ቤባንያ (ዓለማየሁ ገላጋይ)
፪ ማሙሽ (ማይክል አዝመራው)
፫ ጠያይም መላዕክት (ቤተ ማርያም ተሾመ)
፬ ወድቆ የተገኘ ሀገር (ይፍቱሥራ ምትኩ)
፭ አሌፍ ቤት (ወንድሙ ገዳ)

የዓመቱ ምርጥ አጫጭር ልብወለድ
፩ አሳንቲ (ምርት ባቦ)
፪ አዎ እሱ ጋ ያመኛል (አድሃኖም ምትኩ)
፫ ናፍቆት (እስከዳር ግርማይ)
፬ አዝማሪው ልቤ (ጌታነህ ደጉ)
፭ እሰሩኝ (መሠረት ባህሩ)

የዓመቱ ምርጥ ግለታሪክ መጽሐፍ

፩ ኅብር ሕይወቴ (ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ)
፪ ተስፋዬን ፍለጋ (ማርቆስ ተግይበሉ)
፫ ሕይወቱ የአብራሪነት የአውሮፕላን ጠለፋ ትዝታዎቹ (ካፒቴን ልዑል አባተ)
፬ ዓለማየሁ እሸቴ (በወሰን ደበበ ማንደፍሮ)
፭ የህይወት ጎዳና (ሕይወት ጥላሁን)

የዓመቱ ምርጥ ተውኔት
፩ በዓሉ ግርማ ቤርሙዳ (ውድነህ ክፍሌ)
፪ የሌሊት ሙሽሮች (ውድነህ ክፍሌ)
፫ የደፈረሱ ዓይኖች (ውድነህ ክፍሌ)
፬ ነገሩ አይቆምም (ድረስ ደሳለኝ)

የዓመቱ ምርጥ ግጥም
፩ እናርጅ እናውጋ (ጌራወርቅ ጥላዬ)
፪ ፍቅር ሰው ማኅሌት (ዮሐንስ ኃ/ማርያም)
፫ ፍለጋ (ፍቃዱ ጌታቸው)
፬ እንኳን መሃይም ሆንኩ (በለው ገበየሁ)
፭ ምርቃት (ዓለምነህ ረጋሳ)

የዓመቱ ምርጥ የፊልም ድርሰት
፩ ዶቃ (ቅድስት ይልማ እና ቤዛ ኃይሉ)
፪ ጋዜጠኛዋ (ሳሙኤል ተሻገር)
፫ ወዳጅ (ግዛቸው ገብሬ)
፬ ገምዛ (ሙሉቀን አረጋ)
፭ ቅኔ (ቅድስት ሳህለ)

የዓመቱ ምርጥ የወግና መጣጥፍ መጽሐፍ
፩ ችቦ (ዶክተር ዓለማየሁ ዋሴ)
፪ እያል ድሬ (ሚልኬሳ ሙሜ)
፫ ኦብሲቱ (ሐሊ ሙዘይን)

የዓመቱ ምርጥ የዘፈን ግጥም
፩ ላይለ ኩሉ (ዳን አድማሱ)
፪ አትከልክሉኝ (አብነት አጎናፍር)
፫ ገላጋይ (ዮሓና)
፬ እርፍ በይ (ዘሩባቤል ሞላ)
፭ ማንነቴ (ኤልያስ መልካ)

የክብር ሽልማት በሥነጽሑፍ ዘርፍ የሕይወት ዘመን እጩ
፩ ኃይለመለኮት መዋዕል
፪ ሳህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም
፫ ፀሐይ መላኩ
፬ ሲሳይ ንጉሱ
፭ አዳም ረታ

የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የመዝናኛ ዩቲዩብ
፩ ዶንኪ ቲዩብ
፪ ማያ ቲዩብ
፫ መሪ ፖድካስት
፬ ማራኪ ወግ
፭ ከናቲ ጋር

የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው
፩ እሸቴ አሰፋ
፪ ግርማ ፍስሃ
፫ ምንይችል እንግዳ
፬ ወንድዬ ካሳ
፭ መንሱር አብዱልቀኒ

የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ዝግጅት አቅራቢ
፩ ኤደን ገብረሕይወት
፪ ሰይፉ ፋንታሁን
፫ አስካለ ተስፋዬ
፬ ዳናዊት መክብብ
፭ ዮናስ ከበደ

የዓመቱ በጋዜጠኝነት ዘርፍ የሕይወት  ዘመን ዕጩ
፩ ማዕረጉ በዛብህ
፪ ታምራት ገብረጊዮርጊስ
፫ ጸጋዬ ኃይሉ
፬ መርዕድ በቀለ
፭ አማረ አረጋዊ

የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት
፩ ጦቢያ
፪ ውሎ አዳር
፫ ትዝታችን በኢቢኤስ
፬ ፋና ቀለማት
፭ ጠያቂው ሲጠየቅ

የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት
፩ ሁሉ አዲስ
፪ የጥበብ መንገድ
፫ ታዛ
፬ መሰንበቻ
፭ ለዛ

የሬዲዮ መዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ
፩ ትዕግስት በጋሻው
፪ ወንድሙ ኃይሉ
፫ ብርሃኑ ድጋፌ
፬ ብስራት ከፈለኝ
፭ ሰለሞን ጫላ

ከአንድ እስከ አምስት የተጻፉት እንዲሁ ቅደም ተከተል እንጂ ደረጃቸውን አያሳይም፤ የአጻጻፍ ቅደም ተከተል እንጂ።
ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ሊንክ እየገባችሁ የእናንተን አንደኛ ትመርጡ ዘንድ ተጋብዛችኋል።
????????????????????????
https://kibershilemat.com

Read 1034 times