Saturday, 30 December 2023 20:52

የጎንደር የባህል ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  የጎንደር የባህር ፊስቲቫል በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አዘጋጁ ብራና ኤቨንትስ አስታወቀ፡፡ “እናትዋ ጎንደር” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የጎንደር ፌስቲቫል ከጥር 4-6 ቀን 2016 በአዲስ አበባ የኢትዮ ኩባ የወዳጅነት አደባባይ በድምቀት እንደሚካሄድ አዘጋጁ ብራና ኢቨንትስና ፕሮሞሽን ሰሞኑን በኢዮሜር ሆቴል ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ ለሶስት ቀናት በሚቆየውና በአዲስ አበባ በሚካሄደው የጎንደር የባህል ፌስቲቫል ላይ የጎንደር ቱባ ባህሎች አልባሳት፣ ምግብ፣ ጌጣጌጥ፣ የቤትና የውጭ የመገልገያ እቃዎች ሙዚቃና ሌሎችም ጎንደርን የሚገልፁ ሁነቶች ለእይታ እንደሚቀርቡ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
በዚህ ፌስቲቫ ላይ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባስልጣን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ሙያዊ ድጋፍ ያደርጉለታ ተብሏል፡፡ ፌስቲቫሉ በአዲስ አበባ መካሄዱ በተለያዩ ችግሮች ተዳክሞ የነበረውን ቱሪዝም ከማነቃቃቱም በላይ ጎንደርን ቱባ ባህል ሀይማኖታዊና ትውፊታዊ ስርዓት አለባበስ አመጋገብና ሙዚቃ ብሎም አጠቃላይ የጎንደርን ጥንታዊ ታሪክና ቅርስ እዚሁ አዲስ አበባ ማየትና እውቀት መጨበጥ እንዲችል ይረዳዋል ሲሉ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ አዘጋጆቹ አክለውም ከጥር 11-13 ቀን 2016 በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ከጎንደር ከተማ  አስተዳደር ጋር በጋራና በድምቀት ለማክበር በቦታው እንደሚገኙ የጠቆሙ ሲሆን ከጥር 4-6 ቀን 2016 በአዲስ አበባ የሚከበረውን የጎንደር የባህል ፌስቲቫል ማህበረሰቡ በቦታው በመገኘት እንዲጎበኝና እንዲዝናና አዘጋጆቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡


Read 732 times