Saturday, 12 December 2015 11:43

የቅድስት ይልማ “መባ” ፊልም ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

       የቅድስት ይልማ ዘጠነኛ ሥራ የሆነው “መባ” የተሰኘ ፊልም ባለፈው ማክሰኞ ምሽት በብሄራዊ ቴአትር ተመረቀ፡፡ በ “አንድ ሁለት ሦስት ስቱዲዮ” ተዘጋጅቶ በጋላክሲ ፊልም ፕሮዳክሽን የቀረበው ይሄው ፊልም፤ የአንድ ሰዓት ከሀምሳ ርዝመት ያለው ሲሆን ሙሉ ቀረፃው በአዲስ አበባና በዙሪያዋ መካሄዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፊልሙ ላይ የአዕምሮ ህሙማን ከመድኀኒት ይልቅ ፍቅር ሲፈውሳቸው የሚታይ ሲሆን፤ በመሪ ተዋናይነት አማኑኤል ሀብታሙ፣ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ፣ እድለወርቅ ጣሰው፣ ጆሴፍ ዳንኤልና ከ500 በላይ ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት እንደፈጀም ታውቋል፡፡ የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ቅድስት ይልማ፤ ከዚህ ቀደም “ኮሌጅና ውበት”፣ “ረቡኒ”፣ “ከእለታት”፣ “ጢባ ጢቤ”፣ “ገንዘብና ፍቅር (ቁጥር 1 እና 2)” እና ሌሎችንም ፊልሞች ፅፋ በማዘጋጀት እውቅናና ተወዳጅነትን ያተረፈች ሲሆን በተለይ “ረቡኒ” የተሰኘው ፊልሟ በበርካታ ፌስቲቫሎች ላይ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡ “መባ” ፊልም መታሰቢያነቱ በ “ረቡኒ” ፊልም ላይ የባህል ሀኪሙን የ“ዮቶርን” ገፀ ባህሪ ለተጫወቱትና በቅርቡ ህይወታቸው ላለፈው አርቲስት አብነት አየለ እንደሆነ በምርቃቱ ላይ ተገልጿል፡፡

Read 3112 times