Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 18 August 2012 13:39

የጋዜጠኛ የእናት ፋንታ ሆቴል ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ያቀርባል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በኢትዮጵያ ሬዲዮ የመዝናኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባና ለረዥም ዓመታት “ምን ያዝናናዎታል” ዝግጅትን በማቅረብ የምትታወቀው ጋዜጠኛ የእናት ፋንታ ውቤ በከፈተችው ሆቴል ቋሚ ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች እንደምታቀርብ ገለፀች፡፡ የእናት ፋንታ በተለይ ለአዲስ አድማስ እንደገለፀችው፤ ከቤተሰቦቿ ጋር በከፈተችውና ፒያሳ በሚገኘው የ“ኤልቤት” ሆቴል ዝግጅቶቹ ከነገ ጀምሮ ይቀርባሉ፡፡ ከቋሚ ዝግጅቶቹ አንዱ ራሷ ጋዜጠኛዋ አባል የሆነችበት “ዜማ ብዕር” የኢትዮጵያ ሴት የሥነፅሑፍ ማህበር ወርሃዊ ዝግጅት ይገኝበታል፡፡

በተለይ ለሕፃናት ኪነጥበባዊ ዝግጅቶች ቅድሚያ እንሰጣለን ያለችው የእናት ፋንታ፤ ለኪነጥበባዊ ዝግጅቶቹ ከሞሃ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ፣ ከቢጂአይ ኢትዮጵያ፣ ከአርቲስት ቴዎድሮስ መኮንን (ቴዲማክ)፣ ከአርቲስት ዘለቀ ገሠሠና ከሌሎችም ድጋፍ እንደተደረገላት ገልፃለች፡፡

በነገው የመጀመሪያ ዝግጅት አንጋፋው የማስታወቂያ ባለሙያ አቶ ውብሸት ወርቃለማሁ እና ገጣሚና ፀሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ በክብር እንግድነት ሲገኙ ዲጄ ቤቢ፣ ዲጄ ሊ፣ ዲጄ ኤዲ፣ ዲጄ ጌት እና ዲጄ ናትሜሪ በሙዚቃ አቅራቢነት ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጋዜጠኛዋ በዚህ ምክንያት ከኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት መልቀቅ እንደማትፈልግ ተናግራለች፡፡

 

 

Read 1257 times Last modified on Saturday, 18 August 2012 13:46