በሃሊማ ሙዘይን (ሃሊ) የተዘጋጀው “I” ኔ የተሰኘ የግጥም መድብል ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ ከሁለት ወራት በፊት ቢታተምም፤ በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን ለአንባቢያን ሳይደርስ መቆየቱ ፀሐፊዋ ለዝግጅት ክፍላችን ተናግራለች፡፡ 85 ገፆች ያሉት መጽሐፍ በ19 ብር እየተሸጠ ሲሆን 78 ግጥሞችን ይዟል፡፡በነርስ ሙያ ላይ ስትሰራ የነበረችው ሃሊ፡፡ ባሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ ጊዜዋን ለጽሑፍ ሥራ እንደምታውል ተናግራለች፡፡