Thursday, 04 January 2024 00:00

“ሆኖ መገኘት” የተሰኘው በሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ የሕይወት መርሆች ዙሪያ የሚዳስሰው መጽሐፍ ተመረቀ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

“ሆኖ መገኘት” የተሰኘው በሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የህይወት መርሆች እና በሚያስተዳድራቸው ሆቴሎች መነሻ ተደርጎ በአቶ መልካሙ መኮንን እና በአቶ ፋሲል መንግስቴ በጋራ የተዘጋጀው መፅሀፍ በዛሬው እለት በሀይሌ ግራንድ ሆቴል ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት ተመርቋል፡፡
በመፅሐፉ ምረቃ ላይ የመፅሃፉ ፀሀፊ ከሆኑት እንዱ አቶ መልካሙ መኮንን እንደገለጹት የመፅሃፉ ዋና ዋና አላማዎች እያንዳንዳችንን ለስኬት የሚያበቁ እና ሊኖሩን የሚገቡ መርሆዎች እና ባህርያትን በተግባር ከተፈተነው ከሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የሀይወት ተሞክሮ የተቀዱና ተሰናድተው የቀረቡ የስኬት ሚስጥራትን ለአንባቢያን ማድረስ እንደሆነ ተናግረዋል
እንዲሁም መፅሐፉ የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ባህልን በድርጅት ውስጥ ማስረፅ ወይም መገንባት ለድርጅት ዘላቂነት እና ተወዳዳሪነት ዋነኛ መንገድ እንደሆነ ማሳየት ሌላኛው አላማው እንደሆነም ሌላኛው የመፅሃፉ ፀሀፊ አቶ ፋሲል መንግስቴ ገልጸዋል
መፅሀፉን ለአንባቢያን ለማብቃት ከ1 አመት በላይ እንደፈጀ መፅሀፉ ላይ በድርሰት የተሳፉት አቶ ደሳለኝ ስዩም የገለፁ ሲሆን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ የመፅሃፉ ደራስያን ና አዘጋጆች ይህን አስተማሪና አነቃቂ መፅሀፍ ለአንባቢያን በማዘጋጀታቸው ያለውን ትልቅ ምስጋናውን ገልጿል

Read 880 times