Sunday, 09 July 2023 17:15

ቴክኖ ሞባይል ካሞን 20 የተባለውን እጅግ ዘመናዊ ስልክ ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 በዓለማችን ከ70 በላይ አገራት ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ ሞባይል፣ ካሞን 20 የተባለውንና የአለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ የሆነውን ዘመናዊ ሞዴል ስልክ ለኢትዮጵያ ገበያ አቀረበ፡፡
በአያት ሬጀንሲ ትናንት ማምሻውን በተካሄደ ስነስርዓት አዲሱ ካሞን 20 ሞዴል ዘመናዊ ስልክ ለኢትዮጵያ ገበያ መቅረቡ ይፋ ተደርጓል፡፡
የኩባንያው የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለአገራችን ገበያ መቅረቡ ይፋ የተደረገው (Camon 20) ሞዴል ስልክ፤ በ108 ሜጋፒክሰል ካሜራ ፎቶና ቪዲዮ በጥራት በየትኛውም እንቅስቃሴ ውስጥ ሆኖ ለማንሳት ያስችላል የተባለ ሲሆን፤ ይሄው ዘመናዊ ስልክ ተጠቃሚዎች በፍጥነትና በምቾት ዘመናዊ አገልግሎቶችን ሁሉ ለማግኘት እንዲችሉ ያደርጋቸዋልም ተብሏል፡፡
አዲሱ ካሞን 20 ሞዴል ስልክ ለቴክኖ ሞባይልና በአጠቃላይ በአፍሪካ የሞባይል ኢንዱስትሪ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው መሆኑንና ኩባንያው የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት ሌት ተቀን የሚሰራ መሆኑን ማሳያ ምስክር ነው ያሉት የኩንያው የስራ ሃላፊዎች፤ ከተጠቃሚዎች የሚመጣውን ምላሽ ለመስማት ጓጉተናል ብለዋል፡፡
አዲሱን ካሞን 20 ሞዴል የማስተዋወቅ አካል የሆነውና በተለይም የቴክኖሎጂንና የፋሽንን ጥምረት አዋህዶ መተግበሪያ ማሳየትን አላማው ያደረገ ልዩ የፋሽን ትርኢትም በዚሁ የአዲሱን ሞዴል ሞባይ ስልክ የማስተዋወቅያ ፕሮግራም ላይ ተካሂዷል፡፡
ኩባንያው በአዲስ አበባ ከተማ ጎሮ የሚገኘው የኢትዮ አይሲቲ ፓርክ ውስጥ ያስገነባውን ለአገራችን የመጀመሪያ የሆነው ዘመናዊ ፋብሪካ ውስጥ የተለያዩ አይነትና ሞዴል ያላቸውን የቴክኖ ሞባይል ምርቶችን በመገጣጠም ለገበያ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡


Read 1625 times