Saturday, 17 June 2023 00:00

21ኛው “ናፍቆት የኪነጥበብ ምሽት” ነገ በአዳማ ይካሄዳል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   በአዳማ ከተማ የሚገኘውና በየወሩ ኪነጥበባዊ መሰናዶዎችን የሚያዘጋጀው የ”ግሪክ ኪነ ጥበባት” 21ኛ ምሽት የሆነው “ናፍቆት” የኪነ ጥበብ ምሽት በነገው ዕለት ከቀኑ 10፡00 በከተማዋ በሚገኘው ማፊ ሬስቶራንት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል፡፡ በእለቱ ግጥም፣ ወግ፣ መነባንብ፣ ሙዚቃና ሌሎችም ኪነጥበባዊ መሰናዶዎች እንደሚቀርቡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ገጣሚ ተስፋ ብዙወርቅ ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡ በእለቱ አንጋፋና ወጣት ደራሲያንና ገጣሚያን ሥራዎቻቸውን ለታዳምያኑ እንደሚያቀርቡም ለማወቅ ተችሏል፡፡


Read 985 times