Sunday, 10 December 2023 00:00

ከጦርነት የሚገላግለን ሁነኛ የሰላም መፍትሔ እንጨብጣለን

Written by  ዮሃንስ ሰ
Rate this item
(0 votes)

ችግርን ማወቅ ግማሽ መፍትሔ ነው ይባላል። ግን መፍትሔ አይደለም። እናም፣ ጦርነትን መግታትና ሰላምን መፍጠር ከፈለግን፣ የተጨባጭ የመፍትሔ መንገዶችን ለይተን መጥረግ አለብን። ወደዚያው ነው የምንደረደረው።ለ መ ን ደ ር ደ ር ም ፣ … በ ተ ደ ጋ ጋ ሚ ያየናቸውና ልንጨብጣቸው የሚገቡ ግንዛቤዎችን በቅድሚያ እንመልከት፡፡ለይስሙላ ወይም አምነንበት፣ ልማድ ሆኖብን አልያም የጨዋ መንገድ እንደሆነ በማሰብ፣ “ግጭትና ጦርነት ይቁም” ብለን እንናገራለን፡፡ እንሰማለን፡፡“የሰላም መዝሙር” እንከፍታለን፡፡ የማህሙድ ዜማ አልመጣላችሁም?
ጦርነት፣ የስቃይና የእልቂት ገሀነም የመሆኑ ያህል ሰላም ደግሞ፣ የጤናና የፍቅር ገነት ነውና ለሰላም የቱም ያህል ሙገሳና ቅዳሴ አይበዛበትም፡፡ ብንዘምርለት ለጤናችን ለህይወታችን እንደ መዝፈን ነው፡፡ ችግሩ ምንድ ነው?
የሚያስተማምን እርጋታና የሚሰነባብት ሰላም አላገኘንበትም፡፡ደርግ “ያለምንም ደም ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚል የሰላም መዝሙር ይዞ ነበር የመጣው፡፡ ነገር ግን ሰላምን አላገኘም፡፡ ለአገሪቱም ሰላም አልሰጣትም፡፡ ብዙም ሳይቆይ አገሪቱን በደም ጎርፍ አጨቀያት፡፡ “አብዮታዊት ኢትዮጵያ ወይም ሞት!” እያለ ፎከረባት፡፡የደርግ ዘመን፣ የጦርነት ብቻ ሳይሆን የረሀብ ዓመታት የበዙበት ዘመን መሆኑአይገርምም። ድሀ የነበረችውን አገር የድሀ ድሀ አድርጓታል። በንጉሡ ዘመን ወደነበረችበት ሁኔታ ተመልሳ ለማገገም ከደርግ በኋላ 10 ዓመት ፈጅቶባታል።
ታዲያ በደርግ የመጨረሻ ዓመታት ላይ የሰላም መዝሙር ቢመጣ ይገርማል? አገሪቱ ሰላም ናፍቋታል፡፡ የጦርነት እልቂትና ውድመት ይብቃን ተብሎ ምህላ ተዘምሯል።ኢህአዴግም ሲመጣ በተራው ሰላም መዝሙር ይዞ ነው የመጣው፡፡ የቀንና የሌሊት ዘፋኑ “ሰላምና መረጋጋት” የሚሉ ቃላት ነበሩ፡፡ በእርግጥም ትንሽ ሰላም ተገኝቶ ነበር፡፡ ከሰላም ጋርም አገሪቱ አንሰራርታለች። አልዘለቀም እንጂ።ምን ለማለት ፈልጌ ነው? የሰላም እጦት ስር የሰደደ ችግር ነው።የግጭትና የጦርነት፣ የአመፅና የግድያ፣ የጥቃትና የእስር ፖለቲካ፣ የዘንድሮና የአምና ጉዳይ ብቻ አይደለም፡፡ከታሪክ የመማርና የማንበብ ብልሃት ባይኖረን እንኳ፣ የቅርብ የቅርቡን ማስታወስ ያቅተናል?

ወይስ ማስታወስና ማሰብ አንፈልግም?
