Saturday, 07 May 2016 13:29

“ዛሬም ፋሲካ” የንግድ ትርኢትና ኤክስፖ በቢሾፍቱ ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ትልልቅ ባዛርና ኤክስፖዎችን በማዘጋጀት የሚታወቀው “ሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን” የዳግም ትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ “ዛሬም ፋሲካ” የተሰኘ የንግድ ትርኢትና ኤክስፖ በቢሾፍቱ ከተማ ስታዲየም ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ከፈተ፡፡ ለ11 ቀናት በሚቆየው በዚህ የንግድ ትርኢትና ባዛር ላይ በርካታ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን በቀን ከሰባት እስከ 10ሺህ ጐብኚዎች ሰዎች ይጐበኙበታል ተብሎ እንደሚጠበቅና እንደነ ጃሉድ፣ ጌታቸው ኃይለማርያም፤ ዲጴ ሴም፣ ያሬድ ጥጉ (መርካቶ ሰፈሬ) ፣ ቴዲ እና የመሳሰሉት ከ10 በላይ አንጋፋና ታዋቂ ድምፃዊያን ኤክስፖውን እንደሚያደምቁትና እልልታ ባንድና ቀሀስ ባንድ ድምፃዊያኑን እንደሚያጅቧቸው የሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን ሀላፊዎች አቶ አዶኒክ ወርቁና ወ/ሮ ሃና ኢተቻ ተናግረዋል፡፡ ለ11 ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤክስፖ፤ የስራ ፈጠራ ውድድር፣ የንግዱን ማህበረሰብ የሚያሳትፉ አወደጥናቶችና መሰል ዝግጅቶች የሚካሄዱ ሲሆን በመግቢያ ትኬት እድለኛ ለሆኑ በርካታ ሽልማቶች መዘጋጀታቸውም ተገልጿል፡፡ ሀበሻ ዊክሊ ፕሮሞሽን በአገር ውስጥ ካዘጋጃቸው ኤክስፖዎች መካከል በተለይ በ2008 ዓ.ም አዲስ አመት ያዘጋጀው ኤክስፖ በአይነቱና በስኬታማነቱ ተጠቃሽ እንደሆነ ከኃላፊዎቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Read 1007 times