Saturday, 10 February 2024 10:27

ዋልያ ቢራና ሮፍናን አጋርነታቸውን ለ18 ወራት አራዘሙ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

10 አገር አቀፍ ኮንሰርቶችን ለማቅረብ ማቀዳቸውን ገልጸዋል

የሃይንከን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ብራንድ የሆነው ዋልያ ቢራና ዝነኛው ኢትዮጵያዊ ሙዚቀኛ፣ ዜማ ደራሲና አቀናባሪ ሮፍናን ኑሪ፤ “ዘጠኝ” በተሰኘ የሙዚቃ አልበም ላይ አጋርነታቸውን በማራዘም፣ ከትላንት በስቲያ

ሐሙስ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡
ዋልያ ቢራና ሮፍናን አጋርነታቸውን ለቀጣይ 18 ወራት እንደሚቀጥሉ የተጠቆመ ሲሆን፤ በዚህ ጊዜ ውስጥም 10 አገር አቀፍ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በክልል ከተሞች ለማቅረብ ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል -

በሰጡት መግለጫ፡፡
በቅርቡ የሚለቀቀው የሮፍናን አልበም፣ በሙዚቃና በኪነጥበብ የኢትዮጵያን ልዩ ታሪክና ባህል የሚገልጽ ነውም ተብሏል፡፡
በዋልያ ቢራና በሮፍናን መካከል “ስድስት” በተሰኘው አልበም በነበረው ጥምረት የክልል ቱሪዝምን ያደመቁ ስድስት ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ተመልካቾችን ከመሳብም አልፎ ብዙ የሥራ ዕድል መፈጠሩን ባወጣው

መግለጫ ያስታወሰው  ዋልያ ቢራ፤ በተጨማሪም በሮፍናን ማስተርክላስ የሮፍናንን የሙዚቃ ዕውቀት መሰረት አድርጎ፣ ከአንጋፋ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር፣ ከሙያዊ ሥነምግባር እስከ የራስን ብራንድ ፈጠራ

ድረስ ከዋልያ ጋር በመሆን ያለውን ልምድ ማካፈል እንደቻለ አመልክቷል፡፡ሙዚቀኛው ሮፍናን በ“ዘጠኝ” አልበሙ የያዛቸው “ሐራንቤ” እና “ኖር” የተሰኙ አልበሞች በአንድ ቀን እንደሚወጡ የጠቆመው የዋልያ

ቢራ መግለጫ፤ ይህም ሮፍናንን በኢትዮጵያ ሁለት አልበሞችን በአንድ ቀን ያወጣ የመጀመሪያው አርቲስት እንደሚያደርገው ጠቅሶ፣ ዋልያ ቢራም የዚህ ታሪክ አካል በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል ብሏል፡፡
“ከሮፍናን ጋር ያለን ጥምረት የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ከመሥራት ባሻገር የአገራችንን ባህል ማጎልበት፣ ዕምቅ የራስ ጥበብን ማውጣት፣ የሥራ ዕድል መፍጠርና መልካም አመለካከትንም መቅረጽ ነው፡፡” ብሏል -

ዋልያ በመግለጫው፡፡ 

Read 894 times