የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ ”የሥራ መልቀቂያ አስገቡ“ በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰተኛ መሆኑን የባንኩ ባለድርሻ አካላት ገለጹ፡፡
የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ የሥራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን የሚገልጹ መረጃዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች መሰራጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሆኖም መረጃው ሙሉ በሙሉ ሃሰተኛ ነው ብለዋል - ለባንኩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት የሥራ መልቀቂያ አስገቡ በሚል የተሰራጨው ሃሰተኛ መረጃ የባንኩን ጥቅም እንደሚጎዳ የጠቆሙት የባንኩ ባለድርሻ አካላት፤ ሃሰተኛ መረጃውን ያሰራጩ ማህበራዊ ሚዲያዎችንና ግለሰቦችን በህግ እንደሚጠይቁ አመልክተዋል፡፡