Saturday, 20 October 2012 12:06

የጃፓን ፊልም አውደርእይ በመቀሌ ይቀጥላል

Written by  መልካሙ ተክሌ melkamutekle@gmail.com
Rate this item
(2 votes)

ኢትዮጵያ በሚገኘው የጃፓን ኤምባሲ አስተባባሪነት በአዲስ አበባ እየቀረበ ያለው የጃፓን ፊልም አውደርእይ በመቀሌ ከተማ እንደሚቀጥል አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡ ፊልሞቹ ከመጪው ማክሰኞ እስከ ሐሙስ በመቀሌ ከተማ እንደሚታዩ ታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከጥቅምት 5 ጀምሮ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በጣሊያን የባህል ተቋም እየቀረቡ ያሉት ፊልሞች የሚታዩት በነፃ ሲሆን Wanko, Hotel Hibiscus, After The Flowers, The Girl Who Leapt Through, Haru’s Journey እና The Twilight Samurai የተሰኙ ፊልሞች እንደሚታዩ ታውቋል፡፡

Read 1068 times Last modified on Saturday, 20 October 2012 12:13