Thursday, 09 November 2023 00:00

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ23ተኛው ዙር ውድድር ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ከፍተኛ የሆነውን የአትሌት አሸናፊዎች ሽልማት ሊሸልም ነው፡

Written by 
Rate this item
(0 votes)
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ23ተኛው ዙር ውድድር ከዚህ ቀደም ከተደረጉ ከፍተኛ የሆነውን የአትሌት አሸናፊዎች ሽልማት ሊሸልም ነው፡፡
ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ፡- የ2016 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. በሁለቱም ፆታ ላሉ አትሌቶች የ812,000 ብር ሽልማት ሊሸልም ነው፡፡ ካለፈው አመት በአጠቃላይ ከ30 በመቶ በላይ ብልጫ ያለውም ሽልማት ነው ተብሏል፡፡
በ ውድድሩ ላይ የወንድ እና የሴት አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው 200,000 ብር 100,000 እንዲሁም 50,000 ብር 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ለሚወጡ በቅደም ተከተል የሚሸለሙ ይሆናል። ያለፈው ዓመት ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት መጠን 150,000 እንደነበር ይታወቃል፡፡
ውድድሩን በቅርብ ጊዜ ካሸነፉ ወንድ አሸናፊዎች መካከል ሰለሞን ባረጋ (2010) ሀጎስ ገብረህይወት (2011)፣ በሪሁ አረጋዊ (2012) እና አቤ ጋሻው ሶስት ጊዜ በማሸነፍ ብቸኛ ወንድ አትሌት ሲሆን በሴቶች በኩል ያለምዘርፍ የኋላው ባለፉት ዓመታት (2012 እና 2014) ውድድሩን ሁለት ጊዜ ስታሸንፍ ሌሎች አሸናፊዎች ዘይነባ ይመር (2010)፣ ፎይት ተስፋዬ (2011) እና ጽጌ ገብረሰላማ (2013) ይገኙበታል።
የዘንድሮው ውድድር በግሎባል ስፖርት ኮሙኒኬሽን ስር ያሉ ሶስት ወጣት ዩጋንዳውያን አትሌቶችን ጨምሮ ጠንካራ የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች እንደሚሳተፉበት ይጠበቃል።
ጁሪ ቫን ደር ቬልደን ይህንን ውድድር “ለአትሌቶቻችን ጠቃሚ የመማሪያ ቦታ እና ማበረታቻም እንደሆነ እናምናለን” በማለት ገልፀውታል።
በዘንድሮው ውድድር የሚወዳደሩ ታዋቂ አትሌቶች ስም ዝርዝር ማክሰኞ ህዳር 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ይሆናል።
በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10 ኪ.ሜ. (1994-2016) ስለነበሩት ምርጥ ውድድሮች፡-
• በ1994 የመጀመርያው የሩጫ አሸናፊዎች ኃይሌ ገብረስላሴ እና ብርሃነ አደሬ ነበሩ። ባለፈው አመት የ22ኛ ዙር አሸናፊዎች አቤ ጋሻው እና ትግስት ከተማ ነበሩ።
• ሁለት አትሌቶች ገነት ጌታነህ (በ1997 እና 1998) እና ውዴ አያሌው (በ2000 እና 2001 ዓ.ም.) ብቻ የውድድር ዘመናቸውን በተሳካ ሁኔታ አስጠብቀዋል።
• ሁሉም የዚህ ውድድር አሸናፊዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሆነዋል። የኬንያ አትሌቶች በወንዶች ውድድር አንድ ጊዜ በሴቶች ደግሞ ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ሆነው አጠናቀዋል።
• ዉዴ አያሌዉ እና አቤ ጋሻው በውድድሩ ሶስት ጊዜ ያሸነፉ አትሌቶች ናቸው፡፡ ዉዴ በ2000፣ 2001 እና 2007 እና አቤ በ2009፣ 2013 እና 2015 ብቻ ናቸው።
• በወንዶች ፈጣን የማሸነፍ ጊዜ በ1999 (28፡18) በደሪባ መርጋ እና በሴቶች ያለምዘርፍ በ2014 (31፡17)
የ2016 የሶፊ ማልት ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ 10 ኪሎ ሜትር እሁድ ህዳር 19 ቀን 2023 ይካሄዳል። 45,000 ሯጮች ለውድድሩ ተመዝግበዋል።
ውድድሩ በ EBC የቀጥታ ስርጭት በ8፡18 ሰአት (ወንዶች) እና 8፡23 ሰአት (ሴቶች) በሃገር ውስጥ ሰአት አቆጣጠር (GMT + 3) እየተካሄደ ነው።
Read 531 times