“ሰላምና ዕርቅ፣ ይቅርታና መግባባት” የሚሉ ቃላት ስንቴ እየተደጋጋሙ ከአንደበታችን እንደተወጡ፣ ስንቴ እንደ ጣዕመ ዜማ እንደሰማናቸው፣ እንደ ፀሎትና እንደ ውዳሴ ስንቴ እንደደገምናቸው አስታውሱ፡፡ ጊዜው ሩቅ አይደለም፡፡ የዛሬ አምስት ዓመት ነው፡፡
ከአገር ውስጥ ሰላም በተጨማሪ፣ ከጎረቤት አገራት ጋር የወዳጅነትና የፍቅር አበቦች፣ የዘንባባ ዝንጣፊዎች አካባቢውን ሁሉ በመልካም መዓዛ እያወዱ አየር ላይ እንደተወዛወዙ ታስታውሳላችሁ፡፡በአዲስ አበባና በአስመራ፣ ሁለቱ አገራት የሰላም ሰርግና ምላሽ እየተቀባበሉ፣ ግብዣ እየተጠራሩ ከጓዳ እስከ አደባባይ፣ ከተሞቻቸውን አፅድተው አሳምረው ለድግስ ሲጨነቁና ሲጓጉ ተመልክተናል፡፡
ጥሩ ነው፡፡ ደስ ይላል፡፡ ግን… የሆነ አሳዣኝ መንፈስ በውስጡ ይዟል፡፡ “ዛሬ ጤንነት ይሰማኛል” ብለን የጠገበ ድግስ አናዘጋጅም፡፡
በጤንነት እጦት ስንሰቃይ ካከረምን በቀር፣ የጤንነት እልልታና ጥሩንባ አናስጮህም፡፡ የጤንነት ድግስ በጤንነት እጦት መሰቃየታችንን ይጠቁማልና ነው፡፡የሰላም መዝሙርም እንዲሁ ነው፡፡ አስደሳች ቢሆንም በውስጡ የሀዘን ስሜት የተሸከመ ነው፡፡ ሰላም እየራቀን ወይም ከሰላም እየራቅን እልቂትና መከራ በየተራና በተደራራቢ ስለበዛብን ነው የሰላም ምህላ የምንደጋግመው። አገሪቱም እጇን ወደ ሰማይ የምትዘረጋው ሰላም እየናፈቃት ነው። ሰላም ሲመጣም ብርቅ ድንቅ እየሆነብን ነው “ምህላችን ተሰማ፣ ስለታችን ደረሰ” ብለን ለሰላም
በምህላና በምስጋና የምንዘምረው፣ የምንፈነድቀውና በፈንድሻና በአበቦች የምንቦርቀው፡፡ይህን የጦርነት እና የሰላም ዑደት ከታሪክ ማየት ይቻላል። ከዛሬ አምስት ስድስት ዓመት ወዲህም፣ አሳዛኙ ዑደት ተደግሟል።ወደ ቅራኔና ወደ ጭፍን ጥላቻ፣ ከዚያም ወደ ግጭትና ጦርነት እየተደጋገምን እንገባለን፡፡ ሰላም እናጣለን፡፡ ከሰላም እንርቃለን፡፡ በዚያው ልክ የሰላም ምህላና ውዳሴ እየተደጋገመ ይመጣል፡፡ የሰላም ተስፋና ትንሽ እፎይታ ስናገኝም፣ ብርቅ ድንቅ ሆኖብን እንዘምራለን። ጥያቄው ምንድነው?
ከሰላም ምኞት ባሻገር አስማማኝ የሰላም መፍትሔ አንጨምርበትም፡፡ ጭራሽ እንጣላበታለን፡፡እዚያው በዚያው የሰላም መዝሙራችንን የቅራኔ ሰበብ እናደርገዋን። እንበሻሸቅበታለን። እነ እከሌ “ፀረ ሰላም ናቸው” ብለን ለመሳደብ እንጠቀምበታለን።
የጦርነት መቀስቀሻ እንዲሆንልን እንፈልጋለን። መዝሙራችን፣ ቀሽም ቅኔ ሆነ ማለት ነው፡፡
የሰላም መዝሙር ነው። ግን ፀብ ፍለጋም ነው። የፍቅር ጥሪ ነው የጦርነት ዛቻ ነው።በሌላ አነጋገር፣ የሰላም ምህላና መዝሙር ጥሩ የመሆኑ ያህል፣ እንቆቅልሽም ነው።ከመነሻው ለምን ከሰላም እንርቃለን? ብለን መጠየቅ አለብን-እንቆቅልሹን ለመፍታት።ለዚህ ጥያቄ የሚመጡልን ፈጣን መልሶች ምን ምን እንደሆኑ ማሰብ ትችላላችሁ፡፡ መፍትሄ ለማበጀት የሚጠቅሙ መልሶች አይደሉም፡፡ ለምን ወንጀል ተፈፀመ? ለሚል ጥያቄ “ሌቦችና ነፍስ ገዳዮች ናቸው ተጠያቂዎቹ” የሚል መልስ በጭራሽ መፍትሄ አይሆንም፡፡አዎ፣ ወንጀለኞች ናቸው ተጠያቂዎቹ፡፡ ግን ትክክኛ ውንጀላ ብቻ መፍትሔ አይወልድልንም፡፡ ክፋቱ ደግሞ፤ ጭፍን ውንጀላ እንጨምርበታለን፡፡ እንዲሁ በጭፍን አወግዘንና ወንጀልን አንዳች እርካታ ለማግኘት ወይም ከሀሳብ ለመገላገል ካልተመኘን