Saturday, 12 December 2015 11:45

“ወሰንን መሻገር ፌስቲቫልና ጉባኤ” የመዝጊያ ስነስርዓት ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 “8ኛው አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” የሥዕል አውደ ርዕይ ከትናንት በስቲያ ምሽት በሸራተን አዲስ  ተከፈተ፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ 50 እውቅ ሰዓሊያን የሚሳተፉ ሲሆን አስር አስር ስራዎቻቸውን በድምሩ 500 ስዕሎች የቀረቡ ሲሆን ከሀምሳዎቹ ሰዓሊያን 34ቱ ስራቸውን ሲያቀርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የዘንድሮው አውደርዕይ ለሴትና ለወጣት ሰዓሊያን ትኩረት እንደሰጠም ተጠቁሟል፡፡ የስዕል አውደ ርዕዩ እስከ ፊታችን ሰኞ ድረስ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ “አርት ኦፍ ኢትዮጵያ” በየዓመቱ በሸራተን አዲስ የሚቀርብ ትልቅ የስዕል አውደ ርዕይ ሲሆን ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ መዘጋጀቱ ነው፡፡  

Read 860 times