Saturday, 19 August 2023 21:13

ኪ.ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን፣ ለመኖሪያ ቤት ችግር ምን ይዞ መጣ?

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

በ10 ዓመታት ውስጥ 100ሺ መኖሪያ ቤቶችን እገነባለሁ ብሏል


ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን፣ በሀገራችን እየተባባሰ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት፣ “Key-CHF” ሞዴል እና ማህበረሰቡ በሞዴሉ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችለውንና ለሺዎች የሥራ እድል ይፈጥራል የተባለውን ኪ አፊሊየት ፕሮግራም (KAP) አስተዋውቋል፡፡
የኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን  አመራሮች፣ ባለፈው ረቡዕ፣ ነሐሴ 10 ቀን 2015 ዓ.ም በሃያት ሪጀንሲ ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ  መግለጫ፤ በአገሪቱ  የሚስተዋለውን  የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት  ታልመው የተቀረጹ  ሞዴሎችን  ይፋ አድርገዋል፡፡
ኩባንያው፤ Key-CHF በተሰኘ  ሞዴሉ፣ በቀጣይ 10 ዓመታት  100ሺ ሰዎችን  የቤት ባለቤት ለማድረግ ማቀዱን የገለጸ  ሲሆን፤  በሞዴሉ መሰረትም፣ ግንባታቸው በወጪ ቀናሽ የግንባታ ቴክኖሎጂዎች የተጠናቀቁ ቤቶችን ከአልሚዎች ጋር በተደረገ ስምምነት በመግዛትና በዓመት ሁለት ጊዜ እድለኞችን በዕጣ በመለየት፣ የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
“Key-CHF” (Key Common Housing Fund) ሞዴል፣ ከአነስተኛ እስከ መካከለኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች በአነስተኛ የካፒታልና የአገልግሎት ክፍያ፣ እንዲሁም ለ30 ዓመታት በሚቆይ መጠነኛ ወርሀዊ ቁጠባ፣ በጠቅላላው እስከ 65 % ድረስ ብቻ በሚያደርጉት የገንዘብ አስተዋፅኦ፣ በዓመት ሁለት ጊዜ እድለኞችን በእጣ በመለየት፣ ቤት ፈላጊዎችን የቤት ባለቤት የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
ሁሉም ተመዝጋቢዎች እጣ እስኪወጣላቸውና በስማቸው ቤት እስኪገዛላቸው ድረስ የሚጠበቅባቸው ክፍያ ወርሀዊ መዋጮ ሲሆን፤ በዚሁ መሰረት የቤት ባለቤት ለመሆን የሚያስፈልገው 77,280 ብር ቅድመ ክፍያና  ከ2000 ብር የሚጀምር ወርሀዊ ቁጠባ ብቻ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ቀሪዎቹ ክፍያዎች  ተመዝጋቢዎች በስማቸው ቤቶች ከተገዙ በኋላ የሚፈጹማቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
ኪ ሃውሲንግ ፋይናንስ ሶሉሽን፤ በቤት ልማት፣  በተዘዋዋሪ የቁጠባ ፈንድ፣ በአይቲና ማርኬቲንግ መስኮች፣ በአገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሞያዎች የተቋቋመ አገር በቀል ኩባንያ እንደሆነ  ታውቋል፡፡

Read 1053 times