በቀር፣ ጭፍን ስሜት መፍትሄ አይመጣልንም፡፡ሰላም አጥተን በጦርነት ስንሰቃይም፣ ጣት ለመቀሰር እንጣደፋለን፡፡ የምንወነጀለው አካል ላይ ሁሉንም ጣጣ ለመጫን እንቸኩላለን፡፡ሁሉም መከራ በመንግስት ላይ መፍረድ እንችላለን፡፡ የመንግስት ባለስልጣናትን፣ የየዘመኑ ገዢ ፓርቲዎችን መውቀስና መወንጀል ቀላል ነው፡፡ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞችንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማውገዝም አይከብድም፡፡ ነገር ግን ጦርነት ለማስቀረትና ሰላም ለማስፈን አልቻልንም፡፡ መንግስትና ተቃዋሚዎቹ ብዙ ጥፋት ቢኖራቸውም በማውገዝና በማስወገድ ብቻ ሰላም አልፈጠርንም፡፡
የውጭ ኃይሎችንና ታሪካዊ የአገር ጠላቶችን መርገመም፣ እንችላለን፡፡ አውሮፓና አሜሪካ ራሺያና ቻይና፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጣልቃ
የሚገቡ የአምባገነንን መንግስት ደጋፊዎች ናቸው ብለን መፍረድ አያቅተንም፡፡ የአረብ አገራትና ጎረቤቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የዓመፅና የተቃውሞ ድርጅቶች አስታጥቀው የሚያሰማሩ ናቸው ብለንም እናወግዛለን፡፡የውጭ ኃይሎች ቅጥረኛ፣ አምንደኛ፣ ከሃዲና ባንዳ ብለን ተቃዋሚዎችን በማውገዝ… እነሱንም በማጥፋት የሰላም እፎይታ ብናገኝ ትልቅ ግልግል ነበር፡፡ ግን ሲሳካ አልታየም፡፡
ገዢው ፓርቲና የመንግሥት ባለስልጣናት፣… የውጭ ኃይሎች አሻንጉሊት፣ የኢምፔሪያሊዝም ተቀጥላና ጥገኛ፣ የባዕዳን ተላላኪ ናቸው ብለን መኮነን አያቅተንም፡፡ ሕዝብን የካዱና፣ የሰላም ጠንቅ ናቸው፤… የሥልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም ሕዝብን አጣልተውና ከፋፍለው የሚገዙ ናቸው ብለን መወንጀልም እናውቅበታለን፡፡ የገዢው ፓርቲ የሥልጣን ጥሙ ለከት አጥቶ አገር ምድሩን ሁሉ አንድ ላይ ጨፍልቆ ለመግዛት አገሪቱን በጦርነት እሳት ይማግዳታል ብለን ማወገዝ አይከብደንም፡፡እንዲህ አይነት ውግዘቶች ከአጠገባችን የራቁበት ጊዜ የለም፡፡… ገሚሶቻችን የየዘመኑን መንግስት ስናወግዝ፣… ሁሉንም ጠቅልሎ፣ አንድ ላይ ጨፍልቆ የሚረግጥ አምባገነን ነው እንላለን፡፡
ገሚሶቻችን ደግሞ፣ “ሕዝብን በጎራ እያቧደነና እያጋጨ፣ አገሬውን ከፋሎ የሚገዛ መሠሪ ነው” እንላለን፡፡ተቃዋሚ ፓርቲ ወይም የሸፈተና ያመፀ ድርጅት ከሆነም፣ “አገሪቱን ጠቅልሎ ለመርገጥ ወይም ከፋፍሎ ለመግዛት ይፈልጋል” ብለን እንረግመዋን፡፡እንወነጅላለን፤ እናወግዛለን፡፡ እውነት ይሁን ውሸት… ብዙም አያሳስበንም፡፡ የጠላነው ፓርቲና የጠመድነው ፖለቲከኛ ላይ የሚወረወር ማንኛውም ውግዘት
እውነትም ሆነ ውሸት ይመቸናል፡፡ በእንዲህ ዓይነት ጭፍንነት ጦርነትን ማራባት እንጂ ሰላምን ማሰንበት አይቻልም፡፡ገዢ ፓርቲዎችንና ተቃዋሚዎችን እንደየጥፋታቸው ልክ ማውገዝ ብንችልም እንኳ፣ ስህተት ባንሰራም እንኳ፣ መፍትሄ ፈጥረናል ማለት አይደለም፡፡
ጥፋትን ማውገዝ ልማትን መፍጠር አይደለምና፡፡ እንግዲህ እየተባባሰ የመጣው የጭፍንነት ፖለቲካችን ለውግዘትና ለውንጀላ
የመሽቀዳደም አመላችን፣ የጦርነት ማራቢያ እንጂ የሰላም መፍትሄ ካልሆን፣….
