Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 April 2012 12:56

የኦፕራ ቲቪ አልተሳካለትም

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኦፕራ ዊንፍሬይ “ኦውን ኔትዎርክን ማቋቋም ኪሊማንጃሮን መውጣት ነው” ስትል አማረረች፡፡ ስርጭቱን ከጀመረ 16 ወራት ያስቆጠረው የኦፕራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከጅምሩ ከ200 ሚ.ዶላር በላይ ኪሳራ ማድረሱን አንዳንድ መረጃዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ዋናው ችግር በቂ ተመልካች አለማግኘቱ ሲሆን ይህ ሁኔታም  ከማስታወቂያ የሚገኘውን ገቢ አሳንሶታል ተብሏል፡፡

ኦፕራ ዊንፍሬይ በደንብ ሳንዘጋጅ እና ሳንደራጅ ስርጭት መጀመራችን ዋጋ እያስከፈለን ነው ማለቷን  የጠቆመው አሶስዬትድ ፕሬስ፤ የኦፕራ ጣቢያ  ከታዋቂዎቹ ሲቢኤስ፤ ኤንኤቢሲ እና ጂኤምኤ ኔትዎርኮች ጋር የመፎካከር አቅም የለውም ብሏል፡፡ በቴሌቭዥን ጣቢያው ከኦፕራ ዊንፍሬይ ጋር በመሻረክ ከ300 ሚሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ያደረገው “ዲስከቨሪ ኮሚኒኬሽን”ም ጣቢያው በደረሰበት ኪሳራ እየተጎዳ ነው፡፡ ኩባንያው በቅርቡ የማኔጅመንት ቀውስ እንደገጠመውና ከሰራተኞቹ እንደቀነሰ ተገልጿል፡፡

የኦውን ጣቢያ ስርጭት በየቀኑ የሚያገኘው ተመልካች በአማካይ ከ180ሺ አይበልጥም፡፡ ኦፕራ የዊትኒ ሂዩስተንን ቤተሰብ ቃለ መጠይቅ ስታደርግ 3.5 ሚሊዮን እንዲሁም ከሌዲ ጋጋ ጋር በቀጥታ ስርጭት ሲያወጉ 800ሺ ታዳሚዎች እንደነበሯት ያመለከተው ሲቢኤስ፤ ከዚያ ውጭ ግን በጣቢያው መደበኛ ፕሮግራሞች እንዳልተሳካላት ጠቁሟል፡

 

 

Read 1500 times Last modified on Saturday, 14 April 2012 13:00