Monday, 28 January 2019 00:00

“የመረጃ ነፃነት በኢትዮጵያ” መፅሐፍ ሐሙስ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የቀድሞው የዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል መስራች ከነበሩት አንዱ በሆኑት አቶ አማኑኤል አብርሃም የተፃፈው “የመረጃ ነፃነት በኢትዮጵያ” የተሰኘው መፅሐፍ የፊታችን ሐሙስ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ አምስት ኪሎ በሚገኘው ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፣ሚኒስትሮች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ደራሲያን ይታደማሉ የተባለ ሲሆን፤ በመፅሐፉ ላይ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡
 መፅሐፉ በዋናነት የተለያዩ ዓለማት የመረጃ ነፃነት ተሞክሮዎችን ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በመቀመር መረጃ ለማንና ለምን? በአገራችን የመረጃ ነፃነት ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች በመተንተን መፍትሄዎች ያቀርባል ተብሏል፡፡
በ199 ገፆች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በ120 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡    

Read 5290 times Last modified on Saturday, 26 January 2019 16:04