Wednesday, 22 November 2023 20:16

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ሳምንታዊ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዳግም ማዘጋጀት ጀመረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከትምህርት ባሻገር ሁለንተናዊ የሰብዕና መገንቢያና የተሻለ የትምህርትና የሥራ አካባቢ ለመፍጠር ባህል ማዕከሉን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ማዕከሉ በየሳምንቱ ማክሰኞ የኪነ-ጥበብ ምሽት ዳግም ማዘጋጀት እንደሚጀምር የባህል ማዕከሉ ኃላፊ ተስፋዬ እሸቱ ገልጸዋል፡፡

ቅዳሜ፣ ማክሰኞና ሐሙስ ደግሞ ፊልም የሚያሳይ ሲሆን፤ በቀረቡት ፊልሞች ላይ በወር አንድ ጊዜ ውይይት ይደረጋል ብለዋል።

ባህል ማዕከሉ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ማኅበር ጥምረት ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነትም ተፈራርሟል።

Read 1088 times