ሁሉንም ፓርቲና ፖለቲከኛ እንደየስራው መውቀስ ተገቢ ቢሆንም፣…. መጥፎ ነገሮችን ማፍረስ ጥሩ ነገሮችን መገንባት ማለት ስላልሆነ ለብቻው መፍትሄ ካፈጠረልን…
እንዲያውም ውግዘትና በውንጀላ እሽቅድምድም ላይ ብቻ ከተጠመድን፣ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ውለን አድረን ወደ ወደ ሀሰት ውንጀላና ወደ ጭፍን ውንጀላ የምንሸራተት ከሆንን….
የሰላም ምህላና የሰላም መዝሙር፣ የፍቅርና የይቅርታ መነባንብ በጣም አስፈላጊ ቢሆኑም፣… ለብቻቸው ከሆኑ ግን ጦርነትን ለማስቀረትና ለማስቆም፣ ሰላም ለመፍጠርና ለማሰንበት አስተማማኝ መፍትሄ ካልሆኑልን፣…

እንዲያውም፣… መፍትሄ ወደ ማበጀት ስለማንሸጋገር የሰላም ምህላችንና መዝሙራችን፣ ቀስ በቀስ በጭፍን “ሰላም ወዳድና ፀረ ሰላም” ብለን ለመወነዳጀል አመቺ ሰበብ የምናደርጋቸው ከሆነ፣…
እነዚህ ሁሉ…. መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ተደራራቢ ችግሮችና እንቅፋቶች እንጂ ለሰላም የሚጠቅሙ አጋዥ አቅሞች አይሆኑልንም፡፡እንግዲህ ብዙ ስህተቶችንና ችግሮችን ጠቅሰናል፡፡ ችግሮችንና ስህተቶችን ማወቅ የመፍትሄው ግማሽ መንገድ ነው
ይባላል፡፡ እውነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ግን መፍትሄ አይደለም፡፡እናም መፍትሄ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡ጦርነትን ለመግታትና ለማስቆም ብቻ ሳይሆን ከሩቁ ለማስቀረት፣…
ሰላምን ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ለማሰንበትና ለማደላደል የሚያስችል መፍትሄ ያስፈልጋል፡፡ለዚህም፣ ጥሩ ዘዴ ሳይኖር አይቀርም፡፡ የእርስ በርስ ጥርጣሬና ሽኩቻችን፣ የጎራ የቡድን ጥላቻችን ለቀና ሀሳብና ለልባዊ ንግግር እንቅፋት እንዳይሆንብን ከዚህ የሚያድኑ ሁለት ምሳሌዎችን እንጠቅሳለን፡፡ከውጭ ጉዳይ ፈተናዎቻችን መካከል አንዱ፣ የአባይ ወንዝ ጉዳይ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የባህር በር ችግር ነው፡፡ ትልልቅ
ፈተናዎች ናቸው፡፡ለጊዜው፣ የአባይ ወንዝና የባሕር በር ፈተናዎች፣ ወደ ለየለት ግጭትና ወደ ጦርነት እንዲያመሩ መካላከል ችለና፡፡ ከግብፅና ከሌሎች ጎረቤት አገራት ጋር ወደ አስከፊ ጦርነት ሳንገባ፣ ለእነዚህ ፈተናዎች ሁነኛ መፍትሄ ማበጀት ከቻን ትልቅ ስኬት
እንደሚሆን አያጠራጥርም፡፡ ነገር ግን ተጨማሪ ጥቅም እናገኝበታለን፡፡ የውስጥ ችግሮችንም ለመፍታት የሚያገለግል ሁነኛ የሰላም ዘዴ እናገኛላን ማለት ነው፡፡ ይህን እንመለከታለን፡፡ከግብፅ ጋር ሰላም ለመፍጠር የሚያገለግል ሁነኛ የመፍትሔ መንገድ መፍጠር ከቻልን፣ የአገር ውስጥ የእርስ በርስ ሰላም ማስፈንና ማደላደል እንዴት ይከብደናል?
መፍትሔ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ግን በተጨባጭ መፍትሔውን እንየው፡፡

Read 483 times