Sunday, 21 August 2016 00:00

“አንባቢያን” የመፅሐፍት አውደ ርዕይና ባዛር ተከፍቷል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

‹‹አንባቢያን!›› በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ቲያትር ህንፃ ስር በሚገኘው የአርት ጋለሪ ክፍል ውስጥ ከትናንት በስቲያ የመፃህፍት አውደ ርዕይና ባዛር የተከፈተ ሲሆን እስከ ነሐሴ 22 ድረስ ለ9 ቀናት እንደሚቆይም ታውቋል፡፡ በዚህ አውደ ርዕይና ባዛር ላይ የተለያዩ መጽሐፍ ነጋዴዎች የሚሳተፉ ሲሆን ከገበያ የጠፉና አዳዲስ መጽሐፍቶች ከ15% እስከ 50% ቅናሽ ተደርጎባቸው ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ አዘጋጆቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

Read 636 times