Thursday, 18 April 2024 20:40

ሠርተን ለባዳ አገር ነዳጅ? ወጪ መቀነሻ ሃሳብ አለኝ! መቀነሻ ሃሳብ አለኝ!

Written by  ተስፋዬ ድረሴ
Rate this item
(0 votes)

 ”አገሬ ሆይ፤ የነዳጅ ወጪሽን ለመቀነስ፤ መታጠፊያዎችሽን ቀንሺ፥”
                            
    1) ከሰፈሬ እንደ ወጣሁ ወደ ሜክሲኮ አቅጣጫ ለመሄድ፤ ወደ ቀኝ ነድቼ አንድን አደባባይ መዞር አለብኝ። ከአደባባዩ ወደ ግራ ተጠምዝዤ እንደነዳሁ ከሰፈሬ ከወጣሁበት መንገድ ጋር ትይዩ የምሆነው 500 ሜትር ከነዳሁ በኋላ ነው። ይህ፤ ቀጥተኛ መንገድባለመኖሩ የምነዳው፤ ተጨማሪ መንገድ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስወጣኝ ልነግራችሁ ነው!
    ያዙ’ንግዲህ:- በ 1 ቀን 500 ሜትር፤ በትናሹ በአንድ አመት (365 ቀናት) /500 x 365= 182,500ሜትር። ይህ ስንት ኪሎ ሜትር ነው? አንድኪሎ ሜትር 1000 ኪሎ ሜትር በመሆኑ ለ1000 እናካፍልና - ቅድም በሜትር
ያገኘነው ውጤት ኪሎ ሜትሩን ይነግረናል። 182500÷1000= 182 ኪሎሜትር። ይህ ርቀት ቢሾፍቱ/ደብረዘት 2 ደርሶ መልስ ያስኬደኛል። 45x2=90x2=182 ኪሎሜትር! ትርፉ 2 ኪሎ ሜትር ዞርዞር የምልበት ይሆናል።
-------
ወደ 182 ኪሎ ሜትሩ እንመለስ። በአምስት ዓመት ውስጥ ስንት ትርፍ ርቀት ነድቻለሁ? 5 x 182=910 ኪሎ ሜትር!
-------
ወደ ቤንዚን ወጪ እንለውጠው። መኪናዬ በሊትር 10 ኪሎ ሜትር ትጓዛለች። 910 ኪሎ ሜትሩን 10 (አስር) ቦታ ብንሸነሽነው።910÷10=91 ሊትር ሳልፈልግ እጠቀማለሁ።
-----
ወደ ብር እንለውጠው። አንድ ሊትርቤንዚን 78 ነው? ረሳሁት። ብር 78 × 91= 7,098 ብር (በአምስት አመት ‘ትርፍ’ በመንዳቴ ምክንያት አወጣለሁ።
---------
ምዕራፍ 2
***
500 ሜትሩ ከቤቴ እንደወጣሁ፤ አንድ አደባባይ ስዞር የምነዳው ነው። መሀል ከተማ ጉዳዮቼን ከውኜ ለመመለስ በትንሹሁለት ‘የግዴን የምዞራቸው አደባባዮች ወይም መዞሪያዎች ያጋጥሙኛል። አንዳንዶቹ ርቀቶች ግድንግድ ኤሊ በሚመሳስሉ ድንጋዮች በተዘጉ መታጠፊያዎች ምክንያት
የምጓዛቸው ተጨማሪ ርቀቶች ናቸው።
----
ስለዚህ ቅድም ብር 7,098 የነበረው አመታዊ ወጪዬ የተጨማሪዎ ሁለት መዞሪያዎች ሂሳብ ሲደመርበት ስንትይሆናል? 7,098 + (7,098x2) 14,196= ብር21,294!
------
ይህን በዶላር አስሉት። ስንት ይመጣል? እሱ ገንዘብ ማለት ነዳጅ ለምንገዛቸው አገሮች ‘የገበታ ለአገር’ ሽልማት ነው።
ምዕራፍ 3
እኔ በአንድ መኪና በአመት የማወጣውን ነገርኳችሁ። በከተማችን ውስጥ ያሉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ መኪናዎች ስንት ዶላር ለባለነዳጅ አገሮች እንደሚሸልሙ - ገምቱ። ላስጠና ይሆን እንዴ? ነዳጁ የእኛ ቢሆን ኖሮ ባልቆጨኝ፥ ባላበሳጨኝ፥ የቀረች ፀጉሬን ባላስነጨኝ ነበር!
-------
አገሬ ሆይ፤ የነዳጅ ወጪሺን ለመቀነስ፤ የቻልሺዉን ያህል፤ መታጠፊያዎችሽን ቀንሺ፥ !ድንጋዮችሽን አንሺ፥መንገድ መዝጋትን መፍትኼ ያረግሺበትን
ፍልስፍና ፈትሺ! “You-turn መዞር ክልክል ነው?” የሚሉ ምልክቶችሽን ጨርቅ አልብሺ! እሺ?
---
አልኩሽ በቃ!
---
ግልባጭ - ለመንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣናት የፖሊሲ ውይይት መድረክ አዘጋጆች።
---
(ፎቶ ጨማምሩበት! “አሁን እዚህ - ይኼ ከልካይ ምልክት ምን ይሰራል?” የምትሏቸውን ፎቶዎች ደርቡበት)።ይኼ ርዕስ ከራሴ ወርዶልኛል! ትዝብቴን
ስላጋራዃቸሁ ደስ ብሎኛል!
----
ምክረ ሃሳቤን ጨርሻለሁ! ወረፋዬም ደረሰ - መብራት በቴሌ ብር ለመክፈል ሰልፍ ላይ ነበርኩ!! ከምኔው ደረሰኝ? ቻዎ! ኢመቻችሁ!!!



Read 596 times Last modified on Thursday, 18 April 2024 20:43