በቅርቡ ለተቋቋመው የብሔራዊ ዕርቅ ኮሚሽን አባልነት ከ50 በላይ ታዋቂ ግለሰቦችና የአገር ሽማግሌዎች ተመለመሉ፡፡
የብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን አባላትን በተመለከተ ለውይይት በቀረበው ሰነድ ላይ እንደተጠቀሰው፤ ለኮሚሽኑ ከምሁራን፣ ከስነጥበብ ባለሙያዎች፣ ከታዋቂ የህግ ባለሙያዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከአክቲቪስቶች፣ ከአትሌቶች እና ከአባገዳዎች የተውጣጡ አባላት ተመልምለዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኮሚሽኑ አባልነት ተመርጠው ከቀረቡት መካከል የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝና የቀድሞ የደርግ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኮ/ል ጐሹ ወልዴ ይገኙበታል፡፡
ልኡል ራስ መንገሻ ስዩም፣ ልኡል በእደ ማርያም መኮንን፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ፣ ቀደማዊ መፍቲ ሐጂ ሁመር ኢድሪስ፣ ኡስታዝ አህመዲን ጂበል፣ ዶ/ር ምህረት ደበበ፣ መጋቢ ሃዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ፣ ፕ/ር ኤፍሬም ይስሃቅ፣ ፕ/ር አህመድ ዘካሪያ፣ አባገዳ በየነ ሰንበቶ፣ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አትሌት ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ገ/እግዚአብሔር ገ/ማርያም ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በተጨማሪም የጋሞ፣ የሲዳማና የሌሎች አካባቢ የሀገር ሽማግሌዎች በእርቅ ኮሚሽኑ አባል እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ለውይይት ከቀረበው ሰነድ ዝርዝር ለመረዳት ተችሏል፡፡
Saturday, 15 December 2018 14:39
Published in
ዜና