Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 22 September 2012 13:08

የአንጋፋዋ አርቲስት ሐውልት ተመረቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የዛሬ ዓመት መስከረም 2004 ላይ ያረፈችው የአንጋፋዋ አርቲስት አስናቀች ወርቁ ሐውልት ግንባታ ሰሞኑን ተጠናቆ ባለፈው እሁድ ተመርቋል፡፡ የክራር ንግስቷን ሐውልት ለማሰራት በአሜሪካ ያሉ አድናቂዎቿ ቃል ገብተው የነበረ ቢሆንም በተቻለ መጠን ለክብሯ ተመጣጣኝ ሐውልት ለመስራት ከ143 ሺህ ብር በመጠየቁና ገንዘቡ ሳይሟላ በመቅረቱ ለአንድ ዓመት ሊጓተት ችሏል፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ የኪነጥበባት በጐ አድራጐት ማህበር ከአርቲስት ሱራፌል ወንድሙ፣ ከጋዜጠኛ ብርሃኔ ንጉሴ፣ ከሙዚቀኛ ዳዊት ይፍሩ፣ ከገጣሚና ፀሃፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱና አርቲስት ዝናሽ ፀጋዬ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ነሀሱን ከሰጠ በኋላ ቀራፂ ብዙነህ ተስፋ ብዙነህ፤ ጐምቱዋን ከያኒ እንደሚወዳትና እንደሚያደንቃት በመግለፅ በነፃ እንደሰራ ለማወቅ ተችሏል፡፡አራት ኪሎ በቅድስት ስላሴ ደብር የሚገኘው የጐምቱዋ አርቲስት አስናቀች መቃብር ጠባብ መተላለፊያ መንገድ አጠገብ በመሆኑ ሐውልቱ እስኪሰራ እንዳይረጋገጥ ድንጋይ እየደረደሩ እና ቄጠማ እየጐዘጐ እንደነበር ልጇ ወይዘሮ ቢጡ ፈቂ ለአዲስ አድማስ ገልፃለች፡፡

 

 

Read 1576 times Last modified on Saturday, 22 September 2012 13:12