በታፈራ መልቲሚዲያና በሃብል መልቲ ሚዲያ የተዘጋጀው ውበትና ባህል የተሰኘ ኤክስፖ በሚቀጥለው ሳምንት ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ላፍቶ ሞል እንደሚከፈት አዘጋጆቹ አስታወቁ፡፡
በዚህ ኤክስፖ ላይ ባህላዊ አልባሳት ባህላዊ የቤት ቁሳቁስና ባህላዊ የቤት ማስዋቢያዎች በዋናነት ይቀርባል ተብሏል፡፡ የህፃናት መጫወቻዎች የኤክስፖው አካል ናቸው ተብሏል፡፡
ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚዘጋጀው የውበትና ባህል ኤክስፖ በርካታ ጐብኚዎች ይታደሙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Monday, 28 January 2019 00:00
ውበትና ባህል የተሰኘ ኤክስፖ በላፍቶ ሞል ሊቀርብ ነው
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና